>
5:13 pm - Monday April 18, 2478

ጆሲ ሚዲያን “ፈይሣ አዱኛ” ይይልህ! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

ጆሲ ሚዲያን “ፈይሣ አዱኛ” ይይልህ!

 

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

 

ደግሞ ሌላ ነገር እንዳይመስልብኝ፡፡ ባይሆን ሁለተኛ ሰው እንኳን ልሁን ብዬ ነው፡፡ የማይሰማ ነገር የለም፡፡ “የቆዬ ሰው ከሚስቱ ይወልዳል” የሚባለው ትክክል ነው፡፡ እነዚህ ጅሎች ብለው ብለው የታቦታቱን ስም ሁሉ ወደ አፋን ኦሮሞ ለመተርጎም ትልቅ ፕሮጀክት ነድፈው እየተንቀሳቀሱ ነው አሉ፡፡ ምሽቱን ስስቅ ነው ያመሸሁት፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ራቴን እየበላሁ የዮሴፍ ይጥናን ዩቲዩብ እከታተል ያዝኩ፡፡ ከዚያም በሚኒሶታ ያለው አንድ ቅሌታም ጳጳስ ይሠራው ያለውን ነገር ሰማሁ – ጳጳስ ቅሌታም የማይባል ከሆነ ይቅርታ፡፡ አቶ በላይ መኮንን ማለቴ ኦቦ “ቀሲስ” በላይ መኮንን ታቦት ሰርቆ ከሀገር እንደወጣ ሰምቼ ስለነበር ያ ሤራ ምን እንደነበር ዮሴፍ ምንጮቹን እየጠቀሰ ያብራራ ጀመር፡፡ ከዚያም ”መድኃኔ ዓለም” የሚለውን ስም “ፈይሣ አዱኛ” ብለው መተርጎማቸውንና የኦሮሞ ቤተ ክርስቲያን በማቋቋም ላይ መሆናቸውን በጠቀስኩት የዩቲዩብ የዜናና ሀተታ አውታር አደመጥኩ፡፡ ደነቀኝ፡፡ ገረመኝ፡፡ የጅልነታቸው ለከት ማጣት እጅግ አስደመመኝ፡፡ በዓለም በጅልነት ቢወዳደሩ አጠገባቸው የሚደርስ እንደማይኖር ተረዳሁ፡፡ ከ1ኛ እስከ መቶኛ እነሱው ይሆናሉ – በጅልነት፡፡ ሌላ ጅል ቢኖር ከ101ኛ ጀምሮ ቢቀጥል ነው፡፡ ከነማን ጋር ነበር ያን ሁሉ ምዕተ ዓመት የምንኖረው ግን? ተረኝነት ይህን ያህል ያጀዝባል እንዴ? እስከዚህ ያሳብዳል ወገኖቼ? እነዚያኞቹ አሁን እንዲህ ሊያፍሩና ሰማይ ምድር ሊደፋባቸው “እንኳንስ ከአሜሪካ ከመንግሥተ ሰማይም እናስመጣሃለን!”፣ “ጦርነትን መዋጋት ብቻ ሣይሆን ጦርነት ራሱን ጠፍጥፈን መሥራትም እንችላለን!” እስከማለት ደርሰው ጉራቸው ሰማየ ሰማያትን አለፈ – እግዜሩም ሰማ፡፡ የነዚህ ደግሞ ባሰና ከማስገረምም አልፎ በሣቅ ይገድሉን ያዙ – እግዜሩም ሰምቶ እንደኛው በሣቅ እየተንፈቀፈቀ ነው፡፡ ኧረ የመካሪ ያለህ እንበል! በሀፍረት አሸማቀው ሊገድሉን እኮ ነው ምንድን ነው ዝምታው! አንዳች መፍትሔ ፈልጉ እንጂ!

“ፈይሣ አዱኛ” ያጥፋኝ ነው የምላችሁ እነዚህ ጅሎች በዚህች አገር አምስት ዓመት ሥልጣን ላይ ቢቆዩ የአማራና የሌሎቹን ተውትና የትግራይን ስም ራሱ “ኦሮምታገሮ” ወደሚል መለወጣቸው አይቀርም – እነሱን እንኳን ይበሏቸው – ወደሽ ከተደፋሽ ነው ነገሩ፡፡ የለገሣ ዜና ቦምብ እና የኢሱ አፎርቂ ፈንጅ አይደል አሁን እዚህና እዚያ እንደብጉንጅ እየፈነዳዳ ሀገራችንን መቀመቅ እየከተታት ያለው? ጅራፍ አጩኾ ድምጹን የማይሰማ ካለ ደንቆሮ ብቻ ነው፤ ስለዚህ ባጠመዱት ወጥመድ መግባት ያለ ነውና ሁሉም የሥራውን ማግኘቱ አይቀርም፡፡ ለሰው የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ስትሰጥ ላንተ ቢያንስ የመቶ ሃምሣ ዓመት የቤት ሥራ እንደማይታጣልህ እርግጠኛ መሆን አለብህ፡፡ ምክንያቱም በሠፈሩት ቁና መሠፈር አለና፡፡ ፈጣሪ “በቀልን ለኔ ተዋት!” ያለው ለምን መሰለህ? ስለስም ከተነሳ አይቀር የኔንም ለውጠው “ለመፋ ጉዲቱ ካሢቾዳ” ሳይሉኝ አይቀሩም፡፡ እንዴ! ምን ጉዶች ናቸው በል?

