>

የተማሪዎቹን እገታ በተመለከተ እስካሁን በሚዲያ እየተሰጡ ያሉ አደናጋሪ መረጃዎች እና የባለሥልጣናት ምላሾች - በጥቂት ( በፍቃዱ ዘ ሀይሉ)

የተማሪዎቹን እገታ በተመለከተ እስካሁን በሚዲያ እየተሰጡ ያሉ አደናጋሪ መረጃዎች እና የባለሥልጣናት ምላሾች (በጥቂት)

በፍቃዱ ዘ ሀይሉ
1) ታኅሣሥ 7/2012 ከእገታ ያመለጠችው ልጅ (አስምራ ሹሜ) “ሲያፍኑን ሰባት ነበርን” ብላለች። አግተናቸዋል ያለ ሰውዬ በኦሮምኛ የተናገረው ትርጉም “የታገቱት በቄሮ ነው። 18 ናቸው። 14 ቀናቸው ነው ከታገቱ። በመልካም ሁኔታ ውስጥ ናቸው” ብሏል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሕዝብ ግንኙነት ደቻሳ ጉሩሙ “መረጃ የለኝም” ብለዋል። ተመስገን ዓለሙ የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ሕዝብ ግንኙነት “እንደናንተ በወሬ ደረጃ ሰምተናል” አሉ።  https://m.youtube.com/watch?v=jcF5aZDsqBA&feature=youtu.be
2) ‘ቲክቫሕ’ ልጆቹ የታገቱት ሕዳር 20/21 ቀን ሲሆን አስምራ መታገታቸውን የተናገረችው በሕዳር 24 መሆኑን ጽፏል። (ከላይኛው ኢንተርቪው የተገመተ ነው።)
3) ታህሳስ 27 የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ተመስገን ጥሩነህ በጋዜጣዊ መግለጫቸው “ከአባገዳዎች ጋር በመነጋገር የተለቀቁ አሉ። እስካሁን ያልተለቀቁ ደግሞ እኔ ባለኝ መረጃ 4 ተማሪዎች አሉ። ከቤተሰቦቻቸው ጋር አልፎ አልፎ ይደዋወላሉ” ብለዋል። https://m.youtube.com/watch?feature=share&v=aGiyu9qx-WU
4)  ጥር 2 አስምራ ሹሜ ለቢቢሲ “መጀመሪያ በአጋቾቹ የተያዝነው 18 ተማሪዎች ነበርን። እኔ ማምለጥ ስለቻልኩ አሁን ታግተው ያሉት ተማሪዎች ቁጥር 17 ነው።” ብላለች።  https://www.bbc.com/amharic/news-51066440?at_custom4=C721F51E-3451-11EA-B983-AAF6FCA12A29&at_campaign=64&at_medium=custom7&at_custom2=facebook_page&at_custom1=%5Bpost+type%5D&at_custom3=BBC+News+Amharic
5) ጥር 2 የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬተርያት ኃላፊ ንጉሡ ጥላሁን ለኢቲቪ “ታግተው ከነበሩት ውስጥ 13 ሴቶችና 8 ወንዶች በድምሩ 21 ተማሪዎች ተለቀዋል፣ 5 ተማሪዎችና 1 የአካባቢው ተማሪ ወጣት ለማስለቀቅ ድርድር እየተደረገ ነው (…) በየጊዜው መረጃ እንሰጣለን።” ብለዋል።  https://youtu.be/B0QCPUFgXlQ
6) ጥር 7 የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዴሬሳ ተረፈ “ታፍኖ የተወሰደ ተማሪ የለም” ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ  “አላውቅም፤ እኔ የሰማሁት ነገር የለም” ብለዋል። ቢቢሲ ከቤተሰቦቻቸው አገኘሁ ብሎ የ17 ተማሪዎችን ሥም ዘርዝሯል። https://www.bbc.com/amharic/51116492?SThisFB
7) ጥር 8 የኦሮሚያ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ጌታቸው ባልቻ ለዶቸ ቨሌ የተለቀቁት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ ተመልሰዋል። ከወላጆቻቸው ጋር ያልተገናኙት በአገካቢው የስልክ ግንኙነት ባለመኖሩ ነው ብለዋል። https://p.dw.com/p/3WMkc
8) ጥር 8፣ የፌዴራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ኃላፊ ጄይላን አብዲ ለአሥራት ቲቪ “መግለጫ የሰጠው አካል ነው የሚያቀው፣ እኛ አናቅም። እኛ የአንዲት ሴት ጉዳይ ብቻ ነው የምናቀው” ብለዋል። https://www.facebook.com/abebaw.ambaye.5/videos/2671337206486087/
9) ጥር 15 ለአሥራት ቲቪ ጀይላን አብዲ ያለንን መረጃ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስገብተናል። “የከፋ ነገር ሊኖረው ይችላል” ብለዋል። https://m.youtube.com/watch?v=9-ssbsEh5RU&feature=youtu.be
10) ጥር 18 የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኀላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ ለቪኦ ቀሩ የተባሉት 6 ታግተው ይሁን ተደብቀው እያጣራን ነው፤ ጠፍተዋል ነው የምንለው ብለዋል። https://www.facebook.com/voaamharic/videos/3409270655754971/
11) ጥር 19 በደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ በሰላም ምንስቴር በተመራ ቡድን በተሰጠ መግለጫ ላይ 17ቱን ከ21ዱ የተለዩ እንደሆነ ተወርቷል። ንጉሡ “በቀውስ ጊዜ የመረጃ ስህተት ይፈጠራል” ብለዋል። የዩንቨርስቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙለታ ተስፋዬ ሥማቸው ከተዘረዘሩት 17 ተማሪዎች ውስጥ 14ቱ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መሆናቸውን፣ ከነዚህም 2 ተማሪዎች በግቢው ውስጥ መኖራቸውን (ካፌ በመመገባቸው)፣ 2 ተማሪዎች ደቡብ ጎንደር እና ጎጃም ቤተሰቦቻቸው ጋር መመለሳቸውን (በስልክ አነጋግሬ) አረጋግጫለሁ ብለዋል። 10 ተማሪዎች በፍለጋ ላይ መሆናቸውን፣ የተቀሩት 3 ሥማቸው እየተጠቀሱ ያሉት ተማሪዎች ግን የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አለመሆናቸውን ተናግረዋል ብሏል ኢቲቪ፡፡ ኔትዎርክ አለመኖሩ ፍለጋውን አስቸጋሪ አድርጎታል። https://youtu.be/2JHcRtq_JFg
BringBackOurStudents
Filed in: Amharic