>
5:13 pm - Saturday April 20, 2047

አቶ አባይ ጸሀዬና አቶ ስዩም መስፍን ምነው እንዲህ ወረዱ ፣ ቀለሉሳ፣ አበዱ እንዴ??? (አስገደ ገብረስላሴ) 

አቶ አባይ ጸሀዬና አቶ ስዩም መስፍን ምነው እንዲህ ወረዱ ፣ ቀለሉሳ፣ አበዱ እንዴ???

አስገደ ገብረስላሴ 
ትግራይ እንደእነ ዶ/አረጋዊ በርሀ፣ግደይ ዘርአጽዮን፣ያሉ  ሌሎች ቂመኛ  ባንዳዎች  ትግራይ እንዳይረግጧት ረመጥ እናደርጋት አለን አባይ ጸሀዬ!  የመገንጠል አቀንቃኝ አቶ ስዩም መስፍንም እኛ ልንገነጠል ከሆን ያች ኢትዮጱያ የምትባልም አብረን ነው ይዘናት የምንገነጠል ብሎዋል  ።
 አባይ ጸሀዬ እና ስዩም መስፍን   በለካቲት 11 የህዋሓት ትጥቅ ትግል የተጀመረበት በአል ሲከበር  ዋዜማ በሀወልት ሰማአታት ሀወልት  አዳራሽ እጅግ ቡዙ ሙሁራን ፣እድምተኛ እንግዶች ፣ ነባር  ታጋዮች  ፣የንግድ   ማህበረሰብ   መቐለ  አካባቢ ነዋሪዎች ፣ የተሰው ታጋዮች ወላጆች ፣የሀይማኖት አባቶች  በተሰበሰቡበት የ45 አመት የህዋሓት ታሪክ ለትውልድ  በፓኔል መልክ ለማስተላለፍ  ተብሎ በመድረክ ሲቀርቡ የፓኔሉ ተሳታፊዎች አነአባይ ጸሀዬ  ተሞክሮ ሊያስተላልፉ ፊት ለፊት ተሰብሳቢ ቀርበው ሲታዩ  የሚያውቃቸውና የማያውቃቸው ሁሉ ያለልዩነት በጭብጨባ በእልልታ ነበር አዳራሹ ያንቀጠቀጠው ።ዲስኩር ከጀመሩ በኃላ ግን ውስጠ ጉዳቸው የማያውቁ  ቅን ሙሁራን እና እንግዶች ምን ሊያቀርቡልን ይሆን ብለው በጉጉት  ሲጠብቁ   የነበሩ  እንግዶች  የነስዩም መስፍን ደስ የማይል የአላማቸውን አቃራረብ  ሲሰሙ ሁኔታው ድንጋጤ እየፈጠረባቸው በዝምታ ሲመለከቱ ( ተደራጅተው የገቡ  ወጣት አባሎቻቸው  ) ሌሎች እጅግ ብዙ ሰዎች በተለይ ያልበሰሉ በህዋሓት መሪዎች በአጉል የውሼት ታሪክ ጭንቅላታቸው  የታጠበ   በጭፍን ስሜት ሲያንጨበጭቡላቸው እነዛ ከሩቅ  ፣ከቅርብ ፣ከክልሎች የመጡ ፈደራሊስት ብሎው የታደሙ ሳይቀሩ እነአባይ ጸሀዬ ስዩም መስፍን ፣መረሳ ጸሀዬ ባስተላለፉት የእብደት አስተሳሰባቸው በህሊናቸውም በመሰረተ ሀሳብም ፍጹም አልተቀበሉትም ።በተለይ ከአገው የመጡ ታዳሚዎች እንገንጠል የምትለው ቃል በግልጽ ተቃውሞውታል ። እኔም ለአገው ታዳሚዎች ብሯቮ ነው እምላቸው ።
በአጠቃላይ በቅንነት የህዋሓት ታሪክ ሊያውቁ  የመጡ የፓኔሉ ታዳሚዎች ጥሩ ነገር ይጠብቁ ስለነበር  ፤ በተግባር ግን የሚያቀርቡት ተሞኩሮ  እየተዛላበዱ አገር የሚከፋፍል አጀንዳ እያራመዱ እንዳሉ  መሆናቸው እየተገነዘቡ ሲሄዱ በአቀራረባቸው ተስፋ ቆርጠው ማማት ጀመሩ ፣በምሳ በቁርስ ጊዜም በግልጽ የመቃወም ድምጽ ያሰሙ ነበር ። እነዛ በህዋሓት ተመልምለው የመጡ ቤተሰብ ግን  በአጉል ስሜት ሲነዱ የነበሩ  እነዛ ፓኔሊስት ሲያቀርቡት የነበሩ ሀቅ ይሁን ውሼት ፣ትርጉም ያለው ተሞኩሮ ይሁን አይሁን የህዋሓት ቁንጮዎች በመሆናቸው አቅራቢዎች  በጭፍኝ ተደስተው በጭብጨባ ቢያነጉዱት   ፣ምራቃቸው የዋጡ አስተዋዮች ግን የእነ አባይ ጸሀዬ ጸረዲሞክራሲ ዲስኩሩ የወረደ መሆኑ እየተገነዘቡ ሲጓዙ ለወረደ (የወደቀ) ሀሳባቸው  ሲሰሙ እጀጉን ስሜታቸው የሚገድሉ  ቂም አዘል ንግግሮች ስለነበሩ  ሞራላቸው ተነኩ ።
