የማሰብ፣ የመጻፍና የመናገር መብቱን በመጠቀም የብዙ መቶ ሺዎችን ፍቅርና ክብር ያገኘው ወጣቱ ፖለቲከኛና መምህር ኣብርሃ ደስታ በነገው ዕለት 8 ሰዓት ላይ በኣራዳ ፍርድ ቤት ይቀርባል። የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኅላፊ የሆነው አብርሀ ደስታ ከጁላይ 8 ቀን 2014 ጀምሮ ከኣንድ ወር በላይ በእስር መሆኑ ከመገለጹ ውጭ ማንም የቤተሰብ ኣባልም ሆነ ወዳጆቹ እንዲጎበኙት ኣልተደረገም።
በማህበራዊ ድረ-ገጾች (ፌስ ቡክና – ትዊተር) ይህን ወጣት ፖለቲከኛ የናፈቁ ሁሉ በነገው ዕለት ኣዲስ ኣበባ ኣራዳ ፍርድ ቤት በመሄድ ኣጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ እየተላለፈ መሆኑን በዚሁ ኣጋጣሚ እንገልጻለን።
ወጣቱ ፖለቲከኛና የዩንቨርስቲ መምህር ኣብርሃ ደስታ ጁላይ 8 ቀን መቀሌ ውስጥ በፖሊሶች እየተደበደበ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ተልኮ በማዕካላዊ ዕስር ቤት ተጨማሪ ድብደባ ሳይፈጸምበት እንዳልቀር የትግል አጋሮቹ ጥርጣሬያቸውን አሰምተው እንደነበር ኣይዘነጋም።