>

የኢትዮጵያ ታሪክ ወይስ የኦሮሞ ተረት? | አዲሱ የታሪክ ሰነድ !!! (አያሌው መንበር)

የኢትዮጵያ ታሪክ ወይስ የኦሮሞ ተረት? | አዲሱ የታሪክ ሰነድ !

 

አያሌው መንበር
የኢትዮጵያ ታሪክ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንደ “ኮመን ኮርስ” ለሁሉም ተማሪ ይሰጥ ተብሎ ነበር። ለኮርሱ ማስተማርያ ሰነድ ይዘጋጅ ተብሎ ምሁራን ሲመረጡ ግን ቁማሩ ግልፅ ሆነ። 3 PhD ያላቸው የኦሮሞ ብሄርተኞች እና 1 ጀማሪ የደብረ ታቦር ዩ. መምህር እንዲያዘጋጁት ተደረገ። በመሰረቱ በታሪክ ከፍተኛ ዕውቀት ያላቸው ፕሮፌሰሮች እያሉ (እንደ ባህሩ ዘውዴ፣ ኃይሌ ላሬቦ ወዘተ) ለምን ስማቸውን በውጤታማ የታሪክ ምርምር ስራ ሰምተናቸው የማናውቃቸው ሰዎች ተመረጡ? ከአማራ ምሁራንስ ፕሮፌሰሮች ጠፍተው ነው አንድ ማስተርሱን  በቅርቡ ያገኘ ወጣት ከ3ቱ ኦሮሞዎች ጋር “እንዲሰራ” የተላከው? ኧረ ለመሆኑ ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ዘርፍ ገና አንድ ተማሪ ሳያስመርቅ ለምን ውክልና ተሰጠው? ወይስ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተከፈተውን  የታሪክ ት/ክፍል ኃላፊ የሚመራው የጅማ ተወላጅ ኦሮሞ መሆኑን ስላወቁ ነው?
ነገሩ ሁሉ ሴራ መሆኑ የሚገለጥልን ይህን ሰነድ ገልጠን ስናነብ ነው! አጠቃላይ ኢትዮጵያን የሚያዋርድ ኦሮሞን በሀሰት ትርክት ሰማይ የሚሰቅል ነው። እንደ አክሱም፣ ዛግዌ፣ ዳማትና የሰሎሞናዊ ስርወ መንግስታትን “ፖሊቲስ” በሚል ርእስ ስር አስፍሮ ተራ የጎሳ አደረጃጀት አስመስሏቸዋል። ራሳቸውን ችለው በምዕራፍ መቀመጥ ሲገባቸው አንድ ገፅ ተኩል እየሰጠ ያልፋል:: ለአክሱም ሁለት ገፅ ያልሞላ ሽፋን የማይሰጠው ሠነድ ለገዳ ግን ዘጠኝ ገፆችን ይሸልማል! የኦሮሞ ገዳ ስርዓት 9ሺ ዓመቱ ነው ሲል ማስረጃ የለሽ ተረቱን ይዘበዝባል።
ስለሌላው ህዝብ ቁብ የለውም፡፡  እነ ቢዛሞን እና እነርያን ኦሮሞ እንዳጠፋቸው እያወቀ ክርስትያን ኪንግደም አወደማቸው ይላል።
እንደ ኽምራ ያሉ ህዝቦችን ታምታንጋ የሚል የፈጠራ ስም ይሰጣል።  ባጭሩ የኦሮሞን ተረት በኢትዮጵያ ላይ ለመጫን ያደረገውን ጥረት በሚከተለው ቁጥር መግለፅ ይቻላል፦
በሠነዱ የተጠቀሱ ስሞች ብዛት፦
ኦሮሞ 122 ጊዜ ተጠቅሷል
ሶማሊ 56  ” “
ትግራይ 33 ” “
ሲዳማ 20 ” “
አማራ 16 ” ” !
ከዚህ የባሰ ፈጣጣነት አለ ወይ!?
 የአማራ ምሁራን በፍፁም ይህን መቀበል የለባቸውም! ምሁራኑ ባርነት ቢመርጡ እንኳ ተማሪ በጭራሽ ሊቀበለው አይገባም!
ለማንኛውም ነገ ረቡዕ ታህሳስ 2012 ዓ.ም የአማራ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በዚህ ጉዳይ ስብሰባ ጠርቷል። ውሳኔው ይህን ሰነድ ውድቅ የሚያደርግ እንደሚሆን እንጠብቃለን።  ካልሆነ ህዝባዊ ትግል ይጠራል! ወይ ሰነዱ ይስተካከል፤ አልያ ይቀራል።
አፄ ቴዎድሮስ ራሳቸውን ማጥፋታቸው  እንኳ የማይቀበል ሰነድ እኛም እንቀበልም! ጭራሽ የምንሊክ፣ የዮሀንስና የቴድሮስ ምስል እንኳ እንዲታይ አይፈቅዱም! ድሬ ሸክ ሁሴን ብለው የባሌውን ቅርስ ፎቶ ለጥፈው የትግራዩን አልነጃሽና ፋሲል ግንብ አልያ ላሊበላን ማሳየት አይሹም!
ባጭሩ ድፍረት ነው! የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የአማራ ህዝን ይህን አይነቱን አይን ያወጣ ድርሰት በቀላሉ አይመለከተውም!
Filed in: Amharic