>
5:13 pm - Wednesday April 19, 2271

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅን ሲታወስ!!! (ተስፋዬ ሀይለማርያም)

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅን ሲታወስ!!!

 

ተስፋዬ ሀይለማርያም
* ፕሬዝዳንትና ንጉስ ለክብሩ ከመቀመጫቸው የተንሱለት የኢትዮጵያ እንቁ ልጅ ሎሬት ፀጋዬ 
 
ጋሽ ፀጋዬ የሞተው በዚህ ወር ውስጥ ነበር። ፀግሽ ዛሬ በህይወት አለመኖሩ ለሱ በጀው። ምክንያቱም ዘመዶቹ እሱ የሚወዳትን አገሩን ለማፍረስ የሚያደርጉትን ሁሉ እያየ በሽተኛ ይሆን ነበር።
ስለ ፀጋዬ ሳስብ ሁሌ የሚገርመኝን ነገር ማንሳት ወደድኩ ። ፀጋዬ የድሮው የሴኔጋል ፕረዚዳንት የሴዳር ሴንጎር ጓደኛ ነበር። ሁለቱም አብረው ተምረዋል።
አንድ ለቤተመንግሥት ቅርብ የሆኑና አሁን በህይወት የሌሉ ሰው አንድ ታሪክ አጫወቱኝ።
ጃንሆይ በንግሥና ዘመናቸው ለማንም ሰው ከመቀመጫቸው ተነስተው አያውቁም። አንድ ቀን ግን ሳይወዱ በግዳቸው ተነሱ። ጉዳዩ እንዲህ ነው፣
ፕሬዚዳንት ሴንጎር ወደ ኢትዮጵያ መጣ። ጃንሆይም ለሴዳር ሴንጎር በቤተመንግሥት ግብዣ አደረጉ። ሴንጎር በግብዣው ላይ ተቀምጦ ሳለ አዳራሹን በዓይኑ ሲቃኝ ወዳጁን ፀጋዬን አጣውና  ወደ ጃንሆይ ጠጋ ብሎ Where is Tsegaye? ብሎ ጠየቃቸው።
ፀጋዬ በግብዣው ላይ አልተጠራም። ስለዚህ ለሴንጎር ክብር ሲባል ካለበት ተፈልጎ በአስቸኳይ እንዲመጣ መኪና ተላከለት።
ፀጋዬ ቤተመንግሥት ሲደርስ ሴዳር ሴንጎር በደስታ ከመቀመጫው ተነስቶ ተቀበለው። በዚህ ጊዜ ጃንሆይም የክብር እንግዳቸው ቆሞ እሳቸው መቀመጥ ስለሌለባቸው ሳይወዱ በግዳቸው ከመቀመጫቸው ተነሱ። ፀግሽ ነብይ በአገሩ ባይከበርም እኔ ግን ለክብርህ ከመቀመጫዬ ተነስቻለሁ።
Filed in: Amharic