>

" የእስክንድር ነጋን መንገድ እደግፋለሁ !!! " (አርቲስት ሽመልስ አበራ)

” የእስክንድር ነጋን መንገድ እደግፋለሁ !!! “

አርቲስት ሽመልስ አበራ
በይድነቃቸው ከበደ
መንግስት እያለ ማንም ወጥቶ ድንጋይ እየኮለኮለ መንገድ ሲዘጋ ዝም ይባላል፡፡ ሱዳን እኮ ዳቦ ላይ 10 ሳንቲም ተጨመረ ተብሎ ነው ሰዉ ሰልፍ የወጣውና መንግስትን ያስወገደው፡፡ እዚህ ሰላም አጥተህ እየኖርክና በኑሮ እየተሰቃየህ መቃወም አትችልም ትባላለህ፡፡ ችግሩ መቼ ነው የሚፈታው ስትል ሀገር የሚገዙትም ዝምታ ነው መልሳቸው፡፡
      ይህ ዝምታ እስከመቼ ነው የሚቀጥለው ብዬ ነው የምቃወመው፡፡ ዛሬ ላይ ስልጣኑ ከላይ እስከ ወረዳ የተያዘው በአንድ ቡድን ነው፡፡ ባንኩም ሆነ ሌላው የተያዘው በአንድ ወገን ነው፡፡ ትምህርቱ፡ እውቀቱና ብቃቱ እስካለው ድረስ የፈለገውን ያክል ጊዜ ማንም ቢገዛ በግሌ ቅሬታ የለኝም፡፡
      ዛሬ ላይ አክቲቪስት ነን የሚሉት እነ ጃዋር ምን እንደሚፈልጉ እንኳን አይገባኝም፡፡ የፈለገውን ያክል ህዝብ ቢኖርህ በጉልበት መግዛት አትችልም፡፡ ባለፈው 27 አመታት ይህ አከተመ፡፡ ህወሀትና ደርግ ይገረሰሳሉ የሚል ግምት ማን ነበረው፡፡ ዛሬ ሁሉም ተለወጠ፡፡ ዛሬ ላይ የአዲስ አበባ ህዝብ ለምን መቃወም እንዳይችል ተደረገ ?! እኔኮ የኢትዮጵያ ባንዲራ ያለበት ሰደሪያ ለብሼ መስቀል አደባባይ ለበአል መገኘት የተከለከልኩበት ጊዜ ገጥሞኛል፡፡
እኔ ዛሬ ላይ የእስክንድር ነጋን መንገድ እደግፋለሁ፡ ይህን ማድረግ ደግሞ መብቴ ነው፡፡ ለምሳሌ ሌላ ቦታ ተቃውሞና ሰልፍ ማድረግ እየተፈቀደ አዲስ አበባ ይከለከላል፡፡ ለምን ?!  ( አርቲስት ሽመልስ አበራ በጄቲቪ ለጆሲ ከሰጠው ቃለመጠይቅ የተወሰደ )
Filed in: Amharic