>
5:13 pm - Wednesday April 20, 8501

የጠ/ሚ አቢይ አሕመድ ዐይን ያወጣ ውሸት!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

የጠ/ሚ አቢይ አሕመድ ዐይን ያወጣ ውሸት!!!

አቻምየለህ ታምሩ
“ስልጣን ስይዝ ሳምንት አልቆየሁም ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ሳስፈታው!”
 
 ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ከተፈቱ ከ26 ቀናት በኋላ ስልጣን የያዙት ዶ/ር አብይ አህመድ 
/መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ስልጣን የያዙበት ቀን/
“የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ.ም ብ/ጄኔራል አሳምነው ፅጌ የተፈቱበት ቀን!!!
“ትናንትና በአረብ ኢሚሬትስ ባደረገው ንግግር «ስልጣን ስይዝ ሳምንት አልቆየሁም ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ሳስፈታው» ብሎ በድፍረት ተናገረ።
ይህ የዐቢይ አሕመድ ዐይን ያወጣ ቅጥፈት ሰውዬው ለታዳሚው ያለውን ዝቅተኛ ክብርና ምንም ነገር ብነግራቸው ሳያረጋግጡ ያምኑኛል ብሎ እንደሚንቅ ብቻ ነው የሚያሳየው።
እስቲ «ስልጣን ስይዝ ሳምንት አልቆየሁም ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ሳስፈታው» ሲል ዐቢይ አሕመድ በዚያ ሁሉ ሕዝብ ፊት የቀጠፈውን ውሸት በሚመለከት እውነታው ምን እንደሚመስል በማስረጃ እንየው።
ጀነራል አሳምነው ፅጌ [ ከጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ኢንጂነር መንግሥቱ አበበ፣ ኮሎኔል አበረ አሰፋ፣ ኮሎኔል ሰለሞን አሻግሬ፣ ሻለቃ መኮንን ወርቁ፣ ሻለቃ መሰከረ ካሳ፣ ሻለቃ ምስጋናው ተሰማ፣ ኢኒስፔክተር አመራር ባያብል፣ ዋና ሳጅን ጎበና በላይና ሳጅን ይበልጣል ብራሃኑ ጋር] ከዝዋይ እስር ቤት የተፈታው የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ነው።
ልብ በሉ የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ዐቢይ አሕመድ እንኳን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆን የኢሕአዴግና የኦሕዴድ ሊቀመንበርም ገና አልሆነ።
የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢሕአዴን ሊቀመንበር የነበረው ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ነው።
እስከ መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ የኢሕአዴግ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ነው።
እነ ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ከተፈቱ ከ26 ቀናት በኋላ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ከመጋቢት 11 ቀን እስከ መጋቢት 18 ቀን 2010 ጉባኤ አድርጎ የኃይለ ማርያምን የሥልጣን መልቀቂያ ተቀብሎ ዐቢይ አሕመድን መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም ቀጣዩ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።
ይህ ማለት ዐቢይ አሕመድ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር የሆነው እነ ጄኔራል አሳምነው ከተፈቱ ከአንድ ወር ከአራት ቀን በኋላ ነው ማለት ነው።
መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም የኢሕአዴግ ቀጣዩ ሊቀመንበር ሆኖ የተመረጠው ዐቢይ አሕመድ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ፓርላማ ቀርቦ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ቃለ መሀላ ፈጸመ።
ይህ ማለት ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆነው ጀኔራል አሳምነው ጽጌ ከተፈታ ከአንድ ወር ከአስር ቀን በኋላ ነው ማለት ነው።
ጀኔራል አሳምነው ጽጌ ከተፈታ ከአንድ ወር ከአስር ቀን በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ የተሰየመው ዐቢይ አሕመድ ነው እንግዲህ በአረብ ኢሚሬትስ ባደረገው ንግግር «ስልጣን ስይዝ ሳምንት አልቆየሁም ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ሳስፈታው» ሲል በዚያ ሁሉ ሕዝብ ፊት ዐይን ያወጣ ውሸት የዋሸው።
እውነታው ግን ጄኔራል አሳምነው ጽጌ የተፈታው ዐቢይ አሕመድ አይደለም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆን ቀርቶ የኦሕዴድና የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ሆኖ ሳይመረጥ የአማራ ልጆች ባደረጉት ተጋድሎ ነው።”
Filed in: Amharic