>

የፖለቲካ ጨዋታ (ታዬ ደንደዓ)

የፖለቲካ ጨዋታ

ታዬ ደንደዓ
እሾክ የሚወጋው የተከለውን ሰው ነው!!!
የኦሮሞ ተረት ነው። ተንኮል መልሶ ባለተንኮሉን ነው የሚጎዳው ለማለት ነው። ትላንት ደም ለመመለስ እንደምትታገል ተናገርህ ነበር። ትናንት በአንድነት እና በፍቅር የሚኖርን ህዝብ እምነት እና ብሄር ከፋፍለህ እንዲጠራጠር አደረክ። እሳቱ ሲነሳ ደግሞ ሌላ ሰው ተጠያቂ አደረክ። ለራስ የሰራህውን ወንጀል ለሌላ ሰው ማላከክ ትናንት የለመድከው ነው። አሁን የእውነት ጊዜ ተቃርባለች። ለበርካታ አመታት በድራማ ከኦሮሞ ላይ ገንዘብ ገንዘብ ሰበሰብክ።
አሁን ግን ያን ጊዜ አልፏል! ድራማ አዘጋጅቶ የኦሮሞን ድጋፍ መጠየቅ ቀርቷል። ህዝቡ ያንተን አጀንዳ አውቋል። ሀበሻ እና ምኒሊክ ያንተ ገበያ ናቸው። የኦሮሞ ድጋፍ ሲቀዘቅዝ ጠዋት ተነስተህ ሀበሻ እና ሚኒሊክ ብለህ ስድብ በመልቀቅ ገንዘብ ትሰበስባለህ። በዚህ መልክ የራስን ብሄር ታልባለህ። በቅርቡ በአሜሪካ የሰራህው ደባ ሚስጥሩ አሁን ወጣ። ስድብ እና ተቋውሞ እንደምትወድ ተናግረህ ነበር። ለምን የሰላም መንገድ ትተህ ሀበሻ ባለበት ቦታ አድርሱኝ አልክ? የእነሱ ተቋውሞ ነው የገንዘብ ምንጭህ።
ዛሬም የተማርከውን ነው ያደረከው። የሰንደቅ አላማ ዘመቻ አስመስለህ ግጭት ፈጠርክ። የተፈጠረውን ግጭት ልትጠቀምበት ፈለክ። እቅድህ ለፓርቲህ ድጋፍ ማሰባሰብ ነው። ለዚህም ዱርዬ በማሰባሰብ የራስህን ፅ/ቤት መስታወት ላይ የዲንጋይ ዝናብ አስወረድክበት። አሁን ይቺን አጀንዳ ይዘህ ወደ ገበያ ትወጣለህ። “ሀበሻ ጠልቶናል! የኛን እንቅስቃሴ ፈርቷል! አይናቸው ቀልቷል! ለዛ ነው ፅ/ቤታችንን የመቱት” በማለት በOMN ትተነትናለህ ወይም ታስተነትናለህ። ይህ አሁን አይሆንም። ድርጊቱ በህግ እና በስርዓት ብቻ ይመራ። ከዚህ ውጪ ከጥያቄ አታመልጥም። ዘንድሮም እሾክ የተከለውን ሰው መውጋት አታቆምም!ከአፋን ኦሮምኛ ወደ እማርኛ ተተረጎመ 
Filed in: Amharic