>

የአሕመዲን ጀበል ማምታቻ (ክፍል ፪) [አቻምየለህ ታምሩ]

የአሕመዲን ጀበል ማምታቻ

(ክፍል ፪)አቻምየለህ ታምሩ

እነ አሕመዲን ጀበል ለመንጋቸው ከማይነግሯቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ  እውነቶች በጥቂቱ!

 
አበው «ውሸትና ስንቅ  እያደር ይቀላል» እንዲሉ የኦነጉ የፕሮፓጋንዳ ጸሐፊ የአሕመዲን ጀበል ውሸት  በራሱ ቀሏል።  ከትናንትና በስትያ LTV ላይ ቀርቦ “የኢትዮጵያን ሕገ መንግሥት ለምሳሌ የኃይለ ሥላሴን የ1923ቱን ስናይ በግልጽ ሕገ መንግሥቱ መግቢያ ላይ ኢትዮጵያ በታሪኳ በአረመኔዎችና በእስላሞች ተከባ ስትጨነቅ እንደኖረች እያለ ነው መንደርደሪያው የሚነሳው፤ ሕገ መንግሥት ተብሎ የቀረበው ሙስሊዎችን በአሉታዊ መልኩ የሚያይ ነው።” ብሎን ነበር።
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የ1923ቱ ሕገ መንግሥት ውስጥ በLTV  ቀርቦ  የተናገረው እንደሌለና ትርክቱ የእሱ የራሱ  ፈጠራ እንደሆነ  በትናንትናው እለት የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የ1923 ዓ.ም. ሕገ መንግሥት ሙሉውን እዚህ ፌስቡክ ላይ በማተም  ስናጋልጠው «እኔ ያጣቀስኩበት  በኢንተር አፍሪካ ግሩፕ የታተመውንና ከ1923-1983 የነበሩትን ሕገመንግስቶችን በአንድነት የያዘው ‹‹የኢትዮጵያ ሕገ- መንግሥት ከ1923-1983 ልዩ ዕትም (ቁጥር 1)›› የሚለው መጽሐፍ ላይ ‹‹በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የቆመ ሕገ-መንግስት ሐምሌ 9 ቀን 1923›› በሚል ርዕስ በሚጀምረው የንጉሡ መግቢያ (መቅድም) ነው» የሚል ነገር ይዞ መጣ።
የአሕመዲን ውሸት የቀለለው «የ1923ቱን [ሕገ መንግሥት]  ስናይ በግልጽ ሕገ መንግሥቱ መግቢያ ላይ ኢትዮጵያ በታሪኳ በአረመኔዎችና በእስላሞች የተከበበች» በሚል በLTV  የ1923ቱን ሕገ መንግሥት ምንጭ አድርጎ ከጠቀሰበት ወደ  «ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ በ1985 ዓ.ም. ‹‹የኢትዮጵያ ሕገ- መንግሥት ከ1923-1983 ልዩ ዕትም (ቁጥር 1)›› በሚል  ከ1923-1983 የነበሩትን ሕገመንግስቶችን በአንድነት የያዘ» ወዳለው መጽሐፍ ነው።
አሕመዲን ጀበል ለስሙ የታሪክ ተመራማሪ ነኝ ይላል። አንድ ምንጭ ትክክለኛ ቅጂ [original and authentic] ነው የሚባለው ከእናት መዝገቡ ወይም ከዋናው ቅጂ  የሚገኘው ማስረጃ  እንደሆነ ግን አያውቅም። ቀደም  ስላሉ  መጽሐፍትና ድርሳናት ጥናት የሚጠበብ  Philology የሚባል የጥናት መስክ አለ። ይህ የጥናትት ዘርፍ የሚያጣራው ይህንን ነው።  ከዋና ቅጂ ጋር ያልተገኘ  ወይም እናት መዝገብ የሌለው ማንኛውም ምጭ  ታሪክ ምንጭ ሊጠቀስ አይገባውም። አሕመዲን ጀበል የ1923 ዓ.ም. እየጠየቀ ያላወቀው Philology የሚባለውን የጥናት መስክ ብቻ ሳይሆን ታሪክ እንዴት እንደሚጠና  ጭምር ነው።  በ1923 ዓ.ም. የታተመውንና ዋናውን የሕገ መንግሥት ቅጂ መጥቀስ ሲችል  በወያኔ ዘመን በ1985 ዓ.ም. አንድ መጽሐፍ ላይ የታተመና በዋናው ሕገ መንግሥት ላይ የሌለ ዝባዝንኬ የተሞላበት ድርሰት  ለፖለቲካው ስለሚጠቅመው ብቻ እንደ  ምንጭ መጥቀሱ  የተገኘው ሁሉ ሳይመረመር ለምንጭነት እንደማይውል  አለማወቁን ራሱን አጋልጧል።
በወያኔ ዘመን የታተመው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ  ዘመነ መንግሥት የመጀመሪያው ሕገ መንግሥት አንቀጽ ሁለት እንዲህ ይላል፤

