>

የዘንድሮ ምርጫ (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

የዘንድሮ ምርጫ

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም
በታሰበው ምርጫ ላይ ያለው ንትርክ እንዲገባኝ መከርሁ፤ ምርጫው ይተላለፍ የሚሉት አንድ ምክንያት ይጠቅሳሉ፤ በአሁኑ ጊዜ ሰላምና መረጋጋት የለም ይላሉ፤ ይህ የማይካድ እውነት ነው፤ ነገር ግን እነዚሁ ሰዎች ከአንድ ወይም ከአምስት ዓመት በኋላ ሰላምና መረጋጋት ይመጣል ያላቸው ማን ነው? ከዚያም አልፎ ሊባባስ አይችልም ያላቸው ማን ነው? የዛሬው ሁኔታ ሁሉ እንዳለ ሆኖ ነገ ከዛሬ ሊሻል አይችልም፡፡
በአንጻሩ ምርጫው ዘንድሮ ይካሂድ የሚባልበት ምክንያት ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት ነው፤ ሰላምና መረጋጋት የሚመጣው በሕዝብ ድጋፍ የተመረጠና ሰላምንና መረጋጋትን ለማምጣት አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ የመውሰድ ሥልጣን ያለው መንግሥት ሲቋቋም ነው ይላሉ፡፡
እንዲህ ከሆነ ምርጫው ይተላለፍ የሚሉት ሌላ የማይናገሩት አሳማኝ ምክንያት ከሌላቸው ምርጫውን መቀበል ግዴታቸው ይሆናል፤ ሕዝቡን ባያደናብሩት መልካም ይመስለኛል፡፡
Filed in: Amharic