>
5:13 pm - Monday April 19, 0162

¨ የሰላሙ መጀመሪያም መጨረሻም አብይ አህመድ ነዉ! ሽልማቱም ይገባዋል!!! ¨ (ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ) 

የሰላሙ መጀመሪያም መጨረሻም አብይ አህመድ ነዉ! ሽልማቱም ይገባዋል!!!

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ 
በታዬ ቦጋለ
ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ጠዋት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ስለ ኢትዮ-ኤርትራ እርቅ እና የዶ/ር አብይን አስተዋፅኦ አስመልክቶ ይህን ብለዋል፦
◉”አብይ የተለየ ሰዉ ነዉ። እሱን በቃላት መግለፅ ይከብዳል” በኢትዮ ኤርትራ ጉዳይ ህወሓትም ሆነ ኢህአዴግ ምንም ያበረከቱት ሚና የለም። ➲ የድርድሩ ስኬት ሚስጢር እራሱ አብይ አህመድ ነዉ። ኢህአዴግም ሆነ ህወሓት ለሰላም ፍላጎት ቢኖራቸው ሃያ አመት ምን አስጠበቃቸዉ?
◉መጀመሪያ ላይ አብይ ያሾፋል ብዬ እየጠረጠርኩኝ ነበር። እሱ ያደረገልኝን ጥሪ የተቀበልኩት፣ በጣም እየገረመኝ ነበር። በሂደት ነዉ ከትንሽ ጊዜ በኋላ አብይ እዉነተኛ የሰላም አምባሳደር መሆኑን ያወኩትና እንደ ልጄ ማየት የጀመርኩት። በእዉነት እላችኋለሁ አብይ ነዉ ሁለቱን ሀገራት ያስታረቀዉ ማለት እንችላለን።ምክንያቱም አብይ የሰላም ጥሪዉን ባያደርግልን እኛ ከመሬት ተነስተን እንታረቅ ብለን እንጠይቃለን ብዬ አልገምትም።
◉ዛሬ እንደምታዉቁት ኤርትራዉያን እንደልባቸዉ ያለምንም ስጋት ኢትዮጵያ ዉስጥ ይንቀሳቀሳሉ። ኢትዮጵያዉያንም ኤርትራ ዉስጥ እንደልባቸዉ ይንቀሳቀሳሉ።ይህ ቀላል ነገር እንዳይመስላችሁ።
➲ ያኔ እንደ አብይ ቀና አስተሳሰብ ያለዉ አንድ መሪ ቢኖር ልጆቻችን በጦርነት አያልቁም፣ ንብረቶች አይወድሙም፣ ተለያይተንም ሃያ አመት ባልቆየን… ኪሳራዉ በቀላሉ የሚገመት አይደለም። ይሁን እንጂ አሁን በዶ/ር አብይ የተገኘዉን እድል በአግባቡ ብንጠቀምበት ያንን ኪሳራ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ልናካክስ እንችላለን።
 ◉ብዙ የሄድንበት ጉዳዮች እንዳሉ ሁሉ ብዙ የሚቀሩን ነገሮችም አሉን። ለአብይ የተሰጠዉ የሰላም ኖቤል ሽልማትም ለእስካሁኑ ስራዉ ምስጋና፣ለቀሪዉ ስራዎቻችን ደግሞ ሞራል ይሆነዋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
➲ አንተም ሽልማቱን መጋራት አለብህ የሚሉኝ ሰዎች አሉ፣ በምንም ተአምር አይገባኝም። ቀደም ሲል እንደተናገርኩት የእርቁ ዋና ተዋናይ አብይ አህመድ ነዉ።
 ⭕ የሰላሙ መጀመሪያም መጨረሻም አብይ አህመድ ነዉ!
Filed in: Amharic