>

የቱርክ ወታደራዊ ካምፕ በአዲስ አበባ? (ደረጀ ደስታ)

የቱርክ ወታደራዊ ካምፕ በአዲስ አበባ?

ደረጀ ደስታ
የመካከለኛው ምስራቅና ሰሜን አፍሪካ  የፍትህና ልማት ድርጅትን ሪፖርት በመጥቀስ፣  ኢትዮጵያና ቱርክ የዛሬ ስድስት ዓመት በ2013 በተፈራረሙት ወታደራዊ ስምምነት መሠረት፣ ቱርክ በአዲስ አበባ የጦር ሠፈር ለማቋቋም በመሠረተ ሀሳብ ደረጃ ስምምነት ማግኘቷን፣ የቱርኩ አልዋታን ኢንተርናሽናል አስነብቧል። የድርጅቱን ቃል አቀባይ ዚዳን ካኔን ጠቅሶ የወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ ከቱርክ ውጭ ትልቁን ወታደራዊ የጦር ካምፕ በሶማልያ መቋዲሾ በ2016 ያቋቋመቸው ቱርክ፣ ለውለታው የሶማልያ ወታደሮችን እያሰለጠነች ነው። በጅቡቲም እንዲሁ የጦር ሠፈሯን ለመመስረት ከአገሪቱ ይሁንታን ማግኘቷን በወቅቱ አሳውቃለች።
በጥናቱ መሰረት ቱርክ በአፍሪካ ካላት ኢንቨስትመትን ግማሽ ያህሉን (3 ቢሊዮን ዶላር) በኢትዮጵያ ኢንቨስት ማድረጓን በማስታወስ ወታደራዊ ጦር ካምፑ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆንላት ፍላጎቷ መሆኑም ተዘግቧል። የኢትዮጵያና የቱርክን ወታደራዊ ስምምነት ያልደገፈችው ግብጽ ተቃውሞዋን ብታሰማም የስምምነቱን ተግባራዊነት ማስቀረት መቻሏን ዘጋቢዎቹ ተጠራጥረዋል። በምስራቅ አፍሪካ በተለይም በጅቡቲ የወታደራዊ ጦር ካምፕ ምሰረታው ተጧጡፏል። በሌላ ማስታወሻ እናየዋለን። የቱርኮቹ ፍላጎት ግን አዲስ አበባ ላይ መሆኑ ሳያሳስብ አይቀርም። ስምምንቱ ተግባራዊ ከተደረገ ማለት ነው።
Filed in: Amharic