>

ሌላውን "ነፍጠኛ" ሲሉ ራሳቸውን "ወራሪዎች" እያሉ  መሆኑን የማያውቁቱ ግብዞቹ ኦነጋውያን!  (አቻምየለህ ታምሩ)

ሌላውን “ነፍጠኛ” ሲሉ ራሳቸውን “ወራሪዎች” እያሉ  መሆኑን የማያውቁቱ ግብዞቹ ኦነጋውያን!  
አቻምየለህ ታምሩ
ራሳቸውን «ዐሊሙ ነፍጠኛ» በማለት ይጠሩ የነበሩት የዐፄ ዮሐንስ ልጆች ነን የሚሉን  የትግራይ ብሔርተኞች ናቸው እንግዲህ  አማራውን የሰደቡ እየመሰላቸው «ዐሊሙ ነፍጠኛ»  ብለው ራሳቸው የሚጠሩትን ዐፄ ዮሐንስን ጭምር  እየሰደቡ ራሳቸውን ነው ሲያዋርዱ የሚውሉት!
—-
ነፍጠኛ  የተነጠቀውን ርስቱን ለማስመለስ፣ በወራሪ የተቀማውን ባድማውን ለማስከበርና አገሩን ለመጠበቅ የተሰማራ አርበኛ ማለት ነው። አማራውን የሰደቡ እየመሰላቸው ነፍጠኛ ሲሉ የሚውሉት ኦነጋውያን አማራው ነፍጠኛ የሆነው የተነጠቀውን ርስቱን ለማስመለስ የተቀማውን ባድማ ለማስከበርና አገሩን ለመጠበቅ መሆኑን እየመሰከሩለት ነው።
በሌላ አነጋገር  አማራ ርስቱን ለማስመለስ፣ ባድማውን ለማስከበርና አገሩን ለመጠበቅ የዘመተ ነፍጠኛ ሲሆን የሰደቡት እየመሰላቸው ነፍጠኛ  የሚሉት ደግሞ ከርስቱ ያፈለሱት፣ ባድማውን የወሰዱበትና አገሩን የወረሩበት መሆናቸውን  በራሳቸው ላይ እየመሰከሩ ነው።ይህን የማያውቁ ግብዞቹ ኦነጋውያን ግን አማራውን የሰደብን እየመሰላቸው  «ነፍጠኛ» እያሉ ራሳቸውን ወራሪ ሲያደርጉ ይውላሉ።
ከምንም በላይ የሚገርመኝ የትግራይ ብሔርተኞች ነገር ነው። የትግራይ ብሔርተኞች «የትግራይ ሜዲያ ሐውስ» በሚል ባቋቋሙት ዝቅተኛውን የጋዜጠኛነት ሞያ በማያሟሉ  የፕሮፓጋንዳ  ካድሬዎች የሚዘወር  የጥላቻ ጣቢያቸው ላይ ከሰሞኑ አንዱን በአማራ ጥላቻ ጨጓራው የተቃጠለ ሽማግሌ ኦነጋዊ  አቅርበው «ነፍጠኞችን ተባብረን እናጥፋቸው»  እየተባባሉ ሲመካከሩ ነበር። የትግራይ ብሔርተኞቹ ኦነጋዊውን አቅርበው «ነፍጠኞችን ተባብረን እናጥፋቸው» እያለ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንዲከፍት ስፖንሰር ሲያደርጉ የታያቸው አማራውን የሰደበላቸው የመሰላቸውን ነገር ብቻ  እንጂ በራሳቸውም ላይ የዘር ማጥፋት እያወጀባቸው መሆኑን ግብዞች ስለሆኑ ሊታያቸው አልቻለም። ይህን ያለው አማራ ቢሆን ኖሮ አገር ይያዝ ይሉ ነበር።
የትግራይ ብሔርተኞች ሁሉ እንደሚኮሩባቸው የሚነግሩን ዐፄ ዮሐንስ  ነፍጠኛ ብቻ ሳይሆኑ ራሳቸውን «ዐሉሙ ነፍጠኛ» እያሉ የሚጠሩ የነፍጠኞች ነፍጠኛ ነበሩ። በፕሮፓጋንዳ ሳጥናቸው በአማራ ጥላቻ ጨጓራቸው የተቃጠሉ ኦነጋውያንን እያቀረቡ «ነፍጠኞችን ተባብረን እናጥፋቸው» ሲያስብሉ የሚውሉት የትግራይ ብሔርተኞች እንደሚኮሩባቸውና  አባታችን ናቸው በሚሏቸው በዐፄ ዮሐንስና በዐፄ ዮሐንስ ልጆች ወይም በራሳቸው ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱ ወጣቶቹ ብሔርተኞች ጭምር  የፋሽስት ወያኔን የአጥፍቶ መጥፋት  አደገኛ  መንገድ እየተከተሉ ይገኛሉ።
ዐፄ ዮሐንስ ራሳቸውን «ዐሊሙ ነፍጠኛ» ሲሉ የጠሩት  ወሎ የተነሱባቸውን ከወጉ በኋላ የጎጃሙ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ከሸዋው ምኒልክ ጋር ዶልተውብኛል ብለው ስላሰቡ ጎጃምን አጥፍተው ጨርሰው በስተመጨረሻ ዳግማዊ ምኒልክን ለመውጋት ወደ ሸዋ ለዘመቻ ሲነሱ ከዘመቻቸው በፊት ለንጉሥ ምኒልክ በላኩት ደብዳቤ ውስጥ ባሰፈሩት የማስፈራሪያ ግጥም  ነበር። የላኩት ግጥም እንዲህ የሚል ነበር፤
እርሳሱ ብዙ ነው የኅምሌ ቴግብ፣
ድንጋይን መንከስ ነው በዝብዝን ማሰብ፤
ከላይ የወረደው ከጽዮን መቅደስ፣
ባባቱ ሚካኤል በናቱ ሥላስ፣
አጨደው ከመረው ያን ያሕዝብ ገብስ፣
ወጋው ደበደበው ሰጠው ለነፋስ፣
ዐሊሙ ነፍጠኛ ዐፄ ዮሐንስ።
ራሳቸውን «ዐሊሙ ነፍጠኛ» በማለት ይጠሩ የነበሩት የዐፄ ዮሐንስ ልጆች ነን የሚሉን  የትግራይ ብሔርተኞች ናቸው እንግዲህ  አማራውን የሰደቡ እየመሰላቸው «ዐሊሙ ነፍጠኛ»  ብለው ራሳቸው የሚጠሩትን ዐፄ ዮሐንስን ጭምር  እየሰደቡ ራሳቸውን ሲያዋርዱ የሚውሉት! ጉዶች!
Filed in: Amharic