>

መንግሥት፣ ምርጫ ቦርድ እና የብሮድካስት ባለሥልጣን ለወንጀለኛ እየሰጡት ያለው ከለላ!!! (ውብሸት ሙላት)

መንግሥት፣ ምርጫ ቦርድ እና የብሮድካስት ባለሥልጣን ለወንጀለኛ እየሰጡት ያለው ከለላ!!!

ውብሸት ሙላት
• የቱርክ መንግሥት የሚረዳው አንድ የፖለቲካ ድርጅት አለ፡፡ እንኳን ምርጫ ቦርድ እኔም አውቀዋለሁ፡፡ ቱርክ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበራት ቅጥ ያጣ የኢኮኖሚ እና የኢንቨስትመንት ጣልቃ ገብነት መገታት  ሲጀምር፣ የፖለቲካ ድርጅቶችን መርዳት ጀምራለች፡፡ ያለ ገድብ ቀጥላበታለች፡፡ አይደለም ምርጫ ቦርድ የዶ/ር ዓቢይ አስተዳደርም ይህንን መረን የለቀቀ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ አስድንጋጭ ነው!!!
በኢትዮጵያ ሕግ ጥምር ዜግነት አይፈቀድም፡፡ የሌላ አገር ዜግነት ያገኘ ኢትዮጵያዊ፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የኢትዮጵያ ዜግነቱን ያጣል፡፡ ኢትዮጵያዊ ዚግነቱን ያጣ ሰው ያወ የሌላ አገር ዜጋ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ሰው ስለኢትዮጵያ የማያደርጋቸውን ተግባራት ውስጥ እንዳይሳተፍ ሕግ ይከለክላል፡፡
ከእነዚህ መካከልም በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት  የብሮድካስት ሚዲያ ባለቤት  አለመሆንና በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ አለመሳተፍ የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ዜግነት ሳይኖረው፣ አንድ አሜሪካዊ ዜጋ የቴሌቪዥን ጣቢያ ውስጥ የባለቤትነት ድርሻ ኖሮት በይፋ እየሠራ ነው፡፡ የፌደራሉ መንግሥትም የብሮድካስት ባለሥልጣንም ሕጉ ሲጣስ እያዩ ትተውታል፡፡ ከሰውዬው ሕግ ጣሺነት በተጨማሪ የፌደራሉ መንግሥትም ሕግን ባማስከበር ተባባሪ ሆኗል፡፡ ይሄው ሰው በይፋ የፖለቲካ ድርጅት አባል ሆኖ በፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቷል፡፡
አንድ አሜሪካዊ የኢትዮጵያን ፖለቲካ እያቦካ ነው፡፡ እነ ዶ/ር ዓቢይም ፈርተውት እየተርበተበቱ ነው፡፡ መለኪያቸውም የሐሰት (ዓባይ) ሚዛን ሆናለች፡፡ የምርጫ ቦርድም ቢሆኑ ሕግን እያስከበሩ አይደለም፡፡ የምርጫ ቦርድ፣ የቦርድ አባላት፣ የሕግ ባለሙያዎች ቢሆንም ሕግ ቢጣስም ደንታ አልሰጣቸውም፤ አሊያም ይህን ሰው በሚመለከት ሕጉ ተፈጻሚ አይደለም፡፡ እንዲፈጸምም አልፈለጉም፡፡
ዶ/ር ዓቢም፣ብርሃኑ ጸጋዬም፣ ብርቱካን ሚደቅሳም፣ ዶ/ር ጌታቸው ድንቁም የጃዋር ግበረ አበሮች ናቸው፡፡ ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ጃዋር አባል የሆነበትን የፖለቲካ ፓርቲ ላይ እርምጃ መውሰድ ካልቻለች ወይም ካልፈለገች እሷም ያው ጃዋራዊያን ናት ማለት ይቻላል፡፡ የሕግ ባለሙያዎች የታጨቁበት የምርጫ ቦርድ፣ ሕግ ሲጣስ እያዩ ደንታ ካልሰጣቸው ሕግን መሠረት ያደረገ፣ ሕግ የተከበረበት ምርጫ ያደርጋሉ ብሎ መጠበቅ አዳጋች ነው!!!!!
[በነገራችን ላይ የቱርክ መንግሥት የሚረዳው አንድ የፖለቲካ ድርጅት አለ፡፡ እንኳን ምርጫ ቦርድ እኔም አውቀዋለሁ፡፡ ቱርክ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበራት ቅጥ ያጣ የኢኮኖሚ እና የኢንቨስትመንት ጣልቃ ገብነት መገታት  ሲጀምር፣ የፖለቲካ ድርጅቶችን መርዳት ጀምራለች፡፡ ያለ ገድብ ቀጥላበታለች፡፡ አይደለም ምርጫ ቦርድ የዶ/ር ዓቢይ አስተዳደርም ይህንን መረን የለቀቀ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ አስድንጋጭ ነው!!! ቱርክ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ዘው ብላ ገብታለች!!]
Filed in: Amharic