>

ለእስክንድ ነጋ እና ለባልደራስ እውነተኛ ዴሞክራሲ! (ቅዱስ ማህሉ)

ለእስክንድ ነጋ እና ለባልደራስ እውነተኛ ዴሞክራሲ!

 

ቅዱስ ማህሉ
* ….ይህ ፍርሃት እና የጀግንነት እንዲሁም የጀብደኝነት ጥያቄ ሳይሆን በዚያኛው ጎራ ያለውን ያደፈጠ ዘንዶ ቀድሞ አይቶ ውሳኔ ላይ የመድረስ ጉዳይ ነው።ውሳኔው ደግሞ ሲያደባ ከኖረ እና አጋጣሚውን ከሚጠብቅ ቡድን ጋር ያለውን የሃይል ሚዛን እንዲሁም በመሄድ የሚገኘውን ትርፍ በማመዛዘን  የሚገኝ ስሌት ነው!
 
እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ያለውን መዋቅር አጠናክሮ መስራት እና እሱ ላይ ትኩረት አድርጎ ቢንቀሳቀስ ይበልጥ ተመራጭ ነው። አሁን ላይ ደግሞ የግድ አስፈላጊም ጭምር ይመስለኛል። የጉዞ ፕሮግራሞችን ማራዘም አስፈላጊ ነው።  በአሁን ሰዓት እነ አብይ እና የኦሮሞ ብሄርተኞች እስክንድር ነጋ ላይ ጥቃት ለማድረስ ያላቸው ምቹ ቦታ አማራ ክልል ብቻ ነው።
ያን ከማድረግ ወደ ኋላ አይሉም። አማራ ክልል ውስጥ እየተካሄዱ ያሉት ግድያዎች በዋናነት ብአዴንን የሚጋልቡት ኦዴፓዎች እና ኢንፊልትሬት ያደረጉት ኢዜማዎች አጀንዳን ለማስፈጸም የሚካሄዱ ናቸው።
 እስክንድር ነጋ ደግሞ ለሁለቱም ወገን ጠላት ነው።  እንዲያውም በዚህ ሰዓት ከሱ በፊት ሌላ ቀዳሚ ጠላት የላቸውም። ጠ/ሚ ተብየው ለመጀመሪያ ጊዜ ስለባልደራስ ሲናገር “ባልደራስ ሚባል ጨዋታ የለም። ካሁን በኋላ አስረን ማንንም ጀግና አናደርግም።” ያለውን መርሳት እሱ እንዳለው ባለ”ሾርት ሚሞሪ” መሆን ነው። በተለይ ጎጃም እና ጎንደር  ከሰኔ 15ወዲህ ዋነኛ የግድያ ማዕከሎች ናቸው።
እርሱም ላይ ተሰንዝሮ የነበረውን የግድያ ሙከራ ይዘነጋዋል ብዬ አላስብም ። ሳይፈትሹ “እለፍ” ብለው ከፊት ላሉት ጥበቃዎች “ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች ጭኖ አምልጦ የመጣ መኪና አለ ይመታ! ” የሚል ትእዛዝ በማስተላለፋቸው በፈጣሪ እርዳታ ከሞት ማምለጡ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። እና ዛሬም በፋኖ እና በተለያየ የጥቃት ስም የብዙ ሰዎች ደም የፈሰሰባቸው እና ብዙዎች ነፍሳቸውን የገበሩበት ስፍራ ነው ማለት ነው። ይህ ደግሞ እስካሁን አልቆመም።
 እርግጠኛ ሆኘ መናገር የማልፈልገው ግን ከሁለት ወራት በፊት ለብዙዎች ያጋራሁት ስር የሰደደ ሌላም ነገር አለ።  ምናልባት እስክንድር መረጃው ይኑረው አይኑረው ባላውቅም በግሌ ግን ይህን የጻፍኩት ለማሳሰብ እና ለጥንቃቄ ያህል ነው። ይህ ፍርሃት እና የጀግንነት እንዲሁም የጀብደኝነት ጥያቄ ሳይሆን በዚያኛው ጎራ ያለውን ያደፈጠ ዘንዶ ቀድሞ አይቶ ውሳኔ ላይ የመድረስ ጉዳይ ነው።ውሳኔው ደግሞ ሲያደባ ከኖረ እና አጋጣሚውን ከሚጠብቅ ቡድን ጋር ያለውን የሃይል ሚዛን እንዲሁም በመሄድ የሚገኘውን ትርፍ በማመዛዘን  የሚገኝ ስሌት ነው። ስለዚህ ለአስቸኳይ እና ለወሳኝ ስራ ካልሆነ በቀር ይህ ጉዞ አያስፈልግም። የግድ ከሆነም ወኪል መላክ የተሻለ አማራጭ ይመስለኛል። ውሳኔው ግን የፓርቲው ነው።
Filed in: Amharic