>

አድዋ! - ወርቃማው የክተት አዋጅ! (በፍርድ ዘ ፍሬ ካህን)

አድዋ! – ወርቃማው የክተት አዋጅ!

በፍርድ ዘ ፍሬ ካህን
“ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ፤ሃገር አስፍቶ አኖረኝ። እኔም እስካሁን በልዑል እግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ።ከእንግዲህም ብሞት ሞት የሁሉ ነውና ለኔ ሞት አላዝንም።ደግሞ ልዑል እግዚአብሄር አሳፍሮኝ አያውቅም።ከእንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠረጥረውም። አሁንም አገር የሚያጠፋ፤ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት ልዑል እግዚአብሄር የወሰነልንን ባህር አልፎ መጥቷል። እኔም የአገሬን ከብት ማለቅ የሰውን መድከም አይቸ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር።
አሁን ግን በልዑል እግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም። የአገሬ ሰው ከአሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም፤ አንተም እስካሁን አላስቀየምከኝም። አሁንም ጉልበት ካለህ በጉልበትህ እርዳኝ፤ጉልበት የሌለህ ለልጅ፣ ለሚስትህና ለሃይማኖትህ ስትል በሃዘን እርዳኝ። ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ አልተውህም፤ እግዝዕትነ ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም።ዘመቻየም በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ።”
                 የአፄ ምኒልክ 2ኛ ክተት አዋጅ
                  መስከረም 7/1888 ዓ.ም
Filed in: Amharic