>

ዓላማና ዘዴ (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

ዓላማና ዘዴ

 

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

 

አንድ የጎሣ ድርጅት ከአንድ በላይ ቡድኖች ይኖሩት ይሆናል፤ እነዚህ የተለያዩት ቡድኖች በተለያዩ የሥልጣን ፍላጎት ባላቸው ሰዎች ይመራሉ፤ ነገር ግን ሁሉም ለሥልጣን አምሮታቸው መሠረት የሚያደርጉት የጎሣ ዝምድናን ነውና የአንድነት መድረሻ አላቸው፤ ስለዚህ በተመሳሳይ ጎሠኛነታቸው አይለዩም፤ ከጎሠኛነት ውጭ የሚያይዛቸው የፖሊቲካ ሀሳብ ወይም እምነት የላቸውም፤ ዋነው ዘዴያቸው መነሻቸውን ብዙ አድርገው መድረሻቸው ላይ አንድ መሆናቸው ነው፡፡

ከሕዝባዊው ምርጫ በኋላ እነዚህ በሥልጣን ፍላጎታቸው የተለያዩ የአንድ ጎሣ ቡድኖች በአገራዊ ሥልጣን ተወዳዳሪዎች ሆነው ከሌሎች የጎሣና የፖሊቲካ ቡድኖች ጋር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ለምርጫ ሲቀርቡ ወይም ሲፎካከሩ በጎሣቸው አንድ ሆነው ይሰባሰቡና የመንግሥትን ሥልጣን ለመያዝ ይችላሉ፤ ከሕዝባዊው ምርጫ በኋላ ያለው ዓላማ ይህ ነው፡፡

ከምርጫ በፊት በአገር ደረጃ ያለው ምርጫ ከአገራዊው ምርጫ በኋላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመንግሥት ሥልጣን የሚደረገው ውድድር ዓላማ የተለየ ነው፤ በሁለቱ ምርጫዎች መሀከል የሰማይና የመሬት ያህል ልዩነት አለ፤ የዘዴ ልዩነት ነው፤ እኔ ይህንን ዘዴ እሥራኤላዊ እለዋለሁ!

Filed in: Amharic