>

የኖቤል ሽልማቱ እንደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ (አልይ እንድሬ)

የኖቤል ሽልማቱ እንደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ

 

አልይ እንድሬ

 

ኢትዮጲያ ከምትታወቅባቸው አንኳር የታሪክ ገፆች ውስጥ አንደኛው ከአውሮፓ ቅኝ ገዥ ሃይሎች ጋር ተፋልማ ነፃነተዋን አስከብራ የኖረች የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት የሆነች አገር መሆኗ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በተፈጥሮ የታደለች የቀደምት ስልጣኔ ማማ የነበረች ሀገር መሆኗ ነው፡፡ 

      ኢትዮጲያ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ ከዓለም ሀያላን አገሮች መካከል አንዷ የነበረችበትና ከምስራቅና ምዕራብ አረቢያን አገሮች ጋር  ከፍተኛ የባህር ላይ ንግድ ታካሂድ የነበረችበት ዘመን ሲሆን የኢትዮጲያውያን የስነ ህንፃ ጥበብ ቀደምት ስልጣኔ ማሳያ የሆነው የአክሱም ሀውልት የታነፀውም በዚያ ዘመን እንደነበር  መዛግብት ይጠቁማሉ፡፡ ቀደምት አገራችን ኢትዮጲያ በኪነ ጥበብም ሆነ በኢኮኖሚ የተሻለች እንደነበረች የሚያመላክቱ ብዙ ፍንጮች አሉ፡፡ ዛሬ ራሳቸውን እንኳን መመገብ ተስኗቸው በድህነታቸው የዓለም ጭራ ከሆኑ አገሮች ተርታ የምትጠቀሰው አገራችን ኢትዮጲያ  በአንድ ወቅት በጃፓን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ለደረሰው ጉዳት በኢኮኖሚ ደካማ የነበረችው የዛንጊዜይቱ ጃፓን ችግሩን መቋቋም ተስኗት ስለነበር አገሮች ለጃፓን ህዝብ ርዳታ ሲያደርጉ ኢትዮጲያም 7 ሺህ ፓውንድ ለጃፓን ረድታ እንደነበር ተዘግቧል (“ጃፓን እንደምን ሰለጠነች “ ገፅ 36). ከዛን ጊዜ ወዲህ  በኢትዮጲያና በጃፓን መካከል ያለው የእድገትና ስልጣኔ ርምጃ እጅግ የተራራቀ በመሆኑ ምክንያት ዛሬ በጃፓንና በኢትዮጲያ መካከል ያለው የኢከኖሚ ልዩነት የት እየሌሌ ነው፡፡  

      እንግዲህ ነገሬን ላሳጥር፣  የላሊበላ ፍልፍል አቢያተ ክርስቲያናትን፣የጎንደር ፋሲለደስን፣ የአክሱም ሀውልትን ካነፁትና፣ “ፖለቲካና ታሪክ አበቃ በአፍሪካ ውስጥ ታላቅ የተወላጆች ኃይል  መነሳቱ ታወቀ፡፡ የአፍሪካ ጥቁር ህዝቦች ታሪክ ተለወጠ፡፡ ጥቁር ዓለም በአውሮፓውያን ላይ ሲያምፅና ሲያሸንፍ የመጀመሪያው ሆነ፡፡ የነጮችን የቅኝ ግዛት መስፋፋትና ቅዠት፣ የኃያላኑን አገሮች ፍላጎት አድዋ ዘጋው፡፡ በማለት በርክሌይ የተባለው አውሮፓዊ ፀሃፊ የኢትዮያውያንን የእምነት ጥንካሬና ጀግንነት ስለ አድዋ ውሎው በፃፈው ማስታወሻው ላይ ያሰፈረውንና የተደነቀበትን“የአድዋን ድል በማጎናፀፍ የአፍሪካ ፈርጥ እንድንሆን ካስቻሉን አባቶቻችን ገድል ወዲህ የተፈጠርን የኢትዮጲያ ትውልዶች በግለሰብ ደረጃ ከሚስተዋሉ የተበጣጠሱ ስኬቶች በስተቀር የአባቶቻችንን ታሪክ ከመቁጠር ውጭ በአገር ደረጃ ታሪክ መስራት አቅቶን ቆመን ቀርተናል፡፡ በፕሮፌሰር መስፍን አገላለፅ ከሽፈናል፡፡ በተለይ በልማት እድገትና እኩል ተጠቃሚነት (ሙሰኞች ዘርፈውናል)፣ በሳይንስና ቴክኖሎጅ፣ ወ.ዘ.ተ፡፡ 

ከዚህ አንፃር የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህምድን የኖቤል ሽልማት በአገር ደረጃ  አዲስ ታሪክ የመስራት ጅማሮ አድርጌ ወስጀዋለሁ፡፡ በልማቱ፣ በፈጠራው፣ በሳይንስና ቴክኖሎጅው፣ ጅምሩ ከቀጠለ….

Filed in: Amharic