>

" OMN የአንድ ቡድን የፖለቲካ ማሺን በመሆኑና በታሪክም በህግም ተጠያቂነት በማስከተሉ ከቦርድ አባልነት ለቅቄያለሁ!!!" (ጃፈር አሊ ሐሠን)

” OMN የአንድ ቡድን የፖለቲካ ማሺን በመሆኑና በታሪክም በህግም ተጠያቂነት በማስከተሉ ከቦርድ አባልነት ለቅቄያለሁ!!!”

ጃፈር አሊ ሐሠን
 
 
ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ቦርድ
ጃፈር አሊ ሐሠን: የቦርዱ አባል
ጉዳዩ :ከቦርድ አባልነት ስለመልቀቅ
ሁላችንም እንደምናውቀውና እንደምናምነው OMN በሕዝብ አስተዋፅኦ /መዋጮ የተቋቋመና የሚተዳደር ነፃ ሚዲያና በሀገር ውስጥ መራራ ትግል ሲካሔድ በነበረት አመታት የኦሮሞ ሕዝብ ድምፅ በመሆን ሲያገለግል የቆየ ሚዲያ ነበር።እኔም እንደ አንድ የኦሮሞ ሕዝብ ተቋርቋሪ ሆኜ ይህንን ሚዲያ ማጠናከር ትግሉን ማጠናከር ነው በሚል እምነት በተለያየ መልኩ የድርሻዬን አስተዋፅኦ ሳበረክት ቆይቻለሁ።
በዚሁ መሠረት እስከ ዛሬዋ ዕለት የOMN የቦርድ አባል የነበርኩ ቢሆንም ባለፈው ከአንድ አመት በላይ ለሆነ ጊዜ በአንድም የቦርድ ስብሰባ ላይ ከመገኘት ተቆጥቤ የቆየሁ መሆኔ ይታወቃል ።
ይህም የሆነበት ምክንያት:-
1ኛ:- የሚዲያው አመራር/ማናጅመንት ከቦርዱ ቁጥጥር ውጪ በመሆኑና በተለይም ሚዲያው ወደ ሀገር ውስጥ ከገባ ጊዜ ጀምሮ የፋይናንስ ወጪውና ገቢው ብቻ ሳይሆን የሚዲያው ባለቤትነት ወይም ባለንብረትነት(ownership ) ጉዳይ ቦርዱ ሊመልሳቸው የማይችላቸው አጠያያቂ ሁኔታ ስለተፈጠረ
2ኛ:- ሚዲያው ከየትኛውም ፓለቲካዊ ወገንተኝነት ነፃ በመሆን የሚዲያ ሙያና ሥነምግባር ደንብና ሕግ በሚፈቅደው መሠረት በሚዛናዊነት ሁሉንም ወገኖች በማስተናገድ የኦሮሞ ሕዝብ ድምፅ ከመሆን ይልቅ የአንድ ቡድን የፕሮፓጋንዳ ማሽን ወደመሆን እየተሸጋገረ ስለሆነ
3ኛ:- ይህ የማይገባ አካሔድ ውሎ አድሮ የታሪክ ተወቃሽነትንና በሕግ ተጠያቂነትን ማስከተሉ ስለማይቀር:
ከዛሬ ጃንዋሪ 11/2020 ጀምሮ በራሴ ውሳኔ ከOMN የቦርድ አባልነት መልቀቄን በማክበር አሳውቄያለሁ።
በመጨረሻም OMN ጉድለቶቹን አስተካክሎ የሕዝብ ድምፅ ሆኖ እንዲቀጥል ለቦርዱ አባላት መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላችሁ ምኞቴ ነው።
ማንኛውም ሰው ስለዚህ ጉዳይ እኩልና ግልፅ ግንዛቤ እንዲኖረውና ሌላ አካል አካል የኔን መልቀቅ የተለየ ትርጉም ሰጥቶ ለፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ እንዳያደርገው ለማድረግ ሲባል ብቻ ይህን የመልቀቂያ ደብዳቤ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለጥፌዋለሁ።
ጃፈር አሊ ሐሠን
11-01_2020
Filed in: Amharic