ይልቁንስ የልጅነት ጨዋታ አስታወሱኝ፡፡ በልጅነቴ በኔ የጓደኞች ክበብ በትርጉም እኔን “የሚስተካከል” አልነበረም፡፡ጓደኞቼ መዝናናት ሲያምራቸው “በአማርኛ እንዲህ የሚባለው በእንግሊዝኛ እንዴት ይባላል?” ይሉኝና ስነግራቸው ይስቃሉ፡፡ ሲስቁልኝ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ አሁን በነዚህ ጅሎች ስንስቅ ደስ ይበላቸው አይበላቸው አላውቅም፡፡

“Plant religion ድፍት ያርጉህ!” ማለት ተክለ ሃይማኖት ድፍት ያርጉህ ማለት ነበር – ያኔ፡፡ ከበደ ሞላ – Heavy Full፤ በቀለ ማሞ – Germinated Baby፤ ይሄ መሸጦ ባሪያ አለፈለት – This sold slave has passed him (መንግሥተ ኃይለ ማርያምን እኮ ነው!)፤  ከመሬት ተነስቶ ነገር ይፈልገኛል- He finds me a thing standing from the ground፤ እመ ብርሃን ታውቃለች – Mother of light knows…፤ አይሄድ አይመጣ ቁርጥ አባቱን! – He doesn’t go; he doesn’t come; he cuts his father…፤ … እንዲህ እንዲህ እያልን፣ እያስባልንና እየተባባልን በቀልድ እንዝናና ነበር፡፡ አሁን ግን የምር አደረጉትና በሣቅ ሊፈጁን ፈለጉ፡፡ እነዚህ ቀን ሰጠን ያሉ የበሉበትን ወጪት ሰባሪ ነፈዞች ቋንቋም ቁም ነገር መስሏቸው ሲጃጃሉ ሳይ አንጎላቸው ከነጭ ጭቃ የተፈጠረ ስለመሆኑ በትክክል ገባኝ፡፡ ትልቅ መረገም ነው፡፡ ብዙ ያውቃሉ የሚባሉት የሃይማኖት አባቶች እንዲህ ካደረጉ ልጆቻቸው እነ ለማ መገርሣና ሽመልስ አብዲሣ ከታከለ ኡማና አቢይ አመድ ጋር በመመሳጠር የፌዴራል ተብዬውንና የአዲስ አበባን መሥሪያ ቤቶች በተለይም የሥልጣንና የኃላፊነት ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ እጅግ በአብዛኛው የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች በሆኑና ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ተልእኮ በተሰጣቸው በነወርዶፋና ጫላ ማስያዛቸው አይፈረድባቸውም፡፡ ከትራፊክ ፖሊስ አቅም ራሱ ሌላ የምታገኘው ከስንት አንድ ነው – ይበልጡን ጉርሙና አያንቱ ናቸው፡፡ በቋንቋም እኮ መግባባት እያቃተን ነው፡፡ከጥቂት ጊዜ በኋላ አስተርጓሚ ሳያስፈልገን አይቀርም፡፡ እነዚህ ሰዎች በእልህ ስለተነሱ ባንኩንም፣ ጅምሩክንም፣ ምኑንም ምኑንም አፍ በሌላቸው የገጠር ኦሮሞዎች እያስያዙ ሥራውን መበደል ብቻ ሣይሆን ባቢሎንን በኢትዮጵያ እየገነቡ ናቸው፡፡ የኮሮናን በሽታ ለማከም ቻይና በስድስት ቀናት ውስጥ ግዙፍ ሆስፒታል ትገነባለች እነዚህ ይሉኝታቢሶች ደግሞ በሁለት ዓመታት ውስጥ በተረኝነት ሕወሓታዊ የዘር ልምሻ ተለክፈው በኬኛ ፖለቲካ ሁሉንም ነገር ካለደረሰኝ ለራሳቸው ገቢ ያደርጋሉ፡፡ አፋርን፣ ሶማሌን፣ ደቡብንና ሌሎች ቤረቤረሰቦችንማ ከነመፈጠራቸውም ረስተዋቸዋል፡፡ ወገኔ – ትንሽ ሰው አያግኝ፤ትንሽ ሰው አያሸንፍህ፣ ትንሽ ሰው ራሱ አንሶ ሌላውን ያሳንሳልና አያጋጥምህ፡፡ በየመዝናኛው በወረምኛ ሲደነፉ ስታይ በነዚያኞቹ ቦታ ከምንጊዜው ተተኩ ብለህ ትገረማለህ፡፡ እውነቴን ነው – ትንሽ ሰው በፍጹም ጥጋብ አይችልም፡፡ እነዚያም ጥጋብ ባለመቻላቸው የሚሠሩትን አጡና የላይኛው ተቆጣቸው -ለዚያውም “ፈይሣ አዱኛ” የሚውልበትን ዕለት 27 ዓመታትን ያህል ታግሶ፡፡ ተቆጣናም ሳያስቡት ድባቅ መታቸው፡፡ እነዚህኞቹም ማዕዱ ከመቅረቡ ጠገቡና ገና ከአሁኑ ቁንጣኑ ሊገድላቸው ነው፡፡ ሰው የገዛ ሞቱን በገዛ እጁ ያፋጥናል? 

