>
5:13 pm - Wednesday April 18, 4610

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የተሰጠ መግለጫ!!!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የተሰጠ መግለጫ!!!

 
ከእንደዚህ ዓይነቱ አጋጣሚ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየሞከሩ የሚገኙ ኃይሎች ከዚህ ኃላፊነት ከጎደለው አካሄድ እንዲታቀቡ አጥብቀን እናሳስባለን!!!
ትላንት በሞጣ ከተማ በእምነት ተቋማት ላይ በደረሰው ጥቃት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።
በእምነት ተቋማት ላይ የሚደርስ ጥቃት በምንም ምክንያት ተቀባይነት የሌለው እና ጥቃቱ በየትኛውም የእምነት ተቋም ላይ ሲደርስ ሁሉም ማኅበረሰብ በአንድነት ቆሞ ሊያወግዘው የሚገባ ተግባር ነው።
መንግሥት በእምነት ተቋማት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ጨርሶ ሊታገስ አይገባም። በእምነት ተቋማት ላይ የሚፈፀም ጥቃት የዜጎች የእምነት ነፃነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሰፍን የምንፈልገው ሀገራዊ መረጋጋት እና ሰላም ላይ ከፍተኛ እንቅፋት የሚፈጥር የወንጀል ድርጊት መሆኑን በመረዳት መንግሥት በአጥፊዎች ላይ ተገቢውን የህግ እርምጃ መወሰድ አለበት።
ከእንደዚህ ዓይነቱ አጋጣሚ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየሞከሩ የሚገኙ ኃይሎች ከዚህ ኃላፊነት ከጎደለው አካሄድ እንዲታቀቡ አጥብቀን እናሳስባለን።
መንግሥት ትላንት በሞጣ የተፈፀመው ዓይነት ጥቃት በድንገት የሚከሰት አለመሆኑን በመረዳት ለወደፊቱ እንዲህ ዓይነት ጥፋት ከመከሰቱ አስቀድሞ መከላከል የሚቻልበት አቅም መፍጠር ላይ አትኩሮት አድርጎ መሥራት ይገባዋል።
የአጥፊዎቹ ድርጊት በከተማው የሚኖሩ የሁለቱን እምነት ተከታዮች ለዘመናት በሰላም አብሮ በመኖር ያላቸውን ታሪክ በፍጹም የማይገልፅ ቢሆንም፣ በደረሰው ጥፋት ምክንያት ወደፊት በዜጎች መሀከል የሚኖረው ግንኙነት ላይ ሊፈጠር የሚችለውን መቃቃር የሞጣ ከተማ ነዋሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች አና የከተማው አስተዳደር የከተማው ሕዝብን በማረጋጋት፣ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀትና እና አጥፊዎችን አጋልጦ በመስጠት የማያዳግም መፍትሄ ሊያስቀመጡ ይገባቸዋል።
የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት
Filed in: Amharic