>

ጌታቸው ረዳ የጠራውን ስብሰባ የትግራይ ወጣቶች ረግጠው ወጡ! (ብሩክ አበጋዝ)

ጌታቸው ረዳ የጠራውን ስብሰባ የትግራይ ወጣቶች ረግጠው ወጡ!

ብሩክ አበጋዝ
በመቀለ ከተማ የትግራይ ወጣቶች ህብረት አባላትን፣ በወቅቱ የትህነግ አቋም ላይ ለማወያየት አቶ ጌታቸው ረዳ ስብሰባ ጠርተው የነበረ ሲሆን፤ የመደመር ፍልስፍናን ና በብልፅግና ፓርቲን መቀላቀልን አስመልክቶ ትህነግ/ህወሃት የማይቀበለው መሆኑን ና አስፈላጊ ከሆነም ሉአላዊት ትግራይን እስከመመስረት እርምጃ ለመውሰድ መወሰኑን አስመልክተው እየተናገሩ ባሉበት፣ የስብሰባው ታዳሚ ወጣቶች አቶ ጌታቸው ኃሳባቸውን ሳይጨርሱ የተቃውሞ ድምፅ አሰምተዋል። አቶ ጌታቸውም “ልዩነት ካላችሁ እባካችሁ ተረጋጉና እንነጋገርበት ብለው እየተማፀኑ ባሉበት፤ ከተሰብሳቢ ወጣቶች መካከል #ክፍሎም_አብርሃ የተባለ ወጣት ከመድረኩም ሳያስፈቅድ ንግግር አደድርጓል።
.
“የትግራይ ህዝብ ወልዶ፣ አዝሎ አሳድጓችሁ ለአካለ መጠን አደረሳችሁ። እናንተ ግን ውለታውን ከመክፈል ይልቅ ዞር ብላችሁ ሳታዩት በህዝቡ ስም ስትነግዱ ኖራችሁ፤ዛሬ ቀን ሲጨልምባችሁ ለሰራችሁት ወንጀል መደበቂያ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አለያይታችሁ ለመኖር 27 ዓመት የዋሻችሁን ሳያንስ፤ ዛሬም የእናንተ አምላኪ ልታደርጉን አትችሉም! እኛ የትግራይ ህዝቦች የህወሃት አሻንጉሊት ሆነን የምንቀጥልበት ጊዜ አብቅቷል! እናንተ በሰራችሁት ግፍ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አቆራርጣችሁ ባርያችሁ ልታደርጉን አትችሉም! በቅርቡ እንኳን፤ በባህርዳር ስታዲየም በ70 እንደርታና በባህርዳር ከነማ ጨዋታ ጊዜ የባህርዳር ህዝብ ለትግራይ ህዝብ ያለውን ፍቅርና ክብር በአይናችን አይተናል። እዚህ እናንተ የምትሉንና እዚያ ያለው ነገር እጅግ የማይገናኝ የውሸት ጉዞ እንደነበር አረጋግጠናል።” ወጣት ክፍሎም አብረሃ
 .
ወጣት ክፍሎም ንግግሩን ሲጨርስ አደራሹን ለቅቆ የወጣ ሲሆን፣ ሌሎች ተሰብሳቢ ወጣቶችም ተከትለውት ስብሰባውን ረግጠው በመውጣታቸው አቶ ጌታቸው ረዳ ባዶ አዳራሽ ታቅፎ መቅረቱ ታውቋል!!
Filed in: Amharic