>

ራሳችሁን ተከላከሉ! ጃዋርና አብይን ተዋቸው! (ቅዱስ ማህሉ)

ራሳችሁን ተከላከሉ! ጃዋርና አብይን ተዋቸው!

 

ቅዱስ ማህሉ
አንዳንዶች በቅንነት ሌሎች ደግሞ በአድር ባይነት ከጃዋር ጀርባ ግብጽ ስላለች እንጅ አብይ ምንም አያውቅም ሲሉ እና ጥብቅና ሲቆሙ ይታያሉ። በግሌ ትናትም ሆነ ዛሬ ከጃዋር በላይ አብይ ለኢትዮጵያ አደገኛ ሰው እንደሆነ ይሰማኛል። አሁን የብዙዎች ዓይን ቢገለጥም እንኳ! የጃዋር ዓይነት ሰው ምኞቱን የነገረን ገና አገር ቤት ሳይመጣ በአልጀዚራ (ወይም አሜሪካ በተደረገ ስብሰባ ላይ) የተናገረ ቀን ነው። ክርስቲያኑን በሜንጫ ያለ ቀን ማለት ነው። አገር ቤት ገብቶም ባመቸው ጊዜ ሁሉ ያንን ምኞቱን ፈጽሟል።እየፈጸምም ነው። ጃዋር እንደዚያ ያደርግ ዘንድ እና በንጹሃን ደም ላይ ሲረማመድ በዝምታ ያለፈው ብቻ ሳይሆን የህዝብን ገንዘብ ደሞዝ እየከፈለ ሲያስጠብቀው የነበረው ግን አብይ ነበር። ይሄ የምታዩት የግብጽ ባንክ መሃል አዲስ አበባ የተከፈተውም በጃዋር ፈቃድ ሳይሆን በአብይ ፍቃድ ነው። ሌላው አሳዛኙ ነገር ይሄም እንደሌላው በኦሮሚያ ክልል እንደሚታየው ስርዓት አልበኝነት ግብጽ የጃዋር ወዳጅ ናት ተብሎ ካልታለፈ በቀር የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ውስጥ ባንክ መክፈት የሚያስችላቸው ህግ የለም። ህገ መንግስቱም ይከለክላል።
 ዘመኑ በግለሰቦች መልካም ፈቃድ ሃገር የሚሽከረከርበት ነው!
 
 በግለሰቦች መልካም ፈቃድ የሚመራ ሃገር ውስጥ ስርዓት አልበኝነት እና እልቂት እንጅ ብልጽግና አይኖርም። ኖሮም አያውቅም! ስለዚህ በቶሎ ዓይናችሁን ግለጡና እንደሚሆን እንደሚሆን ራሳችሁን ተከላከሉ! በተለይ በተለይ በየቀኑ ሬሳ እየቀበርን ከንፈር የምንመጥ ሰዎች እየተደረገ ያለው በተጠና መንገድ ስለሆነ ይቆማል መስሏችሁ አትዘናጉ! አንድ ባንድ ተለቅማችሁ እና ተያይዛችሁ ሳታልቁ ልክ እንደ ትናንቱ መክቱ! ጥንት ህግ በወረቀት ከመጻፉ በፊትም ሆነ በዛሬ ጊዜ ሁልጊዜም ቢሆን ራስን መከላከል ተፈጥሯዊ መብት ነው። የማንንም ፈቃድ አትጠይቁ! በየቀኑ አጠገባችን የሚካሄደው ግድያ ሊያነቃን ይገባል። #ጎንደር #ጎጃም #ወሎ #ሸዋ የማይቀር ነገር በምኞት ከመሆን አይቀርም! ስለዚህ ወንዶቻችሁ ተለቅመው ሳያልቁ ነቅታችሁ በመናበብ መታገል ጀምሩ! ምክንያቱም ብትነቁ እና ብትባንኑ ምንም የማታመጡበት እና ማምለጫም የማታገኙበት ቀን ከፊታችሁ አድፍጧል።የፖለቲካ ድል በጉልበት ብቻ ሳይሆን ክፍተት በመሙላት እና አጋጣሚዎችን ቀድሞ መጠቀም መቻል ላይ መህለቁን ይጥላል። እኛ እንኳን ለዚያ ልንደርስ ገና ራሳችንን መከላከልም አልጀመርንም!
Filed in: Amharic