>

አምጠን በወለድናት መዲናችን ላይ ቄሮ መጣ አልመጣ እያልን እንድንገላመጥ መደረጋችን የሚያስለቅስ ነው!!! (ያሬድ ጥበቡ)

“ባልደራስ ለዕውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ” ቅድመ ጉባኤ  የምዝገባ ሂደት አዳራሽ ተከልክሎ ሜዳ ላይ ተካሂዷል!!!

ያሬድ ጥበቡ
አምጠን በወለድናት መዲናችን ላይ ቄሮ መጣ አልመጣ እያልን እንድንገላመጥ መደረጋችን የሚያስለቅስ ነው!!!
 
* 90 ሺህ ብር የተከፈለበት ሪሲት ተያይዟል
 
 የሥርአቱን ህገወጥነትና ብልግና ያሳየ ሂደት ነው። እስክንድር የሜዳውን ስብሰባ የመራበት መቻኮልና አለመረጋጋት ከኦሮሚያ ፖሊስና ቄሮ መምጣት በፊት ስብሰባውን ቶሎ ለመጨረስ ካደረገው ጥረት አኳያ መታየት ያለበት ይመስለኛል።
በመጨረሻ፣ ከዚህ በፊት ብርሀኑ ነጋ እየደጋገመ እውነተኛ ዴሞክራሲ ሲል “ምን ለማለት ፈልጎ ነው? ዴሞክራሲ እውነተኛ/ ሀሰተኛ ወዘተ ተብሎ ይከፈላል ወይ?” የሚለው ጥያቄዬ ከደጋፊዎቹ በኩል አቧራ አስነስቶ ነበር። ሆኖም ዛሬም ለእስክንድር ነጋ መልሼ የምጠይቀው ነው።
“እውነተኛ” የሚለው ቅፅል ለምን አስፈለገ? ዴሞክራሲ ግብ ነው ወይስ ሂደት? ሂደት ከሆነ የሃገሩ ንቃተህሊና ፣ የሀይል አሰላለፍ፣ የዜግነት ደረጃ ወዘተ የሚወስነው አይደለም ወይ? የሚሉትን በመጠየቅ በድርጅቱ ስም ላይ ወደፊት በጉባኤ ቋሚ ከመደረጉ በፊት በቂ ውይይት እንዲደረግበት ማሳሰብ እወዳለሁ።
እስክንድር የሜዳውን “ስብሰባ” ሲመራ ያሳየውን መቻኮልና አለመረጋጋት ግን ቀልቤ አልወደደውም። አምጠን በወለድናት መዲናችን ላይ ቄሮ መጣ አልመጣ እያልን እንድንገላመጥ መደረጋችን የሚያስለቅስ ነው። ይሄን እያየን መንግስት አለ፣ ተቀባይነትና ተአማኒነት ያለው ምርጫ  ማካሄድ ይቻላል የሚለው እሳቤ ፈፅሞ አይገባኝም። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሀይሎች ቅድሚያ ሊሰጡት የሚገባው ቄሮን የማይፈራ የሽግግር መንግስት ማቋቋምን እንጂ ለምርጫ መዘጋጀትን መሆን አልነበረበትም። ሳይቃጠል በቅጠል ያለው ማን ነበር ጃል?
Filed in: Amharic