>

"የኢትዮጵያውያን ድል"  ከአድዋ  ጦርነት ፤ (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)

“የኢትዮጵያውያን ድል” 

አድዋ  ጦርነት 

ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ
            የአድዋ ጦርነት በየካቲት ፳፫ ቀን  ፲፰፻፹፰ ዓ.ም. በኢትዮጵያና ኢጣሊያ መካከል የተካሄደ ውጊያ ሲሆን ትልቁና   የመጀመሪያው የኢትዮጵያና የሮማው በትረ-መንግሥት(ጣሊያን)ጦርነት ክፍል ነውየውጤቱም ሐቅ በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት የጣልያን የቀኝ ግዛት ማስፋፋት ተኮላሸቷል
    አድዋ በትግሬ ክፍለ ሐገር የምትገኝ አንድ አውራጃ ናት፤አውራጃዋ በኢትዮጵያ ጠረፍ ላይ የምትገኝ የብዙ አገር ሰዎች የሚገበያዩባት ከተማ ቀመስ ቦታ ብትሆንም ጠላት ዐይኑን ያሳረፈባት መሆኑ ይታወቃል። ለዚህም ነው ጠላት በኤርትራ ጠረፍ በኩል አድርጎ በአሻጥር በተገዙ አገር ከዳተኞች እንዲገቡና እንዲወጡ መንገድ በማሳየት መረጃ በመስጠት ኢትዮጵያ እንድትወጋ ያደረጉት።ሌሎች የስውር ጠላቶችም ቅኝ ለማድረግ ሞክረው እንዳሰቡት ተንኮላቸው ስላልተሳካላቸው:- ሠራዊታቸውን ላለማጣት ወደኢትዮጵያ ወረራ ማድረጉን ሲተዉ፣የሮማዊው ሥረወ- የባላባት መንግሥት ግን ለዘመናት ብዙ አገሮችን በኃይል እንዳስገበረ በዓለም ስለሚታወቅ፣ የክርስቲያን ጭምብሉን በመንግሥትነቱ ላይ አድርጎ ኢትዮጵያ መጣ።
       በሕግ ተንኮል መጠቀሚያ በማድረግ ኢትዮጵያንም በሰበቦች ትዕቢትን አምጦ ኢትዮጵያን በእጅ አዙር በቅኝነት ገዥነት አስገብራለሁ ብሎ በጉልበቱ ለመግዛት ውስጣችን ካሉት ሰላዮቹና የወዳጅ ጠላቶች ጋር መረጃዎችን በማሰባሰብ በጦርነት ሊያስፈፅም ወሰነ።የታሪክ ጉዳይ ሆኖ ግን:-የጣሊያን ባላባታዊ መንግሥት እንዳሰበው”የጥቁር ሕዝብ ከዝንጀሮ የመጣ እንደሆነ”ለዘመናት ሲተረት የነበረውን ሀሳብ በመያዝና በመናቅ ፤በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ያለውን “የሰውን ልጅ ሁሉ በሃምሳሉ እንደፈጠረ” የሚታወቀውን በንቀት በሌሎች አገሮች ላይ ሲያደርገው የነበረውን የግፍ አመፅ ኢትዮጵያ ላይ ለመጀመር ቆርጦ ተነሳ።
     ምክንያት ግን አልነበረውም ነበርና የውጫሌውን የሠላም እና ወዳጅነት ስምምነት ሰበብ አደረገ፤የጠቡም ሰበብ በውጫሌው ስምምነት አንቀጽ ፲፯ ላይ የሰፈረው በጣሊያንኛ እና በአማርኛ የተጻፈው እንደ አገሮቹ ፍላጎት እንጂ አንድ ዓይነት ስምምነት ባለመሆኑ የተፈጠረ ተንኮል ቢሆንም ይህንን ችግር በሰላማዊ መንገድ ልናስተካክለው ይገባል ብለው እምዬ ምንሊክ ለጣሊያን መንግሥት ቢያቀርቡም ሮማውያን ግን “በኃይል እናስፈጽማለን!” ብለው ወሰኑ፤ለዚሁም ጉዳዩን በጦርነት ሊፈቱት ሁለቱም ቀን ቆረጡ የካቲት ፳፫። 
     የሮማውንጉሠ ነገሥት መንግሥት ትልቁ ያልተረዱት ነገር እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በልቡ ውስጥ እግዚአብሔር የሰው የተፈጥሮ እሳት መኖሩን ነው፤( https://www.youtube.com/watch?v=i5ePJjAXxIs ) ይህ ሥጦታ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው   የእያንዳንዱ ፀጋ ነው።ለዚህም ነው በትንንሽ ጦርነቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ተፈትኖም እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች የሮማው መንግሥት ያላቆመው፤የሚያሳዝነው ደግሞ ከሱዳን፣ከግብፅ፣ከትግሬ፣ከኤርትራ እና ከሌሎች የሮማውያን ቅኝ የተገዙ አገሮችን አሰባስቦ በመረጃነት ሥራላይ አዘመተ።