 በፓኔሉ ታድመው የመጡባት ቀንም ሲረግሙ ይሰሙ ነበር ። የፓኔል ተሳታፊዎች መድረኩ ሲሰለቻቸው በውሀ ቀጠነ ምክንያት እየፈጠሩ ከአዳራሹ
ወጣ ገባ ይሉ ነበር።ስብሰባ ትተውም በከተማ መጠጣቸው ይጨልጡ ነበር። ።ለተሰብሳቢዎች ካባሳጩዋቸው ነጥቦችም ፤
1ኛ ተሰብሳቢዎች ከአባይ ጸሀዬ ይጠብቁት የነበረ ዲሞክራሲያዊ የተሞክሮ ልምድ ፣ፍቅር ፣ልዩነት በዲሞክራሲያዊ ውይት ሰላማዊ የግርጭት አፈታት ልምድ  ነበር ። ነገር ግን አይኑ ያፈጠጠ ፋሽሽታዊ ዛቻ የተሞላው በወገኖቹ የሞት ፍርድ (ጦርነት ) አውጆ ቁጭ አለ ። ከጦርነት አዋጅም  አንዱ እነ አረጋዊ በርኸ ፣ግደይ ዘርኣጽዮን እና ሌሎች ቂሞኞች  ባንዳዎች ፣ ቀንደኛ  ጠላቶች ስለሆኑ  ወደ ትግራይ ብቅ አይሏትም ትግራይ ረመጥ ሆና ታቃጣላቸው አለች አለ ፣ አብዛኛው ተሰብሳቢ ከማንጨብጨብ ተቆጥቦ  ዝምታን መረጠ ።
1,1 የተከበርከው  የኢትዮጱያ ህዝብ በተለይ በቅርበት ያለህ የትግራይ ህዝብ አባይ ጸሀዬ በንዳዎች ፣ቂሞኞች ያላቸው ፤መጀመሪያ ባንዳ ፣ቂመኛ የሚባል መነው  ትርጉምስ ሊነግረን ይችላልን ? እኔ ግን አባይ ጸሀዬ ባንዳ የሚባል የሀገር ክህደት ፈጽሞ አገር ለባእድ አሳልፎ ዜጎች በባአዳን ያስጨፈጨፈ ፣አገር ያስደፈረ  ማን መሆኑ አበጥሮ ያውቃል ።የታሪኩ ባለቤት ስለሆነ ። ወይ ደግሞ  በጸረ የባእድ ወራሪ ጣልያን በመቃወም የኢትዮጱያ ጦር መርተው በሰለክለካ ፣ ማይቆልዑ ፣በእንዳባጉና ፣በዓዲዳዕሮ (ሰዬምት አድያቦ) ፣አፍጋሕጋሕ ከጣልያን ሰላቶ ተዋግተው አሸንፈው ከነፈረሱ የቀበሩ  የትግራይ መካንንቶች ጀግንነት ፣በወቅቱ ለኢትዮጱያውያን ሀርቦኞች ከድቶ ዜጎቹ ያስባላ ባንዳ ታሪክ ( ራእሲ እሙሩ ሀይለስላሴ  ;ተዘክሮ ሂወቴ )  የሚል ሰነድ በመጻፍ አሳትመው በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ደርድረው አስቀምጠውታል አባይ ጸሀየ ይሁን ሌሎች ተቆርቋሪ ወገኖች ሄዳችሁ ባንዳ ማነው የሚለው ትርጉም የራእሲ እምሩ መጽሀፍ አንብባቹሁ  ኢትዮጱያውያን ሆነው በዚያች ቀውጥ ጊዜ ወደ ጣልያን ከድተው  የኢትዮጱያ አርበኞች በተለይ ለትግራይ መካንንቶች ያስጨረሱ ባንዳዎች በመጽሀፉ ተዘርዝረው ይገኛሉ ።መሆኑም እወቁዋቸው ። እነአባይ ጸሀየና ሌሎች ባንዳነት  ዘር ወደሌላቸው ንጹሀን የሀገር  ሉኧሏውተነት ተቆርቋሪ ለሆኑ አይለጡፉባቸው ራሳቸው ውስጣቸው ይፈትሹ ! !
