>

ይህች አዲስ አበባ ነች! የአዲስ አበቤ የላቡ ውጤት!!! (አዲስ አበባ - ባልደራስ)

ይህች አዲስ አበባ ነች! የአዲስ አበቤ የላቡ ውጤት!!!

 

አዲስ አበባ – ባልደራስ
 
 ሽሮ ሜዳ ብትሄድ ዶርዜኛ እየሰማክ ቆንጆ የሀገር ልብስ ገዝተክ ትመጣለክ ተክለሀይማኖት ጎራ ብትል ሱማሊኛ እየሰማህ መኪና አስጠግነህ መለዋወጫ ገዝተህ ትመለሳለህ  ፣ ኮተቤ ወይም ካራ ብትሄድ “አካም፣ ነጉማ “ብለህ ተሳስቀክ ለድግስህ ስጋ ገዝተህ ትመለሳለህ ። መርካቶ ያቺ ከወልቂጤ የመጣች ሴትዮ “ወይኀም ዋሬ” ብላህ ቅቤ፣ ሚጥሚጣ፣ ቅመማ ቅመም ትሸጥለሀለች። ጎጃም በረንዳ ብትሄድ ጌታው እንደምን አደሩ ተብለህ ማርና ቅቤ ገዝተህ ትመጣለህ።
አዲሱ ሚካኤል “ኦርያ” እያለችህ ሀሊማ ከጅግጅጋ የመጣ ሰአት ትሸጥልሀለች።ቀጨኔ ብትሄድ ከሚገርም ትህትና ጋር ” እንደምን አደርክ” ተብለክ ሰው ለማደግ በሸማ ስራ ሲጠበብ ታየዋለህ ፣ ፒያሳ ብትሄድ ትግርኛ እያደመጥክ ወርቅ ሸምተህ ትመለሳለህ።ይሄ አዲስ አበባ ነው፤ የክልል ከተማ አይደለም። ብሄር የምትለው አጀንዳ ጉዳዩ አይደለም። ደሀው ኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ላይ የታተመች ሀገሩን እራሱን ለማሳደግ የሚለፋባት የፍቅር ከተማ ናት ።
እዚህ አንድ ሰፈር ከአንድ ሰፈር የወሰን ግጭት የለውም። እዚህ ሰፈር አየኖረ አዛ ሰፈር እየነገደ ከእዛኛው ሰፈር ፍቅረኛ እየፈለገ የሚኖርባት ከተማ ናት ።ይሄ አዲስ አበባ ነው አንድ ሰፈር ከሌላኛው ሰፈር በተሻለ ልዩ ጥቅም ላግኝ ብሎ የሚፎክርባት አይደለችም ባይሆን አንዱ አካባቢ ሌላውን እያገዘና እየተረዳዳ የሚኖርባት ከተማ ናት። እዚህ ልዩ ጥቅም የምታገኘው ወጣ ባለ ሀሳብ ስትነግድ ወይም ብዙ ሰአት ስትሰራ ነው።
አዲስ አበባ ብዙ ቋንቋ የሚነግርባት የብሄር አጀንዳ ይዘህ  ብትቀርብ ማንም የማያስተናግድህ   መንደርተኛ ተብለህ የምትተችበት ብሄር ሳይሆን ሰውና ሰው መሆንህና ስራ ብቻ የሚወደድባትና የሚያስከብርባት ከተማ ናት።የአንዋር መሰጊድ ጎረቤት ራጉኤል ” ቅዱስ አምላክ ቅዱስ እግዚአብሄር ብሎ ይቀድሳል” አንዋር ደግሞ ” አላህ ዋክበር ፣ፈጣሪ ታላቅ ነው ይላል ” ።
የተለያየ ባህል ፣የተለያየ እምነት ይሰበካል፤ ሰው ለዚህ ግድ የለውም አብሮ ይበላል አብሮ ይጠጣል።ይሄ አዲስ አበባ ነው። ከየትኛውም የሀገሪቱ አቅጣጫ ብትመጣ እንግድነት ስሜት አይሰማህም ። ቢቻልህ ይሄን የአዲስ አበባ ቀለም፣ መንፈስ በሁሉም የሀገሪቷ ከተሞች አስፍሮ ዘላቂ ሰላም መፍጠር፣ መገንባት ስትችል ስራ አምላኪዋን አዲስ አበባን በብሄር አጀንዳ ለማተራመስ መሮጡ ምን ትርፍ ያስገኝልሀል ?
ብትችል ከእኛ ቋንቋ ውጪ ላሳር ያሉትን ጠባብተኞችንና መንደርተኞችን ኑ እና ከአዲስ አበባ ተማሩ በላቸው !!!
አዲስ አበባን የምንወዳት “ኑ ተባብረን እንደግ፣ የአቅማችሁን፣ የእውቀታችሁን ስጡኝ” ስለምትል ነው ።ይሄን ሀቅ በብሄር ትግል ለናወዙት ከነሱ ቋንቋ ተናጋሪ ውጭ ሰው የሌለለ ስለሚመስላቸው ሰዎች አስረዷቸው ። “ከወለጋ የመጣው የዘርን ፓለቲካ የሚያራግበው የአንድ ፓርቲ ተወካይ ፊንፊኔ ኬኛ ይለናል። ከአርሲ አርባጉጉ የመጣው  አክቲቪስት ነኝ ባይ ፊንፊኔ ኦሮሞን ኬኛ ይለናል”
እባካችሁ አንዱ አላማችሁ ሲኮላሽ ወደ ሌላ አጀንዳ እየሄዳችሁ ሕዝብን ከሕዝብ ማላተሙን ተዉት። ከላይ እንደገለጽኩት አዲስ አበባ የሁላችንም ናት!!!!
አዱ ገነት የፍቅር ከተማን ኑና እዩ በሏቸው !!! 
አዲስ አበባ እና ሰማይ የኔ ነው አይባልም!!!
Filed in: Amharic