>
5:13 pm - Sunday April 19, 9367

ማን ይናገር የነበረ! (ዮናስ መኮንን)

ማን ይናገር የነበረ!

ዮናስ መኮንን
የኦነግ ሸኔ ግንጣይ እንደሆነ የሚነገርለት ጃልመሮ እና ወታደሮቹ ወለጋን ሠላም እንደነሷት ዓመት አለፈው። ይህንኑ ተከትሎም መንግሥት አካባቢውን ለማረጋጋት በኮማንድ ፖስት እያስተዳደረው ይገኛል። 
.
ሰሞኑን ታዲያ በአከባቢው የስልክ እና የኢንተርኔት መቋረጥን ተከትሎ አቶ ጃዋር “መንግሥት ወለጋ ላይ እያደረገ ስላለው ነገር በአስቸኳይ ማብራሪያ ይስጠን። ስልክ እና ኢንተርኔቱንም ይመልስ።” ሲል አስተያየት ለበስ “ትእዛዝ” ይሰጣል። ለዚሁ የአቶ ጃዋር “ትእዛዝ” በቁቤ መልስ የሰጡት አቶ ታዬ ደንደአ ናቸው። የአቶ ታዬን ጽሑፍ ኦሮምኛ ለማያነቡ ወደአማርኛ መልሼዋለሁ።
.
ለወለጋ እንጩኹላት”
የነጋዴ ስብከት!
.
የወለጋ ህዝብ አስከፊ ችግር ውስጥ ነው የቆየው። በሠላም ወጥቶ መግባት አቅቶታል። ማረስ እና መነገድ ቸግሮታል። በገዛ ቀዬው ተገድሎ አስከሬኑ ተቃጥሏል። ከነሕይወቱ ተሰቅሎ መቀጣጫ ተደርጓል። ታምሞ ሕክምና አያገኝም። ተሸብሮ የሆዱን አውጥቶ መናገር አልቻለም። አባወራ በሚስቱ እና በልጆቹ ፊት ተገርፎ ተገድሏል። ይህንን ሰቆቃ ሀገር ያውቀዋል። እውነት ነው ለወለጋ ህዝብ መጮኽ ያስፈልጋል።
.
ነገር ግን እንዴት? ይህንን ህዝቡን የሚያሸብርን ይህንን ክፉ ሽፍታ ወለጋ ውስጥ እንዲሰነባብት ሠልፍ መውጣት ይሻላል ወይስ ህዝቡ ከፍርሃት እና ከጭንቀት እንዲወጣ ማገዝ ነው መንገዱ? ይቺ ትናንት መሮ (ጃል መሮ) ዘፍኖ ዛሬ ሸኔ (ኦነግ ሸኔ) ላይ ነገሩ ሲጠብቅ ሠልፍ ለመጥራት ጥያቄ ነው።
.
ህዝቡ እንደጠላት ሲንገላታ ዝም ብሎ መንግሥት ህግ ለማስከበር እርምጃ ሲወስድ በህዝብ ስም ለሽፍታ መጮኽ ምን ይሉታል? ህዝብ መውደድ ህዝብን ለሚያስጨንቅ ሽፍታ ጥብቅና መቆም መቆም ነው ለካ! ማንም ሰው ተንጫጫም ዝምም አለ ወደኋላ የሚመለስ ነጠር የለም።የሕግ የበላይነትን ማስከበር ግዴታ ነው።
.
በእውነት ለወለጋ የሚያዝን ሽፍታን አደብ ለማስገዛት የየሚደረገውን እንቅስቃሴ ማገዝ ይገባል። ከዚህ ውጪ ያለው ስብከት ንግድ ነው! በህዝብ ደም እና ጭንቀት ከዚህ በላይ መነገድ ደግሞ አይቻልም። ህዝብም መንግሥትም አይፈቅዱም!
Filed in: Amharic