>

"የቀረበውን ሹመት ለመቀበል ያስቸግረኛል !!" (አቶ ዮሃንስ ቧያለው)

“የቀረበውን ሹመት ለመቀበል ያስቸግረኛል !!”

 

‹‹አሁን ተቋሙ ባለው የሕዝብ አመለካከት በተቋሙ መሥራት የምችልበት ሁኔታ ሥለሌለ የቀረበውን ሹመት ለመቀበል ያስቸግረኛል!?!››   አቶ ዮሃንስ ቧያለው

በጋሻው ፈንታሁን
አዲሱን ምደባ በዜና እንደሰሙ የተናገሩት የቀድሞው የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሃንስ ቧያለው በዜና ከመስማታቸው በፊት በፌደራል ደረጃ ኃላፊነት እንደሚሰጣቸው እንጅ የትኛው መስሪያ ቤት እንደሚመደቡ እውቅናው እንዳልነበራቸው ለአብመድ ገልጸዋል፡፡
‹‹በአሁኑ ጊዜ እራሴን ሳዳምጠው እና ስመረምረው በዚያ ተቋም መሥራት ቢኖርብኝ እንኳ አሁን ተቋሙ ባለው የሕዝብ አመለካከት በተቋሙ መሥራት የምችልበት ሁኔታ ሥለሌለ የቀረበውን ሹመት ለመቀበል ያስቸግረኛል፤ ስለሆነም የሕዝቡን ትግል በተለያየ መልኩ አስተዋጽኦ በማድረግ ፓርቲው ጉዞው እንዲጠናከር በማድረግ በሌላ አግባብ ላገለግል እችላለሁ እንጅ የተመደብኩበት ተቋም አሁን ባለው ስያሜ እና ሥዕል በተቋሙ ለማገልገል እንደማልችል ገልጫለው፡፡ ምደባውን ከሰማሁ በኋላም ምደባውን እንደማልቀበለው ሪፖርት አድርጌአለው›› ብለዋል አቶ ዮሃንስ  ቧያለው፡፡
Filed in: Amharic