>
5:14 pm - Thursday April 20, 1009

ምርጫ በክረምት?!? (ተስፋዬ ሀይለማርያም)

ምርጫ በክረምት?!?

ተስፋዬ ሀይለማርያም
“…ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ፀልዩ” 
የማቴዎስ ወንጌል 24:21
እንደሟርተኛ እንዳትቆጥሩኝ አደራ። በአፍሪካ ከምርጫ ማግሥት ሽሽትና ስደት አይጠፋም። የኛም ምርጫ እነሆ ክረምት ላይ ዋለ። ስደትና ሽሽታችንም እንዲሁ እንዳይሆን። የሁሉም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስለክረምቱ ምርጫ ሲናገሩ፣
– “ወቅቱ ክረምት ነው፤ በዚያ ላይ ከባድ ጭቃ ስለሚኖር መራጮች ችግር ይገጥማቸዋል”
ኦቦ ዳውድ ኢብሳ
– “ዝናብ ስለሚሆን በሎጂስቲክስ ስርጭት ላይ ችግር ሊፈጠር ይችላል…
ኢ.ዜ.ማ
–  “በአገሪቱ ውስጥ አስተማማኝ ሰላም ስለሌለና ምርጫ ደግሞ ቀላል ነገር ስላልሆነ ምርጫው ሳይደረግ መራዘም ነበረበት”
 ልደቱ አያሌው
 
“ብልጽግና ፓርቲ መራጩን ህዝብ በማጉላላት ምርጫውን ለማሸነፍ እንዲመቸው ከቦርዱ ጋር ያወጣው ፕሮግራም ነው” 
የአፍላ ጎረምሳው  የጃዋር አስተያየት ነው
 
 ለዚህም እኔም የጃዋር ንግግር ስላስፈራኝ ነው ከላይ በመግቢያዬ ላይ ያለውን ጥቅስ ያስቀደምኩት።
ምንም እንኳን የልደቱ ኢዴፓ ምንም ዝግጅት ሳያደርግ ከእንቅልፉ ተነስቶ በእንቅልፍ ልቡ ምርጫ ውስጥ ላለመግባት የቀየሳት ዘዴ ብትሆንም፣ በተወሰነ መልኩ ገና ዛሬ ከልደቱ ሃሳብ ጋር ተስማምቻለሁ። የህዝብ ቆጠራ ሳይደረግና ከ25 ዓመት በፊት በነበረው የክልሎች ህዝብ ብዛት ላይ ተመስርቶ የወጣው መመሪያ ሳይሻሻል እንዲሁም አገሪቷ በአስተማማኝ ሰላም ላይ ሳትቆም የሚደረግ ምርጫ እኔም በግሌ አልቀበለውም። ለምን ቢባል ሽሽታችንን በክረምት ያደርግብናል።
ወገኔ! እኛ ስለ ምርጫ፣ ክረምትና ጭቃ ስንጨቃጨቅ ግብጽ ታንኮቿን አሰልፋ በቲቪ እያሳየችን ነው።
ለማንኛውም ምስኪኗ ህወሃት ስለ ክረምቱ ምርጫ ምን ትላለች ይሆን? እግረ መንገዳችንን ስደታችን በክረምት እንዳይሆን እንፀልይ።
Filed in: Amharic