የኢትዮጵያ መሬቱም፣ ሕዝቡም፣ ሕጉም፣ በጠቅላላው የንጉሠ ነገሥቱ ነው።”

ይህን አንቀጽ እየጠቀሱ ብዙ ሰዎች ንጉሡን ሕዝቡን፣ መሬቱን፣ ሕጉን የኔ ነው ብለው ሕገ መንግሥታቸው ላይ ጽፈዋል እያሉ  የንጉሠ ነገሥቱን  መስተዳድር ለማጥላላት ያልሰነዘሩት ትችት አልነበረም። ሆኖም ግን ዋናውንና የመጀመሪያውን  የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ  ዘመነ መንግሥት  ሕገ መንግሥት አንቀጽ ሁለት ስትመለከቱ እንዲህ ነው የሚለው፤
“የኢትዮጵያ መሬቱም፣ ሕዝቡም፣ ሕጉም፣ በጠቅላላው የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ነው።”
የወያኔው ዘመን ሕትመት «መንግሥት» የሚለውን ቁልፍ ቃል  በሴራ ስለተዘለለ ነው  እንግዲህ «ንጉሡን ሕዝቡን፣ መሬቱን፣ ሕጉን የኔ ነው ብለው ሕገ መንግሥታቸው ላይ ጽፈዋል» እያሉ በርካታ አጥኚ ነን የሚሉ ሰዎች የውሸት ታሪክ የጻፉት።
አሕመዲን ጀበልም በLTV ላይ ቀርቦ  የ1923ቱን ሕገ መንግሥት ምንጭ አድርጎ የሕገ መንግሥቱ መግቢያ «ኢትዮጵያ በታሪኳ በአረመኔዎችና በእስላሞች የተከበበች አገር» ይላል እንዳላለን ሁሉ የ1923 ዓ.ም. ሕገ መንግሥት ሲወጣ ግን እኔ  «እኔ ያጣቀስኩ  ከ1923-1983 የነበሩትን ሕገ መንግስቶችን በአንድነት የያዘውና ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ  ‹‹የኢትዮጵያ ሕገ- መንግሥት ከ1923-1983 ልዩ ዕትም (ቁጥር 1)›› በሚል ካሳተመው መጽሐፍ ነው» በማለት በ1985 ዓ.ም.  ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ  አሳተመው ያለውን መጽሐፍ ምንጭ አድርጎ መጣ።  አንድ ምንጭ ትክክለኛ ቅጂ [original and authentic] ነው የሚባለው ከእናት መዝገቡ ወይም ከዋናው ቅጂ  የሚገኘው ማስረጃ  እንደሆነ ብቻ መሆኑን ስለማያውቅ የ1923ቱና ዋናው የሕገ መንግሥቱ ቅጂ ወጥቶ ሳለ ከስድሳ አምት ዓመታት በኋላ ታተመ ያለውንና ሕገ መንግሥት ያልሆነ መጽሐፍ በመጥቀስ የቀለለውን ውሸቱን ለመከላከል ይሞክራል። የአሕመዲን ጀበል «የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የመጀመሪያው ሕገ መንግሥት ኢትዮጵያ  በአረመኔዎችና በእስላሞች ተከባ ስትጨነቅ የኖረች አገር» ማለት አለበት ብሎ ስለተነሳ ዋናው የሕገ መንግሥት ቅጂ እንኳ ቀርቦለት ተሳስቻለሁ ብሎ ለመታረም ዝግጁ አይደለም።
በራሱ ለማጣራትና ለማሰብ ፈቃደኛ ያልሆነው መንጋውም  16 ገጾች፣ ሰባት ምዕራፎችና 55 አንቀጾች ባሉት ዋናው የ1923ቱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የመጀመሪያ ሕገ መንግሥት ውስጥ በየትኛው የሕገ መንግሥቱ ገጽና ክፍል ላይ ነው ኢትዮጵያ በታሪኳ በአረመኔዎችና በእስላሞች ተከባ ስትጨነቅ እንደኖረች የሚያወሳው ብሎ አይጠይቀውም።
«የ1923ቱን [ሕገ መንግሥት]  ስናይ በግልጽ ሕገ መንግሥቱ መግቢያ ላይ ኢትዮጵያ በታሪኳ በአረመኔዎችና በእስላሞች የተከበበች አገር» ይላል ሲል አሕመዲን ጀበል  በድፍረት ስለተናገረው ጉዳይ እስቲ በ1985 ዓ.ም. ከታተመ መጽሐፍ ሳይሆን 16 ገጾች፣ ሰባት ምዕራፎችና 55 አንቀጾች ካሉት ከዋናው የ1923ቱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የመጀመሪያ ሕገ መንግሥት ውስጥ በየትኛው የሕገ መንግሥቱ ገጽና ክፍል ላይ እንደዚያ እንደሚል  አቅርብ በሉት?

