>
5:13 pm - Friday April 19, 2154

ግድ የለም አብይን እንመነው!!!  (ሀብታሙ አያሌው)

ግድ የለም አብይን እንመነው!!!

 ሀብታሙ አያሌው
በኢሬቻ በአል በኦነግ ባንዲራ የተሽቆጠቆጠችው ኢትዮጵያ በታሪኳ ሁሉ በጥምቀት ስትለብሰው የነበረው ሰንደቅ ዓላም ተገፍፏል።  አብይ ጥሩ እያሻገረን ነው።  ግድ የለም አባቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ያከበሩት ሰንደቅ ዓላማ ይረገጥ አብይ ለኢትዮጵያ ችግኝ ውሃ ስለሚያጠጣ ችግር የለም።
ግድ የለም ለውጡ እንዳይደናቀፍ የነጀዋር ትዕዛዝ እንዳይጣስ እኛ ዝም እንበል ኢትዮጵያ ትውደም።  ግድ የለም  አብይን እናምነዋለን  ኢትዮጵያ ቆዳዋ ተገፍፎ እንዲህ ሚጥሚጣ ቢነሰነስባትም እሱ እስካለ አያማትም።  ግድ የለም መቶ ፐርሰንት እንመነው።
Filed in: Amharic