>

ያመኑት ፈረስ ከፈሩት ፈረስ (መስፍን አረጋ)

ያመኑት ፈረስ ከፈሩት ፈረስ

 

መስፍን አረጋ 

 

እያረጋጋ በመለሳለስ

ያመኑት ፈረስ ጥሎ በደንደስ

ይረጋግጣል እስከሚጨርስ፡፡

 

በሌላ በኩል የፈሩት ፈረስ

እንቅስቃሴው ሳያሰኝ ደስ

ስለሚደረግ ልጓም እንዲነክስ፣

አልፎ ከመጣል በኩል በግላስ 

የከፋ ጉዳት ብዙም አያደርስ፡፡ 

 

ከኦነግ ፈረሶች ዐብይና ጃዋር

ጦቢያን የሚገላት ጥሎ ከኦዳ ሥር፣

ሳይሆን የተፈራው የአሩሲው ስናር

ያጋሮው ጮሌ ነው ያመነው ሙሉ አገር፡፡

 

ስለዚህ ወገኔ አማራው በተለይ

ያስጨንቀኛል ካልክ የሀገሬ ጉዳይ

ጃዋር ስላስካካ ወደ ጃዋር ሳታይ

ሙሉ ትኩረትህን አድርግ ባብይ ላይ፡፡ 

 

 

ኢሜል

                mesfin.arega@gmail.com

                   

Filed in: Amharic