>

ወያኔ የወጋቻቸው የበታችነት እሾህ በቀላሉ አይነቀልም! (ታየ ቦጋለ አረጋ)

ወያኔ የወጋቻቸው የበታችነት እሾህ በቀላሉ አይነቀልም!

ታየ ቦጋለ አረጋ (ኢልመ ደሱ ኦዳ)
“ምኒልክ አኖሌ ላይ ጡት አስቆረጡ፤ ጨለንቆ ላይ ተዋጉ” ይላሉ።  መቼ?! ከዛሬ 133 ወዮም 132  ዓመት በፊት (ክርክሩን እናቆየውና ፊታቸው ላይ አሁን ወያኔ ምን አደረገ?)
“Short Memory”
*
ያውልህ ወያኔ የሠራው (ኮፒ ፔስት እያደረጋችሁ ለጥፉት። ዲጂታል ወያኔዎች ሰሞኑን ተፅፈው የተሰጧቸውን ኮመንቶች ኮፒ ፔስት እያደረጉ ፌስቡክን ወረውታል። መልስ ብትሰጧቸው ድጋሚ መፃፍና ማንበብ እንኳን አይችሉም።)
ወያኔ ትህነግ፦
1. በ1980ዎቹ መጀመሪያ የኦነግን ሠራዊት ክዶ ካምፕ አስገብቶ ቁልፍ ሰዎቹን ፈጀ።
2. የኦነግ ታጋዮች ያላቸውን አስርቦና አዋርዶ “የሳራ በረሀ ምሥጢር” በሚል ፌክ ዶኩመንተሪ ሠራና ኢትዮጵያ ቴሌቪዢን (ኢቢሲ) ላይ ለቀቀ።
3. በማጎሪያ ካምፕ ውስጥ በርካታ የኦሮሞ ወንዶችን በግብረ ሰዶም አስገድዶ ደፈረ። (ሴቶችን አሰቃይቶ ደፈረ።)
4. አርቲስት ኤቢሳ አዱኛን ከነህይወቱ ከመኪና ኋላ አስሮ ጎትቶ ገደለ።
5. የደምቢ ዶሎዋን እናት ልጇን ገድሎ = ልጇ አስከሬን ላይ በግፍ እንድትቀመጥ አደረገ።
6. የኢሬቻን ከ800 በላይ ሰው እልቂትና ከጉድጓድና ጭቃ ውስጥ እየጎተቱ ሲያወጡ በዐይናችሁ ዐይታችኋል።
7. ሞያሌ በጠራራ ፀሐይ ‘ኦነግ ገባ ሲሉ ሰምተን ነው’ ብሎ አስራአንድ ንፁሓንን ሲገድል ዐይታችኋል።
8. የአምቦ እናት 27 ዓመታት ሙሉ እንዴት ልጆቿ በግፍ እንደተገደሉ… መላዋ ኦሮሚያ በየከተሞቹ ማልቀሷን
9. እግሩ የተቆረጠውን የሱሉልታ ልጅ
10. የፕሮፌሰር መረራ ጉዲናና በቀለ ገርባ (ሺህዎች) ኦሮሞዎች እንደ ውሻ በሰንሰለት መታሠርና የኦሮሞ የእስር ቤት ሰቆቃ (አሸባሪ ኦነግ ተብለው)
11. መላዋ ኦሮሚያ ደም ዕንባ ማልቀሷ
12. የኦሮሞ ገበሬዎች ከመሬታቸው መፈናቀል።
13. የኦሮሞ ሀብት በግፍ መዘረፍ…
14. እንደ ሀገር የደረሱ ሺህ በደሎች ፊታችሁ ላይ ተገሽረው…
*
አማራ በአንፃሩ፦
1. “የፈሰሰው የኦሮሞ ደም የእኔ ነው!” ብሎ በአንድ ቀን ባህርዳር ውስጥ ብቻ 59 ሰው በስናይፐር ህይወቱን አጥቶ፤ የአንተን ትግል በመደገፍና ለራሱ ነፃነት ጭምር ተሰውቶ…
2. “በቀለ ገርባ መሪያችን ነው!” ብሎ መፈክር አንግቦ አደባባይ ወጥቶ – ሞቶ
3. የኦሮማራን ትግል አቀጣጥሎ
4. ከፕሮፌሰር አሥራት ጀምሮ እስከ ህፃን ድረስ እንዳንተው ተሰውቶ
5. ከ1983 ጀምሮ በአማራ ላይ የደረሰውን ሰቆቃ ሙሉቀን ተስፋው በመፅሐፉ፤
እኔም ‘መራራ እውነት በኢትዮጵያ ታሪክ’ በሚለው መፅሐፌ ስለተነተንኩት አንብበው። (ከአንተ በላይ አማራው ዋጋ ከፍሏል።)
*
በመሆኑም፦ ስትፈልግ ነፍጠኛ ቢሻህ አማራ በለኝ፤ የኮምፒውተር ቺፕስ የፈለሰፍህ መሰለህ? አንግሎ ሳክሶን ነኝ አላልኩም። ማነህና ለታየ ማንነት ዛሬ ትመድባለህ?
የእኔን ማንነት ኩሽናህ ውስጥ አስቀምጥና የእኔን እውነት ስማ!!! (ተደብቄ ማንነቴን አልፅፍም። እየከፈልክ አስወራ። ከ520 ያላነሱ ኦሮሞ ቤተሰቦቼን ቀቅለህ አትበላቸውም።)
*
የአፄ ዮሐንስን 30,000 ሙስሊም ወሎ ውስጥ መጨፍጨፍ ትንፍሽ ማለት አትፈልግም። የ17,000 ጎጃሜ ደም ለአንተ አይሰማህም። ለአክሱም ሙስሊሞች መብት ቅንጣት አትጮህም። የአማራ ሂንቁፍቱ ገደል፤ አርባ ጉጉ ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ጡት መቆረጥ፤ አሁንም በቅርቡ ስለሆነው ትንፍሽ አትልም። መኪና ውስጥ የውጭ ዜጋ ጨምሮ ስለመቃጠሉ፤ ሻሸመኔ ሰው ተዘቅዝቆ ስለመሰቀሉ፤ ጋሞዎች በግፍ ስለመገደላቸው፤ ስለ 36 የኦዴፓ አመራሮች መገደል፤ ስለ 17 ባንክ ዝርፊያ፤ ስለመስጊድና ቤተክርስቲያኖች መቃጠል፤ ስለ 86 ንፁሓን ህልፈት… ትንፍሽ አትልም።
ታክቲክ መሆኑ ነው? ሁለት ወይም ሦስት ሰው ሞተ ብለህ እሪ ያዙኝ ልቀቁኝ ትላለህ። የአንድም ሰው ህይወት ያሳዝናል። እንዳንተ ግን ዝሆን የሚያኽል ነውር ደብቄ፤ የሌላውን በበታችነት አላጎላም።
ወደ ህሊናህ ተመለስ!!!!
በምኒልክ “ጥፋት” ዛሬ ለማን ካሳ ይሰጥ?!
ማን ይጠየቅ?!
ስለመቆራረጡ ስለመመዳመዱማ ያየነውን ጭምር ማውራት እንችላለን። ያውም አንተ ዘር ለመተካት = የሌላውን የሰው ዘር እስከወዲያኛው ስለማምከንህ…
እውነት መዋጥ ለማይፈልጉ ይመራል። ዋጠው!!!
Filed in: Amharic