>

በተቃጠሉ መስጊዶች ስም ጸረ ክርስቲያን እንቅስቃሴ  የሚያደርጉ አሸባሪዎችን እንቃወማለን!! (ሀብታሙ አሰፋ/ሕብር ሬዲዮ)

በተቃጠሉ መስጊዶች ስም ጸረ ክርስቲያን እንቅስቃሴ  የሚያደርጉ አሸባሪዎችን እንቃወማለን!!

ሀብታሙ አሰፋ /ሕብር ሬዲዮ
የሞጣ የመስጊድ ጥቃትን ተከትሎ እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ ጥርጣሬን መጫር ከጀመረ ውሎ አድሯል።የሞጣው ቃጠሎ ምክንያት  በሰላም አብሮ የኖረውን ክርስቲያን እና ሙስሊም የማይወክል ድርጊት የጥቂቶች ድርጊት አድርጎ መቁጠር ይቻላል።ሁሉም ወገን ጥቃቱን አውግዟል።የክልሉ መንግሥት ተጠርጣመሪዎችን ይዙዋል።ገና እይዛለሁ ብሉዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን ባለሀብቶች ጭምር የፈረሰውን መስጊድ ለመስራት የበኩላቸውን ለማገዝ ቃል እስከ መግባት ደርሰዋል። የሁለቱም የሀይማኖት መሪዎች በጋራ ድርጊቱን ከማውገዝ አልፈው በጋራ ሕዝብ ሰብስበው አነጋግረዋል።ይህ ለቀጣይ ሰላም ትልቅ እርምጃ ነው።
በኦሮሚያ ክልል እነ አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ስልጣን ከያዙ ጀምሮ ተደጋጋሚ ጥቃት ቤተ ክርስቲያን ላይ እና ክርስቲያኖች ላይ ተፈጽሙዋል።በቅርቡ እንኩዋን ከአዲስ አበባ አራት ሰዓት የምትርቀው ዶዶላን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች፣በአዲስ አበባ ፣በድሬዳዋ እና በሐረር ተመሳሳይ ጥቃት ተፈጽሙዋል። 86 ንጹሃን ተገድለዋል። ይህ ተራ ግድያ ሳይሆን ክርስቲያኖች አሸባሪው አይስስ በሊቢያ ወገኖቻችን ላይ እንዳደረጉት በእምነታቸው እና በብሄራቸው ሳቢያ ታርደዋል።ስጋቸው ተቆራጡዋል።ቤተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል። ክቡር የሆነው የሰው ልጅ በገዛ አገሩ ይህ ግፍ ሲፈጸምበት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ለችግሩ ምክንያት የሆነውን ተከብቤያለሁ ክንውን ጃዋርን ለህግ ማቅረብ ቀርቶ ዝምታን መርጠው ቆይተው የጽሑፍ መግለጫ ሰጥተዋል። ብሄር ላይ ያተኮረ ዝርዝር የሟቾች መግለጫ ለራሳቸው የፖለቲካ ዓላማ የታሰበ ነው የሚል ተቃውሞ አስነስቱዋል።ይህ ሁሉ ሲሆን የሰሞኑ ዘመቻ አልነበረም። የመንግስትና የፓርቲ መገናኛ ብዙሃን በአንድ ላይ እንዲዘምቱ አልታዘዙም። ለምን!?
የሰሞኑ ዘመቻ ጥርጣሬ ያጭራል።ስለ ሞጣ መስጊዶች ቃጠሎ ገለልተኛ አካል ምርመራ ይጀምር። ኦሮሚያ ክልል ዛሬም ድረስ ማንነት እና ሀይማኖት ላይ ያደረገ ጥቃት አልቆመም።ነገር ግን በክልሉ ጣልቃ እንግባ፣ቤተ ክርስቲያን አፍርሰን መስጊድ እንሰራለን።አናቃጥለውም መስጊድ እናደርገዋለን፣መስጊድ ከሚፈርስ ኢትዮጵያ ይድረስ ሲባል መንግስት ነኝ የሚለው አካል የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል እንቅስቃሴ ዛሬም በአድልዎ እንዲቀጥል እና የለሁበትም ሊል ይሞክራል።