እነ አሕመዲን ጀበል ለመንጋቸው ከማይነግሯቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ  እውነቶች መካከል! 

 
የኦነግ የሃይማኖት ክንፍና የፕሮፓጋንዳ ጸሐፊው አሕመዲን ጀበል «ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከ615 1700 የጭቆናና የትግርል ታሪክ ቅጽ አንድ» በሚል በደረተው ድርሰቱ ያለ ተጨባጭ ማስረጃ በኢትዮጵያ ነገሥታ ተርታ ውስጥ ስሙ ስለማይገኘውና በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች የታሪክ ጽሑፎች ያልተመዘገበ፤ እንዲሁም  የአርኪዎሎጂ ማስረጃ ስለሌለው ነጃሺ ስለሚባል የፈጠራ ንጉሥ ከሰላሳ በላይ ገጾች አባክኖ ውዳሴ ሲደርስ  ስለ መልካም ስራቸው ብዙ ሳይደክም  ተጨባጭ የታሪክ ማስረጃ ስለሚያገኝባቸው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ ተግባራት ግን ተሳስቶ እንኳ ማውሳት አይፈልግም።  
 
ቁርዓንን ከአረብኛ ወደ አማርኛ ያስተረጎሙት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ናቸው። ለዚህም ማስረጃው የቁርዓን የአማርኛ ትርጉም መቅድም ላይ ይገኛል። ይህንን የቁርዓን መግቢያ ከታች አትሜዋለሁ። አሕመዲን ጀበል ያለ ተጨባጭ ማስረጃ ጸረ ሙስሊም አድርጎ ስማቸውን  የሚያጠፋቸው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ  ቁርኣንን ወደ አማርኛ በግል ገንዘባቸው እንዲተረጎም ከማረጋቸው በተጨማሪ መስጂድም ያሰሩ ነበር። ከታች የታተሙት ሁለት ሰነዶች ንጉሠ ነገሥቱ  ምጽዋ መስጂድ ለማሰራት የጣሉትን የመሰረት ድንጋይና የመሰረት ድንጋዩን ከጣሉ በኋላ የሰጡት ንግግር ነው። 
 
እነ አሕመዲን ጀበል በሃይማኖት ስም የሚደርቱትን ፕሮፓጋንዳ ለማጣራትና  በራሱ አስቦ ምርምሩ ወደሚወስደው ድምማዴ ለመድረስ  ፈቃደኛ ያልሆነው መንጋውም የተባለውን እየደገመ አባቶቹ  ከውጭ ጠላት ጋር  ተፋልመው  እንደገና ባቆሙት አገር ላይ ያምጻል።
Filed in: Amharic