>
5:14 pm - Sunday April 20, 2651

እዝች አገር ላይ ምንስ የማይገርም ነገር አለ!!! (መስከረም አበራ)

እዝች አገር ላይ ምንስ የማይገርም ነገር አለ!!! 

 

 

 መስከረም አበራ
• “እኔ ጭቆና ወልዶ ያሳደገኝ ሰው ስለሆንኩ፣የጭቆናን ክብደት ስለማውቅ ኦሮሞ ስልጣን ይዞ ሊጨቁን ካሰበ፣ከተመኘ፣ከሞከረ ቸጉቬራችሁ ሆኜ እታገልላችኋለሁ ባዩ ጃዋር እግረኛ  ወታደሮቹ (የኦሮሚያ ፀጥታ እና የህግ አካላትን ይጨምራል)የሰውን ዲሞክራሲያዊ መብት ቀርቶ ሰብአዊመብት ሲደቀድቁ ፀጥ ረጭ ማለቱ(ሂዱ እስከምድርዳርቻ ያገኛችሁትን ሁሉ በጥብጡ ላለማለቱስ ምን መተማመኛ አለ?)
•  “የምኒልክን ቤተመንግስት ተቆጣጥረን የታደሰ ብሩን ሀውልት እናቆማለን!” የአንድነት የህብረት ዘመናዊ ፖለቲክስ አራማጁ ዶ/ር መረራ በብርሀን ፍጥነት ዘርኛና  ጽንፍ የረገጠ ፖለቲክስ አራማጅ
መሆናቸውን ሳይ ነገ ከነገ ወዲያ (የጃዋርን እግረኛጦር “ኢጆሌ እስከ ምርጫውስ ምን አስጠበቀን የነፍጠኞቹን ቤተ መንግስት እጅ እናድርግ!” ላለማለታቸውስ ምን ዋስትና አለን)
• የታገቱ ተማሪዎችን በተመለከተ በሴቶች ጉዳይ ሚኒስትሯ የተመራው የመንግስት “in action”፣የሃይማኖት መሪዎች ከሞት የበረታ ዝምታ። ከሁሉ ከሁሉ ወላጆች ቀን በቀን  እየሄዱ የሚያለቅሱበት የአማራ ክልል መንግስት መለጎም።
• የስዩም ተሾመ “አፈትላኪ” ፖስቶች 🙂  ከመቀሌ አክሱም ሆቴል ቦክሳዊ፣መጠጣዊ፣ህመማዊ እና ዳንኪራዊ ዜናዎች ከመቅፅበት “Divert” አድርገው ወደ አዲስ አበባው ባልደራስ ፀጉራዊ፣ ጎፈሬያዊ፣ከመከማዊ፣ቁንዳላዊ ወሬዎች መፈትለካቸው።
• በኢሬቻ  አንድ አይሉ ሁለት ( አንዱ አረንጓዴ ቀይ አረንጓዴ ከዛፍ ምልክት ጋር ያለው ሁለተኛው ነጭ ቀይ ጥቁር) አርማ የደረሱበትን ሁሉ ሲያከናንቡ፣በየታዩበት ሁሉ ሲያውለበልቡ፣በቀሚስ ሱሪያቸው ሲያትሙ የነበሩ ሌላው ቀርቶ የአቃቤ ህግ ብርሃኑ ፀጋዬን ፎቶ መስቀል አደባባይ ላይ ሰቅለው የነበሩ  የኦሮሞ ታጋዮች ዛሬ የሌላውን አርማ እያወረዱ ከመሬት ሲያደባልቁ። ምነው ሲባሉ “የእምነት በዓል ባንዲራ የለውም” ማለታቸው ይባስ !…. ኢሬቻ የእምነት በዓል ነው ብለውን ነበር፣ አከባበሩም ረዣዥም ባንዲራ ያጀበው ነበር። ምነው ከእኛ በላይ ላሳር በረከተ?ምነው አስር ሱሪ ታጠቅን በዛ!
Filed in: Amharic