>
5:14 pm - Sunday April 20, 2042

"የእስላም ሚዛን" (ክፍሉ ሁሴን)

“የእስላም ሚዛን”

ክፍሉ ሁሴን

 

ሚዛናዊ ነን የሚሉ ምርጥ የኢትዮጵያ አየር ኃይል መኮንኖችን ፎቶ ደርድረው ካራማራን ሲዘክሩ እነዚህኑ ምርጥ መኮንኖችንና ሌሎች ስንትና ስንት የኢትዮጵያን ጀግኖች እንደመተተኛ ጥላወጊ አበላሽቶ የፈረጠጠውን አካይስት መንግስቱ ኃይለማሪያምንም እንደ ጀግና በማወደስ ዓይነት ሲያነሳሱት ስላየን በማያሻማ ሁኔታ መዝገቡን ለማቃናት (to set the record straight in no uncertain terms እንዲል) የሚከተለውን እንላለን።

ለነገሩ ሚዛን እንዲህ የተሰበረው ደንበኛን ስለማክበር፤ ከፈረንጅ ወይም ከንግድ ሥራ ኮሌጅ ሳይማሩ “እትይዬ! ጋሽዬ!” እያሉ በደጉ ዘበን እየመረቁ ይሸጡልን የነበሩትን ታታሪ ነጋዴዎቻችንን “የእስላም ሚዛን” እያልን ያለስማቸው ስም ስለሰጠን ተረግመን ይሆናል።

< በፎቶው ላይ ከራሰበራውና ሸበቶው መኮንን በስተቀኝ የተቀመጡት፦

1ኛ. ኮሎኔል ዶክተር ጌታቸው አወቀ በአብራሪነት ሰልጥነው ክንፋቸውን ካገኙ በኋላ ዩጎዝላቪያ ተልከው ህክምና ሳይንስ ተምረው የጤና መስፈርትን በመመርመር ለአብራሪነት የምስክር ወረቀት ለመስጠት የሚያበቃ ሙያ አካብተው ከፈረንጆቹ በመረከብ የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ የአየር ኃይሉ flight surgeon ለመሆን በቁ። እኒህን አገራቸውን በታማኝነት ያገለገሉ ምርጥ መኮንንና ከፍተኛ ባለሙያ የመንግስቱ ኃይለማሪያም ጀሌዎች በግንቦት 8 መፈንቅለ መንግስት እጅግ አሰቃቂ በሆነ አረመኔነት አስመራ ላይ ገደሏቸው።

2ኛ. ከሳቸው ቀጥሎ ያሉት በተዋጊ ጄት አብራሪነት አገራቸውን ከዚያድ ባሬ ወረራ የተከላከሉ፤ በበረራ አስተማሪነትም እንደሳቸው የተዋጣላቸውን ጀግና አብራሪ ብርጌዲዬር ጄኔራል አሸናፊ ገብረፃዲቅ ዓይነትን ያፈሩ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ከሀይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ፋክልቲ የኤል ኤልቢ ዲግሪም የነበራቸው ባለሙያ፣ ምሁርና ስመጥሩ መኮንን ነበሩ። ብርጌዲዬር ጄኔራል ተስፉ ደስታ የሚባሉትን እኒህንም ከፍተኛ መኮንን ከሌሎች አስራ አንድ መኮንኖች ጋር መንግስቱ ኃይለማሪያም በግንቦት 1982 ዓ.ም በፍፁም ጨካኝነት እና ነውረኝነት ረሸነ።

3ኛ. ከጄኔራል ተስፉ ጎን ያሉትም በተዋጊ ጄት አብራሪነት፣ አስተማሪነት እና ስኳድሮን አዛዥነት ያለ እረፍት ከደብረዘይት፣ ድሬዳዋ፣ አስመራ እየተመላለሱ አገራቸውን ከጠላት የተከላከሉትን ጀግና መኮንን የመንግስቱ ኃይለማሪያም ጀሌዎች ግንቦት 8, 1981 አስመራ የሚገኘው የአየር ኃይል መደብ አዛዥ በነበሩበት ጊዜ ረሸኗቸው። ብርጌዲዬር ጄኔራል ንጉሴ ዘርጋው ይባላሉ። ይሄ ሳይወሳ፣ ይሄ ሳይዘከር ነው እንደመንግስቱ ኃይለማሪያም ያለ የኢትዮጵያን ጦር ኃይል ያሰደበ ፈርጣጭ እና አረመኔ በካራማራ ድል ላይ የሚወደሰው ወይም የሚወሳው!

Filed in: Amharic