>

"አዲስ አበባ የማናት' ጥያቄ የማይረባ ጥያቄ አይደለም!!! (ኤርሚያስ ለገሰ)

“አዲስ አበባ የማናት‘ ጥያቄ የማይረባ ጥያቄ አይደለም!!!

ኤርሚያስ ለገሰ
አዲስ አበባ የማናት የሚለው ጥያቄ የምንጠይቀው ያሻግሩናል የተባሉት ሰዎች በመግለጫ ‘የኛ ናት’ ስላሉን ነው!!!
የአዲስ አበባ 133 ኛ አመት የኢዜማ መሪ የሆኑት ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አንድ ነገር ሲናገሩ ሰማሁ…. “አዲስ አበባ የማናት የሚለው ጥያቄ የማይረባ ጥያቄ ነው” ቃል በቃል ይህንን ነው ያሉት ። እርግጥ አዲስ አበባ የማናት የሚለው ጥያቄ የማይረባ ጥያቄ ቢሆን ኖሮ ትተነው ወደ ቤታችን ፣ ወደ ቤተሰቦቻችን እንሄድ ነበር። ጊዜያችንንም ባላጠፋን ነበር። ማይረባ ጥያቄ ቢሆን ኖሮ አዲስ አበባ የማናት? የሚለው ጥያቄ አዲስ አበባ የትግል ማዕከል አትሆንም ነበር። አዲስ አበባ የማናት ብለን የምንጠይቀው…. ባለቤቶቿ ባለቤት ስላልሆኑ ነው ፣ ባለቤት መሆን የሚገባቸው ባለቤት ስላልሆኑ ነው። አዲስ አበባ የማናት? ብለን የምንጠይቀው የማይረባ ጥያቄ ሆኖ ሳይሆን ያሻግሩናል ያልናቸው ሳይሆን በመግለጫ አዲስ አበባ የኛ ናት ስላሉን ነው ፣ ኬኛ ስላሉን ነው። እንደ ሁለተኛ ዜጋ መኖር ትችላላቹ ባለቤት ግን አይደላችሁም ስላሉን ነው፡፡ ፣ አዲስ አበባ የማናት የሚረባ የህልውና ጥያቄ የሆነው ያሻግሩናል የተባሉ ሰዎች በልዩ ጥቅም ስም አዲስ አበባን ሊጠቀልሉ ስላሰቡ ነው!።
ስለዚህ የአዲስ አበባ ጥያቄችየማይረባ ጥያቄ አይደለም የአዲስ አበባ ጥያቄ የህልውና ጥያቄ ነው ፣ የመሞትና ያለመሞት ጥያቄ ነው። በቅርቡ ቦሌ ሚካኤል ቤተክርስትያን የተፈፀመው ጥሩ ማሳያ ነው እስክንድር እንደገለፀው በዛች ጠባብ ሰአት ተሰባስበው የመጡት ድንገት አይደለም! የተበተኑ ሃይል ስላልሆኑና ስለተደራጁ ነው። በመሆኑም የህዝቡን ሕልውና ለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ፖሊስን ከተረኞቹ ማላቀቅ ያስፈልጋል። ከተረኞቹ ስናላቅቀው እኩል መብት ይኖረናል ማለት ነው።
ስለዚህ የአዲስ አበባ ጉዳይ የማይረባ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው!
Filed in: Amharic