>

ህወሓት ከኦፌኮ ጋር ለመዋሃድ መግባባት ላይ መድረሱ ተገለፀ‼ (ጋዜጠኛ ደመቀ ነጋሳ)

ህወሓት ከኦፌኮ ጋር ለመዋሃድ መግባባት ላይ መድረሱ ተገለፀ‼

ጋዜጠኛ ደመቀ ነጋሳ
 
 ኦቦ በቀለ ገረባ ፍቃደኛ ሆነዋል‼
“አቶ ጌታቸዉ ረዳ ትናንት ማምሻውን ከድምፅ ወያኔ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ የህወሓት ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል ተብሎ ለተጠየቁት ጥያቄ ፌዴራሊስት ሃይሎችን እንቀላቀላለን በማለት በተለይ አዲሱ የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብን ለመቀላቀል ፍላጎት እንዳለዉ ገልፀዋል። በጉዳዩ እስካሁን የተወሰደ እርምጃ ካለ እንዲያብራሩ ተጠይቀው “በተደጋጋሚ ከኦፌኮዉ ተቀዳሚ ምክትል ሊ/ቀ ኦቦ በቀለ ገርባ ጋር ተነጋግረናል፤ ይሁንታንም አገኝተናል” ብለዋል። በቅርቡም የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ተሰብስቦ በጉዳዩ ከመከረ በኋላ በግልፅ ደብዳቤ ለፓርታዎቹ ጥያቄያዉን ሊያቀርብ እንደምችል ገልፀዋል።
Filed in: Amharic