>

47 ሽህ ተማሪዎች ከኦሮሚያ፤ 391 ከአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ተባረዋል ! (ሚኪ አማራ) 

47 ሽህ ተማሪዎች ከኦሮሚያ፤ 391 ከአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ተባረዋል

ሚኪ አማራ 
የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባጠቃላይ 11 ሰራተኞች እና 395 አካባቢ ተማሪዎች ላይ እርምጃ ወስጃለዉ ብሏል፡፡ ጎንደር ዩኒቨርስቲ ወደ 52 ተማሪ 8 ሰራተኛ አባርሪያለዉ ብሏል፡፡ ወሎ ዩኒቨርስቲ 331 ተማሪ እና 3 ስታፎች፡፡ ይህ ሲደማመር 391፡፡ እስካሁን እርምጃ ከተወሰደባቸዉ ተማሪ እና መምህራን (395 በጠቅላላዉ) 391 የሚሆኑት አማራ እና በአማራ ዩኒቨርስቲዎች ብቻ ላይ ነዉ፡፡
ሌላኛዉን ቁጥር እንየዉ፡፡ ከደንቢደሎ ወደ 15 የሚሆኑ ተማሪዎች ደብዛቸዉ ጠፍቷል፡፡ ወለጋ ዩኒቨርስቲ 3 የአማራ ተማሪዎች ሞተዋል፡፡ ደንቢ ዶሎ 2 የአማራ ተማሪዎች ሞተዋል፡፡ ድሬዳዋ 2 የአማራ ተማሪዎች ሞተዋል፡፡ አለማያ ዩኒቨርስቲ 2 የአማራ ተማሪዎች ሞተዋል፡፡ ወልደያ ዩኒቨርስቲ 1 ደሴ 2 ተማሪዎች ሞተዋል፡፡47 ሽህ የአማራ ተማሪዎች ከኦሮሚያ አካባቢ ካሉ ዩኒቨርስቲዎች ትምህርት አቋርጠዉ በየቤታቸዉ ተቀምጠዋል፡፡
ስለዚህ ችግር የሚፈጠረዉ ኦሮሚያ ነዉ፡፡ እርምጃ እየተወሰደ ያለዉ አማራ ነዉ፡፡ አሁን ሳጣራ ወደ አማራ ዩኒቨርስቲዎች ለማጣራት ብሎም እርምጃ እንዲወስዱ ተብለዉ የመጡት የኦዲፒ አመራሮች ናቸዉ ተብያለሁ፡፡ ለምሳሌ ጎንደር አእነና ወልደያ ዩኒቨርስቲ ለማወያየት ከመጡት ዉስጥ የኦዲፒ ባለስልጣን እና የኦሮሚያ ክልል ሃላፊ እንዲሁም የኦዲፒ የፓርላማ አባል እንደተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አድሏዊ በሆነ መንገድ የአማራ ተማሪዎን እና አስተማሪዎችን እንዲሁም ዩኒቨርስቲዎችን ትኩረት አድርጎ እርምጃ እየወሰደ ነዉ፡፡ ይሄን ነገር ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የአማራ ሙሁራን እና መምህራን ጥያቄ ሊያነሱ ይገባል፡፡ ዝም ብሎ ማየት ተገቢ አይደለም፡፡
Filed in: Amharic