>

የዐቢይ አሕመድ የአገር ሽማግሌዎች እነማን ናቸው?  (አቻምየለህ ታምሩ)

የዐቢይ አሕመድ የአገር ሽማግሌዎች እነማን ናቸው? 

 

አቻምየለህ ታምሩ
ከፊትለፊት  በወንበር ላይ ከተቀመጡት  ሰዎች በስተቀኝ በኩል ያለው [በቀይ የተለመከተው] የዐቢይ አሕመድ የአገር ሽማግሌ የኦነግ  አምበሉ  አባቢያ አባ ጆቢር አባ ጅፋር ነው። አባቢያ የጅማው ንጉሥ የአባ ጅፋር የልጅ ልጅ ነው። አባቱ አባ ጆቢር የአባ ጅፋር ልጅ ነው።
ሐምቡርግ ዩኒቨርሲቲ እ.ኤ.እ. በ2003 ዓ.ም. አባ ጆቢር  በአረብኛ የጻፈውን የጅማ ንጉሣዊ ቤተሰብ ታሪክ «The History of Jimma and the DiGGO Dynasty» በሚል በእንግሊዝኛ ተርጉሞ ያሳተመውን መጽሐፍ አንብቤያለሁ። ኦነጋውያን አባ ጅፋርን ኦሮሞ  አድርገው « አባ ጅፋር ለምኒልክ ሲገብር የጅማ ነጻነት በምኒልክ ተገፈፈ» እያሉ ቢያላዝኑም አባ ጆቢር ግን  ዘራቸው አረብ መሆኑን፤ ከአረብም ከነበቢዩ መሐመድ እደሚወለዱ፤ ለባሪያ ንግድ መጥተው ጅማ እንደቀሩ  ስለ ቤተሰቡ በጻፈው ታሪክ ነግሮናል። ስለዚህ ታሪክ ወደፊት ከነዶሴው እመለስበታለሁ።
አባ ጆቢር ጥሊያን ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ የአማራ ራስ ቆርጦ ለሚወስድለት ሰው  በያንዳንዱ የተቆረጠ የአማራ ራስ ሰላሳ ብር ሽልማት ይሰጥ ነበር። ይህን የጭካኔ ጥግ  የዐይን ምስክሩ ታላቁ አርበኛ፣ ዲፕሎማትና የሥነ ጽሑፍ ሰው ሐዲስ አለማየሁ «ትዝታ» በሚል በጻፈው መጽሐፉ ከገጽ 166-167 በዝርዝር ጽፎታል።
አባቢያ አባጆቢር በ1983 ዓ.ም. ደርግና ተገንጣዮች ለንደን ላይ በኸርማን ኮሕን «ሸምጋይነት» «ሲደራደሩ» ኦነግን ወክሎ ከገተኙት ተገንጣዮች መካከል አንዱ ነበር። ከቀናት በኋላ ኦነግ በ1983 ዓ.ም. በወያኔ ግብዣ የሽግግር መንግሥት አካል ሆኖ አዲስ አበባ ሲገባ  ኦነግን ወክሎ  የሽግግር መንግሥት  ተብዮው ምክር ቤት አባል ሆነ። ወያኔ ኦነግን ከአገር ሲያባርር አባቢያ ካገር ወጥቶ በ2000 ዓ.ም. በፕሮፌሰር ኤፍሬም ሸምጋይነት ወደ አገር ቤት ገብቷል።
በ1984 ዓ.ም. በአርባጉጉ፣ በወተርና በሐረጌ በአማሮች ላይ የተካሄደው  ጭፍጨፋ በኦነግ አመራር ትዕዛዝ የተካሄደ መሆኑን አባቢያ በሽግግር ምክር ቤቱ ፊት ማመኑን ነጋሶ ጊዳዳ በመጽሐፉ ነግሮናል። በሌላ አነጋገር  አባቢያ እንደ ኦነግ አመራርነቱ  በአርባጉጉ፣ በወተርና በሐረጌ  ኦነግ በአማሮች ላይ ባካሄደው ጭፍጨፋ  ተጠያቂ የሆነ የአማራ ባለደም ነው። ለዚህም ማስረጃው ከራሱ በላይ ምስክር ሊቀርብ አይችልም። አባቢያ የሰጠው ምስክርነት በምስልና በድም የተቀዳና በሽግግር መንግሥት ተብዮው የድምጽና የምስል ላይበራሪ ውስጥ  ዛሬም ድረስ ተመርጆ ይገኛል።
እንግዲህ! ዐቢይ አሕመድ  የአገር ሽማግሌ አድርጎ የሾመው  አባቱም እሱም በአማራ ደም የተጨማለቀውን አባቢያ አባጆቢርን ነው። ድንቄም የአገር ሽማግሌ!
ሌለኛው የዐቢይ የአገር ሽማግሌ የወያኔ ሎሌው  ፓስተር ዳንኤል ገብረ ሥላሴ ነው።  ፓስተር ዳንኤል ከቆሙት መካከል በቀይ የተመለከተው ነው። ፓስተር ዳንኤል  በወያኔ ዘመን ሲሰራው የኖረውን ነውረኛነት ሰው ሁሉ ስለሚያውቀው  ስለሱ በመጻፍ የአንባቢን ጊዜ አላባክንም።
ባጭሩ  የዐቢይ አሕመድ የአገር ሽማግሌዎች  ጸረ አማራ፣ ፀረ ኢትዮጵያኖቹ ኦነግና ወያኔ ናቸው!  ድመት መንኩሳ ነውና ኦነግና ወያኔ በአገር ሽማግሌነት ከተሰየሙበት መድረክ  ከ1983ቱ የሽግግር መንግሥት ተብዬ ውጤት የተለየ ውጤት የሚጠብቅ ቢኖር  ቢቀቀል ቢቀቀል የማይበስል የአሞራ ስጋ ብቻ ነው።
Filed in: Amharic