2 ኛ የጠባብነት አቀንቃኝ ስዩም  መስፍንም በዚሁ ፓኔል ሀቅ ይሁን ውሼት እየዘባረቀ ሲናገር በሂደት ግን በ1968 ዓ ም የነደፈው ትግራይ የመገንጠል ሀሳብ  የሚገልጽ ያሳተመው ፕሮግራም አገርሽቶበት ከያዘው አጀንዳ ወጥቶ  ትግራይ ገልለውናል የሚል አርስት ይዞ ሲተነትን ወደ 68 ዓ ም በመመለስ እኛ ማኸል አገር ካገለሉን የምንገነጠል ከሆነ ያች ኢትዮጱያ የምትባል ይዘናት እንገነጠላለን ብሎ አስረግጦ ሲናገር  የፓኔሉ ተሳታፊዎች በአባይ ጸሀዬ አቀራረብ  የነበራቸው ንዴት ሳይበርድ የስዩም የመገንጠል  ዘመቻ ብዙ የህዋሓት አባል ሳይቀር አግራሞት ፈጥሮሎታል ።እኔ እሚገርመኝ አቶ ስዩም መስፍን ከ1968 ዓ ም እስከ ከአዲስ አበባ መቐለ ፕላኔት ሆቴል  መጥቶ ኩማንድ ፖስት እሰኪመሰርት በዲዲፕሎማሲ አለም ነው የነበረው ።ይሰውዬ ስለአገር አቀፋውነት ፣ስለየመገነጣጠል አደጋ የያዘው የጨበጠው ነገር አልነበረም ማለት ነውን ? አሳፋሪ ነገር
3ኛ በዚሁ በእነ አባይ ጸሀዬ አና  ስዩም መስፍን ተጽእኖ የተገነጠለ ገና በወጣትነቱ ሳይ ጎብዝ ( ሳይጎረምስ )  ያረጀ  ወጣት ረዳት ፕሮፈሰር ነኝ ባይ የመቐለ  ዩንቨርሲቲ ሊክቸረር መረሳ  ጸሀዬ የተባለ አዲስ ገንጣይ የነ ስዩምመስፍ ሌጋሲ በመከተል እነዚህ ሰዎች ሰላም ከከለከሉን  እኛ  ከኢተዮጱያ ተገንጥለን ሀገራችን መስርተን እንኖራለን  ከአሁን በፊት ሀገር እያልን ከባድ መስዋእት የከፈልነው ይብቃን  ምን  ተጠቀምን በማለት  ለተሳታፊዎች ተሳታፊዎች  ጨለምተኛነት ፈጠረባቸው ። ከየት የመጣ ጥገኛ ገንጣይ ሰው ?  ይህ ሙሁር ተብየው በእውነት አገር ተረካቢ የሆኑ ዜጎች ሊያፈራ ተብሎ ነው የተቀመጠው ?በእኔ እምነት እንደዚህ አይነት ጭፍን አይናቸው የታወረ ጠባቦች ያመጡ እነ አባይ ጸሀየ ስዩም መስፍን ዶ/ደብረጽዮን ናቸው ተጠያቂዎች ።
የተከበራቹ የትግራይ ህዝቦች በዋናነት ለደኩተር ደብረጽዮን  አንድ ጥያቄ አለን ለመሆ እነ ስዩም መስፍን ፣አባይ ጸሀዬ ፣ስብሓት ነጋ ፣ጸጋይ በርሀ እዋ እነዚህ ሰዎች በየተኛው የስለልጣን መንገድ ነው በመላው ትግራይ እስከ ወረዳ እየዞሩ የጦርነ አዋጅ የመገንጠል አዋጅ ሲያሰሙ ከርመዋል።በባአሉ ድምዳሚ    ቀንም ተዋናዮች እነሱ ነበሩ ።በበኩሌ ስልጣናቸው እስከየት ይሄዳል ።ወይ አንተ ለስሙ ነው የተቀመጥከው ?ለነገሩ አንተም የእመገንጠል አስተሳሰብ እንዳለህ በእስቶዲዮሙ አውጀሀል ።
                  ይቀጥላል
                        መቐለ ፤
                   17 / 06  / 20 12
Filed in: Amharic