>
5:13 pm - Wednesday April 19, 6879

አሁን መጠየቅ ያለበት ጥያቄ  «ምን አለን»?  የሚል ሳይሆን ምንድን ነን? የሚለው መሆን አለበት!  ( አቻምየለህ ታምሩ)

አሁን መጠየቅ ያለበት ጥያቄ  «ምን አለን»?  የሚል ሳይሆን ምንድን ነን? የሚለው መሆን አለበት! 

አቻምየለህ ታምሩ
በዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ  ይሁንታ በአገዛዙ የመሳሪያ ግምጃ ቤት  የተከማቸውን መሳሪያ ታጥቆ  ወለጋ የሸመቀው ኦነግ የሚባለው አሸባሪ ድርጅት እምቦቀቅላ የአማራ ተማሪዎችን በግፍ ካገተ ከኀምሳ ቀን በላይ ሆኖታል። አብዛኛዎቹ ታጋቾች ሴቶች የሆኑት እነዚህ የአማራ ተማሪዎች አገርና መንግሥት ስለሌላቸው ከኀምሳ  ቀን በላይ በኦነግ ታግተው ሲማቅቁ ሲከርሙ  እስካሁን ድረስ ሊያስለቅቃቸው የሞከረና ድምጽ ሊሆናቸው የፈለገ መንግሥት ነኝ የሚል አካል የለም። አማራ አገርና ሕዝብ ቢኖረው ኖሮ ከነዚህ እምቦቀቅላ ሴት ልጆች መታገት በላይ አገራዊ፣ መንግሥታዊና ሕዝባዊ አጀንዳ ባልኖረ ነበር።
የአማራው ሞሼ መሪን ንጉሡ ጥላሁን  በስምና በፎቶ ለይቶ ያልነገረንን ታጋች  የአማራ ተማሪዎች አገዛዙ ተደራድሮ እንዳስለቀቀ ከነገረን  ሁለት ሳምንት በላይ ቢሆነውም  እስካሁን ግን ተለቀቁ ከተባሉት  ተማሪዎች መካከል አንዳቸውንም ልናያቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሊገናኙ አልቻሉም።
አሁን ጥያቄው  አማራ ነን ብለን የምናስብ ሰዎች ምን አለን የሚለው ሳይሆን ምንድን ነን የሚለው ነው መሆን ያለበት። ምንድን ነን? ለሚለው ጥያቄ  መልሱ  ሰዎች ነን  የሚል ከሆነ  እየደረሰብን ያለውን ውርደትና ንቀት መሸከም  የሚችል ትክሻ ያለን ብቸኛ ሰዎች እኛ ብቻ መሆን አለብን!
ሰዎች ነን ብለን የምናስብ  አማሮች ሁሉ ብአዴን የሚባል የአማራ ጠላቶች እንደራሴ እስካለ ድረስ የአማራ ውርደት እንደሚቀጥል ካላሰብን  እየደረሰብን ያለውን ውርደትና ንቀት መሸከም  የሚችል ትክሻ ያለን ብቸኛ ሰዎች እኛ ብቻ እንሆናለን።
 ሁሉም ብአዴኖች ልክ እንደ ንጉሱ ጥላሁን ናቸው። የአማራ ሕዝብ በየቀኑ እየደረሰበት ካለው ውርደት ለመውጣት ፋሽስት ወያኔን በብርቱ እንደተፋለመው ሁሉ በእንደራሴነት የጫነበበትን የፋሽስት ወያኔን ነውረኛ ድርጅት ብአዴንም ከቀድሞ ጌታው ከፋሽስት ወያኔ እኩል መዋጋት አለበት። በብአዴን ውስጥ ከንጉሱ ጥላሁን የተለየ አስተሳሰብ ያለው ስናዳራዊ ይኖራል ብሎ ማሰብ ከጅልነት በላይ ቂልነት ነው።
ብአዴኖች ሁሉ የዐቢይ አሕመድ አተላ ተሸካሚ ሆኖ መኖር የሞቃቸው፤ በአስካሪስነት ዘመናቸው ባንዳ ሆኖ ከመኖር በቀር የሕዝባቸው ጉዳይ ቅንጣት ታህል አሳስቧቸው እንቅልፍ የማይነሳቸው፤ ኅሊናቸውን በዐቢይ አሕመድ ሙሉ ቁጥጥር ስር ያዋሉ ከርሳሞች፤ ዘወትር ለሆዳቸው ማደር የአእምሮ እረፍት የማይነሳቸው በድኖች፤ ባልበደላቸው የአማራ ሕዝብ ላይ የጠላቶቹን ሴራ ሲያስፈጽሙ ቀኑን ሙሉ ውለው ሌሊቱን ሙሉ ቢያድሩ የማይጠግቡ  የፖለቲካ ጅቦች ናቸው።
ባጭሩ  ሰዎች ከሆንን ፋሽስት ወያኔ፣ ናዚ ኦነግና የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ በአማራ ሕዝብ  ላይ እያደረሱት ያለው የዘር ማጥፋት አማራን ጠላት ያደረጉ ኃይሎችን አላማ ግንባር ቀደም መሳሪያ ሆኖ  እያስፈጸመ ያለውን ብአዴን  የሚባለው ስብስብ በአማራ ሕዝብ ላይ ተጭኖ እስከቀጠለ ድረስ  በከፋ ሁኔታ እንደሚቀጥል፤ አማራው  ወደፊትም ገና ብዙ ውርደት እንደሚጠብቀው ማሰባችንን በተግባር ማሳየት ይጠበቅብናል።
ቻይ ካመረረ ፤  በግ ከበረረ. . . 
 
