>

አዲስ አበባ በፋሽስት ወያኔና በናዚ ኦነግ ዘመን በግማሽ ጠበበች እንጂ ፈጽሞ አልሰፋችም! (አቻምየለህ ታምሩ)

አዲስ አበባ በፋሽስት ወያኔና በናዚ ኦነግ ዘመን በግማሽ ጠበበች እንጂ ፈጽሞ አልሰፋችም!

አቻምየለህ ታምሩ
ከታች የታተመው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ካርታ የደርግ አገዛዝ  መጋቢት 6 ቀን 1968 ዓ.ም. በነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 25 ላይ ያወጣው የወቅቱን የአዲስ አበባ ከተማ ስፋት የሚያሳይ ካርታ ነው። ካርታው የታተመው የአዲስ አበባ ከተማ ካርታ የከተማ ቦታ የኪራይና የከተማ ቤት ግብር አዋጅ ቁጥር 80/1968 ዓ.ም.ን ለመደንገግ ከመጣው አዋጅ ጋር ነው።
ከታች የታተመውን የአዲስ አበባ ካርታና አዋጁን ፈርሞ በነጋሪ ጋዜጣ መጋቢት 6 ቀን 1968 ዓ.ም. እንዲወጣ ያደረገው የአዲስ አበባ ከንቲባ መኮንን ሙላት ይባላል። በአዋጁ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ የወቅቱ ስፋት 122,000 ሄክታር ነው።  ይህ የአዲስ አበባ ካርታ በቀዳማዊ ኃይለ ዘመነ መንግሥት ከነበረው የአዲስ አበባ ስፋት ጋር አንድ አይነት ነው። በፋሽስት ወያኔና በናዚ ኦነግ  ዘመን ግን የአዲስ አበባ ከተማ ስፋት 54,000 ሄክታር እንደሆነ ልብ ይሏል። ይታያችሁ! ኦነጋውያን አዲስ  አበባን ሰፋች የሚሉት በግማሽ የጠበበችውን  54,000 ሄክታሩን ነው።
ከካርታው ላይ በግልጽ እንደሚታየው በፋሽስት ወያኔና በናዚ ኦነግ ዘመን «ኦሮምያ» በሚል የተፈጠረው ክልል አንድ ዞን የተደረገው «ፊንፊኔ ልዩ ዞን» አካል የሆነው ገፈርሳ በ1968 ዓ.ም.  በወጣው አዋጅ የአዲስ አበባ ከተማ አንዱ ክፍለ ከተማ ነበር። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመንም እንደዚያ ነበር። «የፊንፊኔ ልዩ ዞን» ተብሎ ኦሮምያ ክልል ውስጥ የተካተተው መሬት የአዲስ አበባ ክፍል ነበር።
ኦነጋውያን ከሰሞኑ “የፊንፊኔ ከተማና የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ከምርጫው በፊት ምላሽ ማግኘት አለበት” በማለት በጃዋር ቴሌቭዥን ያለማቋረጥ እየቀሰቀሱ ናቸው። አዎ የአዲስ አበባ ከተማ ወደ ቀድሞው ይዞታው መመለስ ይኖርበታል። አዲስ አበባ  በፋሽስት ወያኔና በናዚ  ኦነግ ዘመን የተወሰደባትን ገፈርሳ ክፍለ ከተማና የተቀሩት  ከአዲስ አበባ ተወስደው «የፊንፊኔ ልዩ ዞን» የተደረጉት ክፍለ ከተሞቿ  በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና  በደርግ ዘመን እንደነበረው ተመልሰው የከተማዋ አካል መሆን አለባቸው። በሚቀጥለው ጽሑፌ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የነበረውን  የአዲስ አበባ ስፋትና ክፍለ ከተሞቿን አቀርባለሁ።
Filed in: Amharic