>
5:13 pm - Friday April 19, 8069

"አጤ ምኒልክና አርሲ!!!" (ማቲዎስ ናታኒም)

“አጤ ምኒልክና አርሲ!!!”

 

ማቲዎስ ናታኒም
✍ አጤ ምኒልክ እኛ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በነጻነት እንኖር ዘንድ ብዙ መስዋዕትነትን ከፍለዋል ከዚህ ባሻገር በውጭ ሀገር የነበረውን ጥበባዊ ሥራ ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡ ሰው ናቸው በመሆኑም ኢትዮጵያን መሥርተው በእግርዋ ያቆሙ የፍቅር ንጉሥ ናቸው ዳሩ ግን በዚህ ዘመን አጤ ምኒልክ በድለውናል ብለው ከሚያስቡ አካባቢዎች መካከል አንዱ #አርሲ ነው ነገር ግን እምዬ ምኒልክ ለአርሲዎች ያለቸውን ልዩ ፍቅር አንጋፋው የታሪክ ጸሐፊ #ጳውሎስ_ኞኞ “አጤ ምኒልክ” በሚለው መጽሐፋቸው ሲጽፉልን እንዲህ ብለዋል፦
“ደጃች ወልደ ገብርኤል አርሲን ለማቅናት ዘምተው አገሩን ቢይዙም የአርሲ ኦሮሞ አንገዛም እያለ በማስቸገሩ ምኒልክ በ1874 ዓ/ም ዘምተው ነበረ አብዛኛው የአርሲ ሕዝብ አሜን ብሎ ሲገብር አንዳንድ ባላባቶች አስቸግረው ነበር ምኒልክም በ1874 አርሲን መትተው አስገበርኩ ብለው ተመለሱ የምኒልክን መመለስ ያወቀው የአርሲ ሕዝብ እንደገና በገዢው በደጃዝማች ወልደገብርኤል ላይ አመፀ
ምኒልክ በ1878 ዓ/ም እንደገና ወደ አርሲ ለመዝመት ግንቦት 5 ቀን ከእንጦጦ ተነሱ በሶዶ፣ በከንባታ፣ በዝዋይ አልፈው ጭላሎን፣ ሳቶን፣ ዲጋሎን አስገብረው አልባሶ ሜዳ ሠፈሩ በዚህም ጊዜ #ኮጂ የሚባለው የአርሲ ባላባት ለሊት ከደጃዝማች ወልደገብርኤል ሠፈር ገብቶ አደጋ አደረሰ 700 ያህል ሰዎችም ገደለ ምኒልክ የሠፈሩት ከደጃዝማች ወልደገብርኤል ሠፈር ራቅ ብለው ነበርና የአደጋውን መድረስ አልሰሙም በዚያም ለሊት አንዲት የሸሸች ሴት ከንጉሡ ሠፈር ገብታ የአደጋውን መድረስ ነገረች በማግስቱም ምኒልክ ለደጃዝማች ወልደገብርኤል ርዳታ ላኩ የእርዳታውን መድረስ ያላወቁ የአርሲ ሕዝብ እንደልማዱ ለሊት አደጋ ለመጣል ሲመጣ የምኒልክ ሠራዊት ፈጀው ከዚህ በኃላ አንዳንድ ጥቃቅን ግጭቶች ከመደረጋቸው በስተቀር የአርሲ ሕዝብ ገበረ ንጉሥ ምኒልክም ለአርሲ አጎታቸውን ራስ ዳርጌን ሾሙ
የአርሲ ባላባቶች በገበሩበት ጊዜ የምኒልክ ሠራዊት ከአርሲ ሕዝብ ብዙ ሰው ማርኮ ነበረ በዚያን ዘመን በየትም አገር ላይ እንደሚደረገው ሁሉ በጦርነት የተማረከ ለማራኪው ባርያ ይሆን ነበረ የሸዋውም የምኒልክ ሠራዊት የማረከውን ሰው ባርያ አድርጎ ያዘ ይህን ያወቁት ምኒልክ በዚያው በአርሲ ውስጥ እንዳሉ ሠራዊታቸውን ሰብስበው አዋጅ አስነገሩ አዋጁም  “…አሩሲን ከግራኝ ወዲህ የገዛውና ያስገበረው የለም እኛ ጥንትም የኛ ነው በማለት መጣንበት እንጂ እርሱ አልመጣብንም ባለማወቁ እከላከላለሁ ብሎ አለቀ ተጎዳም ግን ባርያ አድርገን ልንገዛው አይገባንም ወንድማችን ነውና የማረከውን የሰው ምርኮኛ ሁሉ ልቀቅልኝ በአዋጅ ከለመንሁህ በኃላ ወስልተህ የአሩሲን ሰው ባርያ አድርገህ የያዝህ ከተገኘህ እጣላሃለው ልቀቅ ብያለሁና ልቀቅ…ላምና ከብቱ ለስንቅህ ይበቃሃልና ሰውን ልቀቅልኝ።…” የሚል ነበረ ከዚህ በኃላ የምኒልክ ወታደር የሚሸጠውም ሆነ የሚያሠራው ባርያ(ምርኮኛ) በማጣቱ ቢናደድም የያዘውን ሁሉ ለቀቀ።” በማለት ጽፈውልናል።[አጤ ምኒልክ በጳውሎስ ኞኞ ገጽ 29]
✍ እንግዲህ የእኚን የፍቅር ንጉሥ ታሪካቸውን ሊያጠለሽ የተቀነባበረው የሀሰት ታሪክን በመስማት ባለማወቅ እምዬን የጠላህ ሆይ እነሆ አጤ ምኒልክ ፍቅር ናቸውና ልብህን ለእምዬ ፍቅር ክፍት አድርግ ሰው ናቸውና ስህተት እንኳን የሰሩት ቢኖር ከስህተታቸው ተምረህ በጀግነታቸው ጀግነህ ኩሩ ኢትዮጵያዊነትህን አስቀጥል።

👉ክብር ለእምዬ ምኒልክ!

Filed in: Amharic