>
5:15 pm - Monday May 11, 6065

ለሰላሳ አመታት የታገልንለት ለውጥ ኢህአዴግን  በህዝብ ድምጽ  ከስልጣን በማሰናበት ፍሬ አፍርቶ እናያለን!!!!  (የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት - D.W)

ለሰላሳ አመታት የታገልንለት ለውጥ ኢህአዴግን  በህዝብ ድምጽ  ከስልጣን በማሰናበት ፍሬ አፍርቶ እናያለን!!!

D.W ሠለሞን ሙጬ 
የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት በቀጣዩ ምርጫ እጩዎቹ በአዲስ አበባ የሚሳተፉ ቢሆንም ፣ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚንቀሳቀሱ ሃገር አቀፍ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ተጣምሮ ሃገራዊ አማራጭ የሚሆን ጥምረት እና ቅንጅት ይዞ ምርጫውን በሙሉ ልብ እና ሃይል እንደሚገባበት አስታውቋል።
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ በአሜሪካ እና አውሮፖ የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ዛሬ አዲስ አባባ ሲገባ ኢትዮጵያ ውስጥ ለ ሰላሳ አመታት በሰላም የታገልንለት ለውጥ ኢህአዴግን በሰላማዊ መንገድ ከስልጣን በማሰናበት ፍሬ አፍርቶ እናያለን ብሏል። በሄደባቸው ሃገሮች ሁሉ “ጀግኖች ወገኖቼ” ያላቸው ዲያስፖራዎች የተሟላ የፋይናንስ እና የሞራል ስንቅ አስታጥቀው እንደመለሱትም ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በተደረገለት አቀባበል ላይ ተናግሯል።
እሁድ የፓርቲ ቅድመ እውቅና ለማግኘት የሚያስፈልገውን ህጋዊ መስፈርት ሟሟያ ስብሰባ እንደሚያካሂዱ የገለጸው የባለ አደራው ምክር ቤት ሳብሳቢ ሰኞ ህጋዊ ሰርቲፊኬቱን ለማግኘት ወደ ምርጫ ቦርድ እንደሚሄዱም ተናግሯል።
ይህንን ካለፉ በኃላም የፓርቲ የመስራች ጉባኤ በማድረግ በቀጥታ ወደ ምርጫ እንደሚገቡ አስታውቋል። ኢህአዴግ አዲስ አባባ ላይ ካሉ 23 የፌዴራል መቀመጫዎች ላይ በምርጫ አንድም ወንበር ማግኘት የለበትም፤ ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ከዛሬ ጀምሮ እንሰራለን ብሏል። አዲስ አበባ በመሰረታዊነት የክልልነት ጥያቄ እንዳላት እና የባለ አደራው ምክር ቤት አንዱ ትልቅ ጉዳይ መሆኑንም ነው እስክንድር ነጋ የተናገረው።
በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ላይ የኦሮሚያ ልዬ ጥቅም የማይል ህገ መንግስትም እንደሚፈልጉ ገልጿል።
Filed in: Amharic