>
5:13 pm - Saturday April 18, 3407

በፍጥነት እየተዛመተ የሚገኘው የዓለማችን አደገኛ በሽታ!!!

በፍጥነት እየተዛመተ የሚገኘው የዓለማችን አደገኛ በሽታ!!!

IbroChumeta 
• ጣልያን ብዙ መዝናኛዎች እስፖርት ማዝዉተሪያዎች  ትምህርት ቤቶች ዝግ ናቸው መንግስቱ እስካሁን ድረስ 3400 በላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች እንዳሉ አረጋግጡዋል ይህ ማለትም አውሮፖ ውስጥ ጣልያን በኮሮና በሽታ ብዛት ከፍ ያለ ቁጥር ያለባት ትሆናለች ።
• የኢራን መንግስት ማዛንድራን የተባለች ከተማ ዋናውን መንገድ ዘግቱዋል የተለየ ፍተሻ እና ጥንቃቄም እያደረገ ነው !
• አውስትራሊያ ሲድኒ በከፍተኛ ትምህርት ቤት በተደረገ ምርመራ በተማሪዎች ላይ ቫይረስ በመገኘቱ አብዛኛው ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ተደርጉዋል !
• ሳውዲ አረብያ መካን በሚገርም እና በሚያስደነግጥ  ሁኔታ ዛሬ ባዶ አርጋለች  የተባበሩት አረብ ኤመሬት ከእረፍት ግዜ ቀደም ብሎ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ እና የጁምአ ሰላት ደሞ ከአስር ደቂቃ እንዳያልፍ የመንግስት ሚዲያዎች ገልጸዋል ።
• አለም ላይ ከ100ሺ በላይ ቫይረሱ ያለበት ሰው አለ ቻይና ላይ ይጀመር እንጂ አሁን እያስፈራ ያለው ሌሎች ሀገሮች ላይ እያሳየ ያለው ፍጥነት ነው ቻይና ላይ እንደውም  የተረጋጋ ይመስላል !
• የአየር መንገዱ ተቆጣጣሪ IATA አየር መንገዶች በኮሮና በሽታ ምክንያት 115 ቢሊየን ዶላር እንዳጡ ተናግረዋል ፣ እንዲሁን በተለያዩ ዘርፎች እሚሰሩ የግል ድርጅቶችም በቱሪዝም ምናምን ከ 215ቢሊየን ዶላር በላይ እንዳጡ ተናግረዋል ።
• ትዊተር ለሰራተኞቹ በቤታቸው ሆነው በኦን ላይን ስራቸውን እንዲሰሩ ፈቅዱዋል አብዛኛው አውሮፖ ህንድ እና መካከለኛው ምስራቅ ያሉ መስራቤቶች በኦን ላይን ሚሰሩ ሰራተኞችን እቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲከታተሉ ፈቅደዋል !
• ህንድ የተለያዩ  ስጋዎችን መብላት መቆም አለበት እና እጅ ለእጅ መጨባበጥ ቀርቶ የድሮ የባህላችን 🙏🏻ነመስቴ መሆን አለበት ብለዋል አንድ ትልቅ የመንግስት ባለስልጣን !
Filed in: Amharic