>
5:13 pm - Saturday April 19, 4149

የዚህች ሃገር ችግር የሴራ ፓለቲካ ነው!!! (ታዬ ደንደዓ)

የዚህች ሃገር ችግር የሴራ ፓለቲካ ነው!!!

 

ታዬ ደንደዓ 

ጀዋር ሞሃመድ ዛሬ ለማየት የሚሰቀጥጥ አንድ ቪዲዮ ለጠፈ።
በጣም አንጀት የሚበላ ጥቁርም ሆነ ነጭ ኦሮሞም ሆነ አማራ፤የሰውን ልጅ እንደዛ በጭካኔ ማሰቃየት ከባድ የሰብዓዊነት ጥሰት ነው።የህግ ተጠያቂነት ደግሞ ግድ ነው❗
ግን ደግሞ ማነው ይህን ወንጀል የፈጸመው?
ዋናው ነገር ይህንን ወንጀል የፈጸመውን እና ያስፈጸመውን ለይቶ ለህግ ማቅረብ ነው።
ቪዲዮው ልጁ ግፍ ሲፈጸምበት እንጂ ግፍ የፈጸሙትን አያሳይም ለምን ወንጀለኞችን መደበቅ አስፈለገ? ታስቦበት ስለተፈጸመ ነው።
በሴራ ከመዘፈቅ ይልቅ ወንጀሉን የፈጸሙትን በማጋለጥ ለህግ የበላይነት መተባበር ነበር። ግን ያንን ትተው ግፍ የተፈጸመበትን በማሳየት ህዝብን ማበሳጨት ነበር የተፈለገ።
ወንጀሉን የፈጸመውን በመደበቅ አማራ ኦሮሞን አሰቃየ ማለት የፖለቲካ ሴራ ነው።
ነገሩ ድራማ መሆኑ በግልጽ ያሳያል። በሰው ጭንቅ እና ሰቆቃ ፖለቲካ ይሰራል።
የድራማው ባለቤት ደግሞ <<Jawar>> እራሱ ነው❗የዚህ ጉዳይ አላማ ግልጽ ነው።
1ኛው, አጀንዳ ማስቀየር ነው። የፖለቲካ ምረጡኝ <<ጉማ እና ዲቃላ>>ከሽፏል። “ጂርቱ እና ጂራ”የሚለው መፈክርም ተበላሽቷል። የጠባቂዎቼ መነሳት ፖለቲካም ውሃ አላነሳም። ስለዚህ አዲስ ኦሮሞን ስሜት የሚያነሳሳ አጀንዳ ማምጣት ያስፈለገው።
2ኛው. ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲ የምታደርገውን ጉዞ ማቆሸሽ ነው።ቡዙ አለም ሃገር መሪዎች አዲስአበባ ናቸው። ሁሉም ኢትዮጵያ ያለችበትን የሽግግር ጊዜ ትልቅ ቦታ ሰጥተውታል ይህ የኢትዮጵያን ተቀባይነት ያሳድጋል። ይህንንም ለማቆሸሽ ነው ይህን ዘግናኝ ነገር ማምጣት ያስፈለገው።
3ኛው. ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው።
ማሳያውም በቅርቡ የአማራ ክልል ተማሪዎች በደንቢዶሎ መታገት ተነገረ።
ኦሮሞ አማራን አገተ ሲባል ነበር። ዛሬ ደግሞ የአማራ ፖሊሶች ድሬዳዋ ላይ ኦሮሞን እያሰቃዩ ነው ብሎ ለጠፈ። ይህ ኦሮሞ እና አማራን የማባላት ከዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እርስበርስ ማገዳደል የቀጠለ አጀንዳ መሆኑ ነው። ኢትዮጵያ ለማፍረስ ነው ይህ ሁሉ።
ወያኔ የሃውዜንን ህዝብ በእቅድ አስጨርሶ የትግራይን እና የአለምን ድጋፍ አገኘ።ዛሬ ውጪ የሚኖሩ ኦሮሞችን ደጋፍ ለመሸመት የወያኔን ተሞክሮ ወሰደ።ይህ መንገድ ዛሬ አያዋጣም።ጀዋር በቀደም ተከበብኩ በማለት የ97 ንጹሃንን ህይወት አጥፍቷል።ይህ የኖቤሉን ድል በደም ለመቀባት የተደረገ ነበር። ዛሬ ደግሞ አጀንዳ ለማስቀየር እና ህዝብን ለማባላት ቪዲዮ በማዘጋጀት ለቀቀ። መንግስት በጣም ነው የታገሰው። ከዚህ በላይ በህዝብ ደም እና ስቃይ መነገድ መቆም አለበት።ተጠያቂነትም ይመጣል።እንደ ትናንቱ በንጹሃን ደም እና ስቃይ በመጫወት GoFunDMe መክፈት የለም።ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል። ምርመራም ተጀምሯል።
ሰባአዊ መብት❗የህግ የበላይነት!
Filed in: Amharic