አሁን ለመጻፍ ምንም ፍላጎት አልነበረኝም፡፡ ከሞነጫጨርኩ አይቀር ጥቂት ነገር ላክልና ልተኛበት፡

እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ኦሮሞዎች እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ትግሬና አማራ ሁሉ በነዚህ ገልቱዎች እንዳትጨነቁ፡፡ ችግሩ ያለው ከተራው ዜጋ ሳይሆን ልሂቅ ተብዬው ጋ ነው፡፡ ተራውማ ዓለም ብታልፍ አብሮነቱን አይጠላም፤ ተጣላ ስላሉትም አይጣላም –  መሠሪዎች ከሚጭሯቸው የተወሰኑ መጥፎ አጋጣሚዎች በስተቀር፡፡ የአማራ ገልቱ እንዳለ ሁሉ የትግሬም ገልቱ አለ፡፡ የጉራጌ ሃቱ እንዳለ ሁሉ የኦሮሞም ሃቱ አለ፡፡ ሃቱነት ወይም ገልቱነት የጎሣና የብሄር ኮታ የለውም፡፡ ዋናው ነገር አመራሩን የያዘው ነው፡፡ ጫፉን የያዘው ገልቱ ከሆነ ነገሮች ይበላሻሉ፡፡ ምክንያቱም በሀገራችን የእስካሁኑ ተጨባጭ ሁኔታ የሥረኛው የላይኛውን ከመከተል ያለፈ ብዙም አቅም ያለው አይመስልም፡፡ ስለዚህ ወዳጆቼ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣና ጄኔራል መርዳሣ ሌሊሣ በነዚህ ዐይጠ መጎጦች ከማንም በበለጠ ቅር እንዳትሰኙ አደራ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ሁሉም ሊሆን የግድ ነው፡፡ እኛም ልንማር የግድ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሰፊ ሕዝብም እርጥቡን ከደረቁ ሊለይ የግድ ነው፡፡ የኛው ክፍያው በዝቶ አንገሸገሸን እንጂ ትምህርት ሁሉ ካለ ምንም መስዋዕትነት በነፃ እንዲገኝ አይጠበቅም፡፡ በአንድ በኩልም በታላቅ መስዋዕትነት የሚገኙ ትምህርቶችም አሉና የኛም ከነዚህ አንዱ እንደሆነ እንቁጠረው – ከነዚህም ሆነ ከነዚያኞቹ ግን እንማርና መጪውን ዘመን እናስተካክል – ቢያንስ ለልጆቻችን ስንል፡፡ ባይሆን መጪውን መስዋዕትነት ቀለል እንዲያደርግልን መጸለይ እንጂ በምናየው የቂልነት ተግባር ሁሉ ብዙም መሣቅ አይገባንም ታዲያ – ካስቻለን ሣቃችንን ቆጥበን ወደ ምህላው እንግባ፡፡ የጅል በትር አስቀያሚ መሆኑን ከጃዋራውያን ሜንጫ በከባድ ወጪ እየተማርን ነውና ይህን የሰይጣን ቁራጭ ከነጌታው እንዲገላግለን ፈጣሪን በየእምነታችን አጥብቀን እንለምን፡፡ “ፈይሣ አዱኛ” በያለንበት ይጠብቀን፡፡ ቻው፡፡ (ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት፡፡)

Filed in: Amharic