>
5:13 pm - Saturday April 18, 9807

ተማሪዎችን ያገታቸው ማን ነው…? (ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው)

ተማሪዎችን ያገታቸው ማን ነው…?

ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው
    የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር አትመኑት በሚሉት እና በቅርብ  በስማቸው  አድራሻ ከፍተው በተቀላቀሉበት ፌስቡክ ነበር የተማሪዎቹ መጠለፍ ወሬ የተጀመረው፡፡ ይህ ወሬና መረጃ በሰአቱ ከአማራ ክልል ተወላጆች ፌስቡከሮች  ብቻ የሚሰማ ጉዳይ ነበር፡፡ እሳት በሌለበት  ጭስ አይታይም ነው ነገሩ፡፡
  በማህበራዊ ሚዲያው የተረናፈሰው ወሬ ግን ወሬ ብቻ ሆኖ አልቀረም፡፡ በብዙ ፖለቲካዊ አርምሞ እና መቆዘም ውስጥ የነበሩ ሰው ናቸው -አቶ ተመስገን ጥሩነህ፡፡  በገና ዋዜማ ግን ከነበሩበት ፖለቲካዊ አርምሞ እና መቆዘም ወጥተው መግለጫ ሰጡ፡፡ በዚህ መግለጫ ነው ጭሱ እሳት እንደነበረው የተጋገጠው፡፡
  የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት  አቶ ተመስገን ጥሩነሕ በኦሮሚያ የታገቱ የአማራ ክልል ተወላጅ  የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አሉ አሉ፡፡ ይህንን ጉዳይ ከመስማታቸው ባለፈ ለፌዴራል ፖሊስ እና ለከመከላከያ ሰራዊት  እንዳሳወቁ ተናገሩ፡፡ አቶ  ተመስገን ጥሩነሕ ግን በዚህ አላበቀም -ለፈፌደራራል ፖሊሲ እና ለመከላከያ ሰራዊት ብናሳውቅም ግን  መረጃ ማግኘት አልተቻለም ሲሉ ተናገሩ፡፡ ይህ ብዙዎችን አስደነገጠ፡፡ ፌዴራል ፖሊስ እና መከላከላካ ሃይል መረጃ ያላገኙበት ወንጀል የፈፀመው ማነው የሚለው አስደንጋጩ ጉዳይ ሆነ፡፡
አቶ ተመስገን ጥሩነህ ታህሳስ 27/2012 ዓም  የገና በአል ዋዜማ የሚመሩት የአማራ ህዝብ  ልጆች ታግተዋል ከማለት ውጭ ሌላ አላሉም! ፌዴራል ፖሊስ እና መከላከያ ያላወቀውን መረጃ አግኝተው ምን ማለት ይችሉ  ነበር፣…. ጥያቄ ነው፡፡
   ተማሪዎች  ታግተዋል በተባሉበት አካባቢ እና ሌሎች አካባቢዎች  አጠቃላይ የቴሌ አግልግሎት ከተቋረጠ ቀናት አልፈዋል የተባለውም በዚሁ ቀን ነበር፡፡ በተለይም ተማሪዎቹ ታግተዋል በተባለበት አካባቢም መጠነኛ ውጊያ እንዳለም ይፋ ተደረገ፡፡ ቢቢሲ አማርኛ እንዳስነበበው ከሆነ በአካበቢው የቴሌ አግልግሎት የቋረጠው በምን ምክንያት እንደሆነ አልታወቀም ነበር፡፡   ግን “የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎቱ እንዲቋረጥ የተደረገው በቴሌ ከፍተኛ አመራሮች ትዕዛዝ ነው።” በማለት ቢቢሲ አስነበበ፡፡
   ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ታህሳስ 28 /2012 ዓም ለይፋዊ የስራ ጉብት ጊኒ ኮናክሬ ገቡ፡፡  ዶከተር አብይ  ወደ ጊኒ ኮናከሪ በሚያቀኑበት በዚህ እለት ግን  በማህበራዊ ሚዲያው የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ዋና አጀንዳ ነው፡፡  ጠቅላይ ሚኒስተሩ የጎበኛዋት ሃገር ጊኒ ኮናክሪ  ጎረቤት  ናይጅሪያ ናት፡፡ ናይጀሪያ በቦኩ ሃራም ሲትታመስ የቆይች ሀገር ናት፡፡ በተለይም በፈረንጆቹ 2014 እና 2015 ቦኩ ሃራም በአክራሪነቱ የነገሰበት ወቅት ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ነበር  ቦኩ ሃራም የናይጀሪያ ልጃገረዶችን የጠለፈውና ያፈነው፡፡ አለም ልጆቻችንን መልሱ በማለት በተለያየ መንገድ  ተቃወመ፡፡