በዘመናዊ መሳሪያዎች እና የጦር ባለሙያዎች ታጅቦ፣የጣሊያን ገበሬዎችን ሳይቀር በግዴታ አሰልፎ  ሲጠቀምባቸውበኢትዮጵያ  በወቅቱ ንጉሠ ነገሥት የነበሩት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ነበሩ ትዕግሥት ጥበብ ዘዴ እና ቆራጥ የእናት ልብ የያዙት እምዬ ምንሊክ፣በኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ ያለውን የእያንዳንዱን ልብ ችቦ በወኔ አቀጣጥለው፣በአገር ፍቅር አጥምደው ዋጅ አስነግረው ነጋሪት አስጎስመው አድዋ ድረስ ለሁለት ወራት በመጓዝ ወዳጅም ሆነ ጠላት ባልጠበቀው መንገድ የቅዱስ ጊዮርጊስን ታቦት አስሸክመው የሮማውያንን የዘር ባላባት ሠራዊትን አድዋ ላይ ጦርነት ገጥመው በእግዚአብሔር ክንድ አዋርደው የካቲት ፳፫ (ማርች ፪)አድዋው ጦርነት “የኢትዮጵያን ድል”ለዘላለም ለማስጠበቅ የሮማውያን ቅኝ-ገዢዎችን ድል አደረጓቸው።  
        የሮማው ሥርወ-ባላባት መንግሥት ለዘመናት በጉልበቱ እየተመካ ብዙ መንግሥታትን ሲያሸንፍና ቅኝ ሲያደርግ የነበረው በዓለም መንግሥታት ፊት የተዋረደበት ምክንያት:- “የጥቁር አገር ሕዝብ አልሰለጠነም”እየተባለ በዓለም ላይ ግፍ ይሰራ እንደነበረ እና ይህም ጭቆና ፍፁም ከማይታመን በካቶሊክ ዕምነት በሚመራ መንግሥታት ውስጥ መሆኑ እጅግ አሳዛኝ መሆኑ ነበር።በውጭ መንግሥታት ውስጧ ብዙ የማትታወቀው አገራችን ኢትዮጵያ፣ለውጭ ዜጎች በሯ ጥንት የተዘጋ ሲሆን፣ጠንካራ ጦር ባላት የክርስቲያን አገር በሆነች በሮማውያን ካቶሊክ የመወረር ሚሥጥራዊ ምክንያት፣ከትዕቢት የመነጨ ክርስቶስን እንኳ የዳኘነው እኛ ነን ብሎ የሚመፃደቅ መንግሥት በመሆኑ እና፣”ጥቁር ሰው ዝንጀሮ እንጂ ሰው አይደለም”ብለው ከተሰለፉት መካከል፣ግንባር ቀደም ስለ ሆነ ነው።አሳፋሪው ደግሞ በክርስትና ሥም በዓለም ላይ ሠይጣናዊ ግፍ በትውልድ ላይ መፈፀሙ ሳያንስ የብዙ አገሮች በቅኝ መያዝ ዋናው መረጃ አቀባይ መሆናቸው ሲታወቅ፣ዛሬ ግን”በኢትዮጵያ”ያውም(በጥቁር ሕዝቦች) ተሸነፈ ሲባል ሠለጠኑ የተባሉት መንግሥታት ሁሉ አፋቸውን ሲይዙ የሮማው ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግን ውርደቱን ተከናንቦ በሰላም ሊኖር አልፈለገም፤ስለዚህም ራሱን ለመረረ የመሰሪ በቀል በግዴታ እምቢ ያለውንም ውል “ኢትዮጵያ በነፃነቷ የነበርችና አሁንም ያለች ሉአላዊ መንግሥት ያላት የክርስቲያን አገር መሆኗን አረጋግጣለሁ ብላ ፈርማለች።
         አሳዛኙና የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት የሆነውና በዓለም የተዋረደው የሮማውያን ሥረወ-መንግሥት የሆነው ኢትዮጵያ ላይ እንደዚህ ጠላት የሆነበት ምሥጢር የተዋሕዶ ኦርቶዶክስን በማጥፋት የካቶሊክ ዕምነትን ወደኢትዮጵያ ለማስገባት በሚደረግ የመጨረሻው ሰማያዊ ፍልሚያ ለመሆኑ በጥንቃቄ ማገናዘብ የሚቻል ነው።ምንም ዓይነት ዕምነት ይሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዕምነትን የሚያዳክም ሁሉ(ተራ ፖለቲከኛም ሆነ አክራሪ እስላም) ኢትዮጵያያን ለመበታተን ካቶሊኮች እንደሚ ያግዛቸው ስላመኑበት በማንኛውም መንገድ የመንግሥት ሥልጣንነትና የገንዘብ ያላሰለሰ ድጋፍ የበሮማውያኑ መንግሥት (ኢጣሊያ) በሚሥጥር ድጋፍ ይደረግላቸዋል።ዳሩ ግን ኃይሉ የእግዚአብሔር ነውና እኛ ግን በኢትዮጵያ አገራችን ለኢትዮጵያ   ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ዕምነታችን ዛሬም በኢትዮጵያ ነፃነት ውስጥ እንደ አድዋው ጦርነት “የኢትዮጵያን ድል”ለዘላለም ለማስጠበቅ እንታገላለን። 
 

ኢትዮጵያ በልጆቿ ፍቅርና አንድነት ለዘላለም ትኑር።

Filed in: Amharic