>

የደርጉ ስኬታማ ፕሮፓጋንዳ!!! "ደህንነቱ!" (ይስማዕከ ወርቁ)

የደርጉ ስኬታማ ፕሮፓጋንዳ!!! “ደህንነቱ!” 

 

ይስማዕከ ወርቁ

 
በደርጉ ወቅት ሶማሊያ ስትወረን መንግስቱ ኃይለማርያም የሶማሌውን ድርጊት ለማውገዝ እዚህ ቦታ {መስቀል አደባባይ} መጥተው ነበረ እንኳን ሶማሌያን አፍሪካንም መውረር እንችላለን ብለው ወታደራዊ ትርኢት ያሳዩበት ቦታ ነበር ወታደሩ ግን የያዘው ከእንጦጦ ተራራ የተቆረጠ ባህር ዛፍ እንደነበረ በመፃፍ ራሳቸው ጽፈውት አነበብኩት ወታደሩም የተሰጠው ስልጠና አጭርና ግልጽ ነው እሱም ከባህር ዛፍ የተሰራ ጠብመንጃ የእውነት ጠብመንጃ አስመስሎ መያዝ ወታደሩም የሆሊውድ አሰልጣኝ እንዳሰለጠነው አድርጎ ያዘው የአለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘገቡት ከዛም ለሶማሌያ ሥጋት ነገሰባት- ዚያድ ባሬ እድሉን ረገመ ኢትዮጵያን መተንኮሱ ኃይለኛ ውጋት ለቀቀበት መንግሥቱ ኃይለማርያም እዚህ በመስቀል አደባባይ የነዙት ፕሮፖጋንዳ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲዘግቡት እንኳን ሶማሌያን አፍሪካን መውረርም ይችላሉ ነበር ሰበካቸው ይህ ጫወታ ምርጥ የመንግሥቱ ኃይለማርያም ተውኔት መሆኑ አልታወቀም መንግሥቱ ኃይለማርያምን የምወደው አንዱ በዚህች ፕሮፖጋንዳው ነው ሆኖም ኢትዮጵያ በዛ ወቅት የነበራት ሃያ ሺህ የሰለጠነ ወታደር ነው ሶስት መቶ ደግሞ በደምብ ያልሰለጠነ ህዝባዊ ሰራዊት ነበራት ነገር ግን መንግሥቱ ኃይለማርያም ከግማሽ ሚሊዮን የበለጠ ሰራዊት አለን ብሎ አወራ እንኳን ሶማሊያን አፍሪካንም መውረር እንችላለን ብሎ መጀመሪያ ዚያድ ባሬን ፕሮፖጋንዳ ለቀቀበት ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች መንግሥቱን አምነው ዘገቡት ሆኖም ሶማሊያን ያሸነፍነውና ለሶስት የከፋፈልናቸው፣ ከሌሎች ወዳጅ ሀገራት ጦር ተልኮልን ነው ይህ ያለፈ ምስጢር ነው ይህ የትናንትናችን፣ ሀገራችን የዳነችበት ምስጢር ነው ይህ የአሸናፊነትታችን ምስጢር ነው እንደ ሎጥ ሚስት ዞር ብለን የምናዬው ክፉውን ነገር አይደለም ጥለነውን የመጣነውን ተንኮል አይደለም የምናየው አያቶቻችን በጦርነት ጊዜ የተሳሳቱትን ላለመድገም እንይዘዋለን አባቶቻችን ያሳኩትን ነገር፣ በቅርስነት እናስቀምጠዋለን አለበለዚያ በጦርነት ወቅት የሠሩትን ስህተት ዞር ብለን አናዬውም መቼም በጦርነት ወቅት ለመሳም አይዘጋጁም የጠላቶቻቸውን ጉንጭም አይስሙትም። (ደህንነቱ በይስማዕከ ወርቁ፤ ገጽ 116-117)
Filed in: Amharic