  ቦኩ ሃራም ግን በካዱ ግዛት  ከጠለፋቸው 238 ሴቶች  መካከል  አምልጠው የወጡ አራት ሴቶች ነበሩ፡፡ እነሱም  ለማስረጃነት ቀረቡ፡፡ ይደበድቡናል ይደፍሩናል አሉ፡፡ ቀሪዎችን ግን ከቦኩ ሃራም ማስለቅቅ አልታቸለም፡፡ አካባቢው ላይ ኔትወርካና የስልክ አግልግሎት እንዲቋረጥ ተደረጎ ነበር፡፡ በሰአቱ በናይጀሪያ ከፍተኛ  ባለሥልጣን የነበሩት ሰው በጉዳዩ ላይ ከሚታሙት ውስጥ አንዱ ነበሩ፡፡  እኒህ ሰው ኤል ሩፋይ  ናቸው፡፡  በአሁኑ ሰአት ልጃገረዶት የታገቱበት እና እሳቸውም አስቀድመው የታሙበት የካዱ ግዛት ገዥ ናቸው፤ ኤል ሩፋይ፡፡
   አጋጣሚ ነው ወይስ ሌላ በሚያስብል ደረጃ በጊኒ ኮናከሪ  ዶከተር አብይ ካገኟቸው ሰዎች እንዱ ኤል ሩፋ ናቸው፡፡ ከዚህ ሰው ጋር ጠቅላይ  ሚኒስት  አብይ አህመድን ያገኙ ሌላ የአፍሪካ ሃብታም ናይጀሪያውያን ደግሞ ማፍያ ባለሃብት የሚሏቸው እና በአለም ህገወጥ የሰወች ዝውውር ውስጥ ይሳተፋሉ ተብለው የሚታሙት  ስመጥር የንግድ ሰው ቶኒ ኦሉሜሉ  ነበሩ፡፡ በናይጀሪያ ቦኩ ሃራም ያስቸገራቸው ሃገረ ገዥ ኤል ሩፋይ እና  በወለጋ ኦነግ ሼነ ያስቸገራቸው  አብይ አህመድ አንድ ላይ መከሩ…; እንዴት ?  የሚለው ጥቄ ነው
   የሃገር ውስጥ የመንግት ሚዲያዊች ጠቅላይ ሚኒስተር ዶከተር አብይ አህመድ  የሚያድርጉትን  ጉብት ካለ እረፍት ያስነብባሉ ይነገራሉ ያሳያሉ! ነገር ግን  ስለ ልጃገረዶቹ መታፈገትም ሆነ በወላጋ ስላለው ጦርነት  ምንም አላሉም፡፡
    ከአቶ ተመስግን ጥሩነህ ቀጥሎ በሚዲያ ብቅ ያሉት አቶ ታየየ ደንደአ ናቸው፡፡ አርብ ማታ ጥር 01 /2012 ዓም በቪኦኤ የተጠየቁት አቶ ታየ ደንደኣ እና የብልፅግና ፓርቲ ሃላፊ አዎ የጣገጡ ተማሪዎች አሉ እሱንም ለማስለቀቅ የሽምቅ ውግያ እያካሄድኝ ነው አሉ፡፡ ከማን ጋ የሽምቅ ውጊያው እንደሚካሄድ እና የታገቱት ማሪዎች ስንት እንደሆኑ ግን አልተናገሩም፡፡ አቶ ታየ ደንደአ ይህንን አይናገሩ እንጂ ቢቢ አማርኛ ግን 17 የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጸጥታ ስጋት ወደ ትውልድ ቀያቸው ሲያመሩ በታጣቂዎች ከታገቱ ሳምንታት ተቆጠሩ  በማለት ዘገበ፡፡ ይህንንም የዘገበው ከታገጡት ውስጥ አምልጣ የወጣጨው ን ተማሪ ዋቢ ማድረግ እና በመጠየቅ ነው፡፡ ቢቢሲ አያይዞም  ተማሪዎቹ የታገቱት ከደምቢ ዶሎ ጋምቤላ በሚወስደው መንገድ ላይ ነው አለ፡፡
   ይህ ሁሉ ሲሆን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የሰባዊ መብት ታጋዪች፤ የሴቶች ጉዳይ  ሚኒስትሮች አና ተቆርቋራችም ሆኑ ሌሎት ባለስልጣናት ዝምታን መርጠዋል፡፡ የአማራ ክልል ሚዲያዎች እና ሌሎች የግል ሚዲያወችን ጨምሮ በርካቶች በጉዳዩ ላይ ትኩረት ሰጥተው እይዘገቡ ነው፡፡ ለመንግስት ቅርብ ነን የሚሉ እና ቅርበት አላቸው የሚባሉ የፌስቡክ ፀሃፊዎች ጉዳዩ ውሸት ነው አሉ፡፡ የታገተ ተማሪ የለም ሲሉም ተሳለቁ፡፡
ይህ ሁሉ እየሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ የኢኳቶሪያል ጊኒን የክብር ኒሻን ተሸለሙ።
ሽልማቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገር ውስጥ እና ሰላምን ከማስፈን አንጻር በአፍሪካ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የተበረከተ መሆኑም ታውቋል ሲል ፋና ዘገበ፡፡   ዜጎች ታፈነው የሚሰቃዩባት ሃገር መሪ ኒሻኝ መሸለማቻ ትዝብት በዛበት፡፡
