>
5:13 pm - Tuesday April 19, 6405

አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን የኦሮሚያ የማድረግ የሴራ ዲፕሎማሲ! (ቅዱስ ማህሉ)

አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን የኦሮሚያ የማድረግ የሴራ ዲፕሎማሲ!

ቅዱስ ማህሉ
 
ይህ ከታች የምታዩት ቅጽ የአሜሪካ መንግስት ይፋዊ ድረገጽ ነው! የአሜሪካ ፌደራል መንግስት ድረገጽ ላይ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚገልጽ ሰው ከየትኛው የኢትዮጵያ አካባቢ እንደሆነ በድጋሚ ይጠየቃል። በዚያ አማራጭ ላይ አዲስ አበባና ከዚህ በታች የምታይዋቸው ክልሎች ይዘረዘሩ ነበር። አሁን ላይ አዲስ አበባ የት እንደገባች አይታወቅም። በዝርዝሩ ውስጥ የለችም። ምናልባት የኦሮሞ አክራሪ ብሄርተኞች እና በኦዴፓ የሚመራው “መንግስት” በኦሮሚያ ስር ውጠዋት ይህንኑ ለአሜሪካ እና ለሌሎች መንግስታት  ማስተካከያ እንዲያደርጉ በደብዳቤ አሳውቀው ሊሆን ይችላል። ባለፈው የኦሮሞ ክልልን ካርታ እስከ ወሎ ድረስ ሰርተው ጎግልን አሳስተውት ነበር። ከፍተኛ በሆነ ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ሃይበርኔት የሚያደርጉት የአማራ ክልል ገዥዎች ኋላ ከእንቅልፋቸው ለአፍታ ባነው የቅሬታ ደብዳቤ ለኦዴፓ አለቆቻቸው ጽፈው ነበር። መልስ ያግኙ አያግኙ አይታወቅም። አዴፓ ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ የተባለው እየደረሰበት ነው።
ለባርነት ራሱን አሳልፎ የሸጠው ራሱ ነው። አሁንም አዲስ አበባን አንቀላፍቶ ሳያሸጣት አይቀርም። ምናልባት ካላወቁ ላፍታም ቢሆን ከእንቅልፋቸው ነቅተው የቅሬታ ደብዳቤ በድጋሚ ይጻፉና እንደተለመደው ከሆነ በኋላም ቢሆን “አለን” ይበሉና ይተኙ። በተረፈ በውጭ ሃገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና አዲስ አበባን በአዲስ አበባነት እና የኢትዮጵያ ህዝብ መዲና መሆኗን የሚቀበል ሁሉ ፒቲሽን በማሰባሰብ የአሜሪካ መንግስት ከፌደራል ቅጾች ላይ ያነሳትን አዲስ አበባ በድጋሚ እንዲያስገባ ይረባረቡ።
በርግጥ የአሜሪካ መንግስት ከነባሩ የክልል እና አስተዳደር ነባር ዝርዝር  ውስጥ ያወጣው አዲስ አበባን ብቻ ሳይሆን ድሬዳዋንም ጭምር ነው። ጥያቄው የት ሄዱ ነው? በተዘረዘሩት ክልሎች ውስጥ በየትኛው ተካተው ይሆን የሚል ነው። በአሜሪካ የሚኖር ማንኛውም ሰው ይህን ለማረጋገጥ ስልኩን ወይም ሌሎች የፌደራል መንግስት ፎርሙ ውስጥ ለመግባት የሚያስፈልጉ ጥያቄዎችን አሟልቶ ሊያገኘው ይችላል። ፎርሙ የሚገኝበት የአሜሪካ መንግስት ይፋዊ ድረገጽ ይህ ነውhttps://www.usajobs.gov ።  በአዲስ አበባ ለሚገኘውም የአሜሪካ ኢምባሲ የቅሬታ ደብዳቤ በመጻፍ ጉዳዩን እናሳውቅ። ባልደራስ እና ሌሎች የፖለቲካ ሃይሎችም በኦፊሴል ለአሜሪካ ኢምባሲ ደብዳቤያቸውን ይላኩ።እርስዎም ይህንን ጥሪ ለብዙዎች በማሳወቅ እና በማስተላለፍ የበኩልዎን ይወጡ!
Filed in: Amharic