ብአዴን የሚባለው የፋሽስት ወያኔ ነውረኛ ድርጅትና የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ እንደራሴ ወድቆበት የተዋረደው፣ የተናቀው፣ የተበደለውና ተለይቶ የተጠቃው የአማራ ሕዝብ  የመከራ ጽዋው ሞልቶ ሲገነፍልበት ለአመጽ መነሳቱ አይቀሬ ነው። የአመጽ ምዕራፍ መክፈቻ እንዲሆንለትም የሚከተለውን የአባቶቹን  እንጉርጉሮ ያሰማል፤
ታርሶም ተሸምቶም ይበላል እንጀራ፤ 
እንዴት አለሽ ጥቃት የሞት ባልንጀራ! 
በመጨረሻ ለአመጽ የሚነሳው አሁን እየተደረገበት  እንዳለው ጥቃቱና ውርደቱን ለመሸከም የሚችልበት ትከሻው ሲሰበርበት ነው። ውርደቱን የሚያሰተናግድበት የታጋሽነት ኅሌናው ሲሟጠጥበትና የትዕግስቱ ከረጢት ሞልቶ ሲተረተርበት፤ ትእግስቱን ወደ ንዴት  ነበልባልና ደም ወደሚያስተፋ ቁጣ ለውጦ ለአመጽ ይነሳል። ያን ጊዜ  የሚያቆመውና የሚገታው ኃይል አይኖርም።
ፍትሕና  ርትዕ በጎደልበት፤  ያገጠጠ  የአፓርታይድ ከአማራ አንጻር  በታወጀበት  አገር  ውስጥ አንድ ቋጫ ዕምባ ቢያፈስሱት አዛኝና ሰሚ ስለሌለ  አማራው ለበደሉ ሰሚ ይኖራል በማለት እየተጠቃ  የውርደት ኑሮ እየገፋ በዚህ ወቅት ካጋጠመው ብሔራዊ ሐዘን ሰልስት በኋላ አማራን የግፍ ሁሉ መሞከሪያ ያደረጉት ጠላቶቹ  በእንደራሴያቸው ብአዴን በኩል ተጨማሪ ውርደት ይዘውለት እስኪመጡ ድረስ ከመጠበቅ ከውርደት ኑሮ ለመላቀቅ  “ቻይ ካመረረ ፤ በግ ከበረረ” እንደሚባለው ቻይነቱን ወደ ቁጣ በመቀየር መተማመን ፈጥሮ  በአንድነት ከደረሰበት ውርደትና ሀፍረት ለመውጣት  ደም የሚያስተፋ ንዴትና ቁጣ ማሰማት አለበት።
Filed in: Amharic