     በዚሁ ቀን ማታ ነበር ዶናልድ ትርምፖ የሰላም ኖቦል ሽልማቱን ያስለምኩት እኔ ነኝ፤ ጦርነት አስቅርቻለሁ በማለት የተናገሩት! ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስረተር ዶከጀተር አብይ አህመድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ብቻ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ቢነገርም እሳቸው ግን ተማሪዎች ታገጡ ሲባል ወላጋ ላይ ጦርነት ጠናሳ ሲባል ብድግ ብለው ወዳለልተጠበቀ ሃገር አመሩ፡፡ ለምን አጋጣሚ ይሆን ይህም ጥያቄ ነው…
 ይህ በዕበነንዲህ እናዳለ የጥቀላ ሚኒስትሩ  ሬስ ሰክሬተሪያት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በሃገሪተ ብሄራዊ ሚዲያ ብቅ አሉ፡፡ ከታገቱት ውስጥ 21 አስለቅቀናል 6 ይቀረናል አሉ፡፡  ይህ መረጃ ብዙዎችን አስደነገጠ፡፡   የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ 4 ብቻ ተማሪች ታግተዋል አሉ፡፡ ከታገቱት መካከል ያመለጠችው ተማሪ ግን የታገትነው 17 ነን  አለች፡፡ የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ንጉሱ ደግሞ የታገቱት 27 ነበሩ 6ቱ አልተለቀቁም አሉ፡፡
   የተጋቱ ሰዎች መኖራቸው ያላመነው መንግስት ቃል አቀባ አቶ ንጉሱ ጥላሁን  የተለቀቁት ተማሪዎች የት እንዳሉ እና እንዴት እንደተለቀቁ ግን አልተናገሩም፡፡  የታገቱት ተማሪዎች ወላጆች ግን ይጠይቃሉ…. ልጆቻችንን ከተለቀቁ የት ነው ያሉት በማለት፡፡ አነዚህ ተማዎች ታገቱ የተባሉት በኦሮሚያ ክልለ ነው! የክልሉ ሃለፊዎች በተለይም የጽፀጥታ እና እና የደህንነት ሃላፊዎች ግን ስለጉዳዩ የሚመልስት መልስ አሳሳቢ ነው ።ቢቢሲ ቅዳሜ ጥር 2/2012 ዓ.ም. ያነጋገራቸው የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በምዕራብ ኦሮሚያ ስላለው ጠቅላላ ሁኔታ “ምንም አይነት መረጃ የለኝም። እኔ የሰማሁት ነገር የለም” በማለት መልሰዋል፡፡ ጉዳዩ እርሳቸው የሚመሩትን ቢሮ በቀጥታ የሚመለከት መሆኑን በመጥቀስ ስለጉዳይ እንዴት መረጃ ሳይኖራቸው እንደቀረ የተጠየቁት ኮሎኔል አበበ ገረሱ፤ “እኔ ምንም አልሰማሁም ነው የምልህ። ለምድን ነው የምትጠይቀኝ?” በማለት በቁጣ መልሰዋል።
  የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ በበኩላቸው ታፍነው የተወሰዱ ተማሪዎች የሉም በማለት ለቢቢሲ  ተናገረዋል፡፡ የፌደራል መንግስት የታገቱትን አስፈትቻለሁ አለ፡፡ ገና የማስፈታቸው አሉም አለ፡፡ አቶ ታዬ ደንደአ ሽምቅ ውጊያ ላይ ነን አሉ፡፡ ኦሮሚያ የደህንነት ባለሥልጣናት እና የመረጃ ሰዎች ደግሞ የምናውቀው ነገር የለም፤ የታገተም የለም አሉ!
   ይህ ሁሉ ሆኖ ቀናት ቢቆጠሩም ተለቀቁ የተባሉት ተማሪዎች  ከታገቱት እኩል ዳናቸው አልታየም፡፡ መጥሃም ዝመ ቄሱም ዝም!  ማን ምን እናደሆነ አልታወቅም፡፡ መንግስት የኦነግ ሸኔ ጦር ነው ያገታቸው ይበል  እንጅ በትክክል ያገታቸው ማን እንደሆነ ግን አልታወቀም፡፡
አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተለቀዋል ያሏቸው 21 ተማሮዎች አስካሁን በአካል አልታዩም፡፡  እሳቸው ዋሽተው ይሆን…?
የአውሎ ሚዲያ ምንጮች እንዳረጋጡት ከሆነ ግን  ከደንቢዶሎ ተማሪዎች በተጨማሪ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ  ጊምቢ ካምፓስም የታገቱ ተማሪዎች አሉ፡፡ እስከ ሞት የደረሰ ጉዳት የደረሰባቸው አሉም ተብላል፡፡
ማን ነው ያገታቸው…?
 የታገቱት ስንት ናቸው… ?
የተለቀቁጥስ የት ሄዱ..?  የሚለው እያነጋገረ ነው!
ዘጋቢ   በቃሉ አላምረው
አውሎ ሚዲያ ጥር 4/2012 ዓም
Filed in: Amharic