>
5:13 pm - Monday April 19, 0123

የኖቤል ሽልማቱ ጣጣ!! (ዮናስ አበራ)

የኖቤል ሽልማቱ ጣጣ!!

ዮናስ አበራ
የዘንድሮውን የሰላም ኖቤል ሽልማት “ያሸነፈው” አብይ አህመድ የፊታችን ማክሰኞ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ተገኝቶ ሽልማቱን ይወስዳል። በሽልማቱ ኮሚቴ ቀደምት ባህል መሰረት ኖቤል ሽልማት የሚያሸንፉ ሰዎች ከአለም ለሚሰባሰቡ ታላላቅ የሚዲያ ጋዜጠኞች ፊት ቀርበው ጥያቄዎች እንዲመልሱ መድረክ ይሰናዳል። ታዲያ የእኛ ጉድ ሽልማቱን ሄጄ እወስዳለሁ፥ ጋዜጠኞች ፊት ቀርቤ ግን ጥያቄ አልመልስም ብሏል። አብይ የኖቤል ኮሚቴውን ታላቅ ውርደት ውስጥ አስገብቶታል የሚሉ አስተያየቶች ከተለያዩ ሚዲያዎች እየተሰጡ ነው። Views and News from Norway በተባለው ዌብ ሳይት (ከታች ይመልከቱ) አብይ “ለህፃናትም ቢሆን ጥያቄ አልመልስም” ብሏል ብሎ ትናንት ባወጣው ዘገባ ላይ አስፍሯል!!  ለህፃናትም ቢሆን!!
ባለፈው ኖቤሉን “አሸነፈ” ሲባል ሰውዬው ሽልማቱ ከቁመቱ በላይ የገዘፈ ነው ያልነው ወደን አልነበረም እኮ። He didn’t deserve it!!
የትናንቱ ኢሳት አለታዊ ላይ ያ ሲሳይ አጌና “አብይ የወሰደው እርምጃ ትክክል ነው፥ ከዚህ ቀደም ባራክ ኦባምም የሰላም ኖቤሉን ከወሰደ በኋላ ጋዜጠኞች ፊት አልቀርብም ብሎ ነበር፥ አዲስ ነገር አይደለም፥ አያስደንቅምም” ሲል ነበር።
Peace Prize winner avoids questions
December 5, 2019
The Norwegian Nobel Committee is grappling with some awkward challenges just days before the man they selected to win this year’s Nobel Peace Prize arrives in Oslo. Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed Ali has made it clear he won’t attend any event where he could publicly be asked questions, either by the press or even children, and the committee finds that “highly problematic.”
For full info find the link in comment box below.
የኖቤል ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር.  እንዲሁም 
– የጠ/ሚሩ ፕረስ ሰክረታሪ ቢለኔ ስዩም ስለ ኖቤል ሽልማት ፕሮግራም ይህን ብለዋል፦
* የኖርዌይ የኖቤል ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ኦላቭ ጆልስታድ ጠ/ሚር አብይ ከአምስት ቀን በሁዋላ ሽልማታቸውን በሚቀበሉበት ወቅት ጥያቄዎች የሚጠየቁበት ፕሮግራም ላይ እንደማይገኙ ገልፀው “ይህ በጣም ችግር ነው። ጠ/ሚር አብይ የኖርዌይ እና የአለም አቀፍ ሚድያ ጋዜጠኞችን ቢያገኙ ምኞቴ ነበር” ብለው ለአሶሼትድ ፕረስ ተናግረዋል።
* ዛሬ የጠ/ሚሩ ፕረስ ሰክረታሪ ቢለኔ ስዩም በላከችልኝ መረጃ “የኖቤል ሽልማት ፕሮግራም ረዥም/ሰፋ ያለ ነው። ለአንድ የሀገር መሪ ሁሉም ፕሮግራሞች ላይ መካፈል አስቸጋሪ ነው፣ በተለይ ሀገር ውስጥ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ባሉበት ወቅት። ስለዚህ ጠ/ሚሩ በተመረጡ እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ፕሮግራሞች ላይ ከኖቤል ኢንስቲትዩት ጋር በመነጋገር ይካፈላሉ” ብላለች።
Filed in: Amharic