ትላንት በሻሸመኔ በክርስቲያኖች ንብረት ላይ የደረሰው ዝርፊያ፣ቃጠሎ፣በጅማ ቤት እስከ ማቃጠል የሄዱበት ድርጊት የሞጣውን አጋጣሚ ተጠቅሞ የሽብር ሀይል ከሁዋላው የሚገፋው በአጠቃላይ ጸረ ክርስቲያን እንቅስቅሴ እና ቅስቀሳ ተጠናክሮ ቀጥሉዋል። ይህ የሽብር ቡድን ሰይፍ ይዞ፣የአረብ አግራትን ባንዲራ አንግቦ ሰልፍ በአንድ ሉዓላዊት አገር ሲያደርግ ለመስቀል በዓል ዜጎችን በገዛ አገራቸው ኮከብ የሌለበትን ባንዲራ ሲያስፈታ የነበረ መንግስት አላየም ማለት አይቻልም።ያያል። በቅርቡ በኦሮሚያ የተካሄደው የሽብር ጭፍጨፋ የክልሉ የጸጥታና የአስተዳደር መዋቅር ባይኖረው ኖሮ ይህን ያህል ጥፋት ባልደረሰ። ዛሬም መንግስት ቆሞ እያየ ሊቆጣጠረው የማይችል የሀይማኖት ግጭት የሚጋብዝ ቅስቀሳና እንቅስቅሴ ሲደረግ ቆሞ እየተመለከተ ነው። ይህን ማንም ሊታገሰው አይችልም።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ክርስቲያን ሙስሊሙ በሰላም ተከባብሮ ኖሯል።ነገም ይኖራል ይህን ሰላማዊ ግንኙነት የተለያዩ ወገኖች ግጭትን በማስነሳት ለራሳቸው ዓላማ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል።ምርጫ ለማራዘም የሚፈልግ ዜጎችን የግድ እስኪጫረሱ መጠበቅ የለበትም። እስላማዊ መንግስት በጉልበት እመሰርታለሁ የሚል ኃይልን መንግስት ከጀርባ የሚገፉ ባለስልጣናትን ተው የማይል ከሆነ ይህ እሳት አንዱን አንድም ሌላው የሚተው አይደለም እና ዛሬም ወደ ልቦናው መመለስ የማይፈልገውን ሀይል ሳይሆን የመንግሥትን ስልጣን የያዘው ሀይል ከአድልዎ እና ክፕተራ የፖለቲካ ንግድ ወጥቶ የአገሪቱን ዘላቂ ሰላም የሚያናጉ የሞጣውን የመስጊዶች ቃጠሎ ምክንያት ያደረጉ ህገ ወጥ ቅስቀሳዎች እና ግጭት ቀስቃሽ እርምጃዎች ገደብ ሊያሲዝ ይገባል ለማለት እንወዳለን።
ዛሬም በኦሮሚያ ክልል እና በሌሎቹ ከተሞች ሀይማኖት እና ብሄር ላይ መሰረት ባደረገ ጥቃት የሞቱ ዜጎች ጉዳይ ፍትህ ይፈልጋል።ፍትህ አልተገኘም።የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናት አልተሰሩም።ክልሉ ተጨማሪ ግጭት ለማስነሳት እየተሞከረበት ነው። ስለዚህ ሁሉም ሰላም ወዳድ ወገን በአግር ውስጥ እና በውጭ ለክርስትና እምነት ተከታዮች የተከለከለ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲፈቀድ እና ክርስቲያኖች ላይ ያነጣጠረ  ቅስቀሳ እንዲቆም፣ገዳዮች እና አስገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ፣በሞጣው መስጊድ ቃጠሎ ተጠርጣሪዎች እንደተያዙት ቤተ ክርስቲያንም ያቃጠሉ፣ክርስቲያኖችን ያረዱ፣በድንጋይ እና ዱላ ወግረው የገደሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ ፈጣን ዘመቻ በማድረግ ድምጽ ማሰማት አለባቸው።
የሀይማኖት እኩልነት ይኑር በሀይማኖት ሽፋን የሚደረግ እንቅስቅሴ ህጋዊ እና የሌላውን መብት ያከበረ እንዲሆን የመጠበቅ የመንግስት ሀላፊነት መሆኑን ማስታወስ እንወዳለን።
ሕብር ሬዲዮ(ሕብር ሬዲዮ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በፌስ ቡክ ስርጭቱ እንዲገታ ተደርጉዋል።ለጻፍነው ምላሽ እየጠበቅን ነው።ከቀናት በሁዋላ በይፋ ተቃውሟችንን እንጀምራለን። 
Filed in: Amharic