>

አይ ቲም ??? (ያሬድ ሀይለማርያም)

አይ ቲም ???

ያሬድ ሀይለማርያም
ጎበዝ ለውጡን የሚመራው ቡድን ወገቤን ማለት ከጀመረ እኮ ውሎ አደረ። የለማም ዛሬ በቬኦኤ መደመር እና ብልጽግና ባፍንጫዮ ይውጣ ማለት ሰበር ዜና ሊሆን አይችልም። ወሬው እየተሸራረፈም ቢሆን ሲያለማምዱን ቆይተዋል። አሁን ማሰብ የሚያስፈልገው ይች አገር እና ይህ ድሃ ሕዝብ ምንድን ነው የተደገሰለት የሚለው ነው። ኦዴፓ እየተንሸራተተ እንደሆነ እኮ ከአመት በፊት ምልክቶች ታይተው ስጋታችንን ስንገልጽ ነበር። የአቶ ለማም ነገር ከኢትዮጵያ ሱሴ ወደ ዲሞግራፊ የተሸጋገረ ለት ይች ነገር ወዴት እያመራች ነው ብለን ነበር። የገዢው ፓርቲ አባል ድርጅቶች እርስ በርስ መጎነታተል እና በአደባባይ መግለጫ እያወጡ መነቋቆር ሲጀምሩ እና የለውጥ ኃይሉ ሕግ እና ሥርዓት ማስከበር እየተሳነው ሲመጣ እኛንም እናንተንም አብሮ የሚያሻግረን አንድ ብሄራዊ ንቅናቄ የግድ ያስፈልጋል በለን አሳስበን ነበር። አሁን ግራ የገባ ነገር ነው። ለማን የሚያህል የለውጡ ሞተር ተደርጎ የሚጠቀስ ሰው እኔ የለሁበትም ማለት መዘዙ ብዙ ነው።
እስኪ ልክ እንደ ዲሞግራፊዋ የዛሬው የቪኦኤ መግለጫም ከእኔ ሃሳብ ውጭ የተተረጎመ እና ማለት የፈለኩትን የሚያሳይ አይደለም ብለው ከርመው መግለጫ ይሰጡናል ብለን ተስፋ እናድርግ።
Filed in: Amharic